የተጀመሩ አበረታች ተግባራትን በማጠናከር ዞኑን በሁሉም ዘርፍ ግንባር ቀደም ለማድረግ አመራሩ በቁርጠኝነት ሊሠራ ይገባል ሲሉ የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር
የጎፋ ዞን መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
ቀን 2022-11-02
የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ጌትነት በጋሻው የአስተዳደር ምክር ቤቱን የ 2015 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ግምግመዋል። የአፈፃፀም ግምገማው በዋናነት ትኩረት ያደርገው በኢኮኖሚያዊ ፣ በማህበራዊና በአስተዳደራዊ ዘርፎች የሚገኙ ሴክተሮች ዋና ዋና ተግባራትን መነሻ በማድረግ በጥንካሬ እና በጉድለት የተለዩ ተግባራት ላይ ነው። በ 2015 በጀት ዓመት በ1ኛው ሩብ ዓመት በኢኮኖሚ ፣ ማህበራዊ እና አስተዳደራዊ ዘርፍ ባሉ ሴክተሮች መልካም የጅምር ሥራዎች መታየታቸው በመድረኩ ተገልጿል። ዶ/ር ጌትነት በጋሻው በመድረኩ እንደገለፁት ዞኑን ለማስተዋወቅ የተጀመሩ ዘርፈ ብዙ ሥራዎች ተጠናክረው በመቀጠል ዞናችንን በኢትዮጵያ ከማሳወቅ አልፈን ለሌሎች የአለማችን ክፍሎች ማሳወቅ ይገባናል ብለዋል። ዋና አስተዳዳሪው አክለውም ግብርናን ማዘመንና የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማሻሻል ጎፋ ከራሷ አልፋ ለኢትዮጵያ የሚበቃ ምርት ለማምረት እንድትችል ከአመራሩ ጀምሮ እስከ አርሶ አደሩ ድረስ በቁጭት መረባረብ እንደሚገባ ገልፀዋል። በተለይ የስንዴ ምርት ከሀገር ውስጥ ፍጆታ አልፎ ለውጭ ገበያ እንዲቀርብና የቅመማ ቅመም ምርቶችን በስፋትና በጥራት ማምረት እንደሚገባ ዶ/ር ጌትነት በጋሻው ገልፀዋል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ15ኛ ጊዜ የሚከበረው ብሔራዊ የሰንደቅዓላማ ቀን በጎፋ ዞን በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ተከበረ
የጎፋ ዞን መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
ቀን 2022-10-18
በደቡብ ክልል "ሰንደቅ አላማችን የብዝሐነታችን መገለጫ፤ የሉዓላዊነታችን ምሰሶ ነው" በሚል መሪ ቃል ለ15ኛ ጊዜ የሚከበረው የዘንድሮው ብሔራዊ የሰንደቅዓላማ ቀን በጎፋ ዞን በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ተከብሯል። የጎፋ ዞን ሕዝብ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ጠንክር ጠንካ በተሻሻለው የሰንደቅ አላማ አዋጅ ቁጥር 863/2006 መሰረት የሰንደቅ አላማ ቀን በየዓመቱ ጥቅምት ወር በገባ የመጀመሪያው ሰኞ የሚከበር መሆኑን በመድረኩ ተናግረዋል። የዘንድሮው ብሄራዊ የሰንደቅዓላማ ቀን በሚከበርበት ወቅት ሃገራዊ ነባራዊ ሁኔታውን በማሰብ የሀገር አንድነትና ሉአላዊ ክብር የሚረጋገጥበት ልዩ ምልክት ወይም አርማ መሆኑን ስለ ብሔራዊ ክብር ዜጎች እንዲረዱ በማድረግ ሊሆን ይገባልም ብለዋል፡፡ ሰንደቅ አላማ ቀን ሲከበር ብሄራዊ አንድነትንና የዜጎችና ብሄሮች ብሄረሰቦች አንድነትና ወንድማማችነት ትስስር የሚያጠናክር ይሆናልም ተብሏል፡፡ የሰንደቅ አላማ ቀን በዓል ሲከበር ወቅታዊ ሁኔታዎችን ታሳቢ አድርጎ የሚከበር ሲሆን የሃገራዊ ለውጥ እንቅስቃሴውንና ሃገራችን ያለችበትን ሁኔታ በመገንዘብ ወጣቱ ወይም አዲሱ ትውልድ የሰንደቅ አላማን ክብርና ምንነት መረዳት ያስችለዋል ብለዋል፡፡ የጎፋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አብርሃም ዞራ በበኩላቸው ሰንደቅዓላማችን የነፃነታችንና የክብራችን መገለጫ ነው ሲሉ ተናግረዋል። የሰንደቅዓላማ ቀን ስናከብር ከመንግሥትና ከሕዝብ የተሰጠንን አደራና ኃላፊነት በማሰብ በተሰማራንበት የሥራ መስክ ጠንክረን በመስራት የኢትዮጵያን ብልጽግና ራዕይ እውን ለማድረግ ቃል የምንገባበት መሆኑን ገልጸዋል። የዘንድሮው የሰንደቅዓላማ ቀን ለየት የሚያደርገው ነገር ቢኖር አሸባሪው የሕወሓት ቡድን ከውጭ ታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር በማበር የከፈተብንን ጦርነት እየመከትንና የሀገራችንን ሉአላዊነት ለማስከበር ሁላችንም በአንድነት በቆምንበት ወቅት ላይ መከበሩ ነው ብለዋል። የዘንድሮው የሰንደቅዓላማ ቀን በጎፋ ዞን ስር በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደር መዋቅሮች በድምቀት ተከብሯል። በመርሃ ግብሩ ላይ የዞኑ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የሁሉም መምሪያና ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል። የጎፋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ፀጋዬ ጽጌ ታዳሚዎችን ቃለ-መሃላ ያስገቡ ሲሆን፣ በመጨረሻም የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር በመዘመር መርሃግብሩ ተጠናቋል።
በጎፋ ዞን ኡባ ደብረፀሃይ ወረዳ በግብርናው ዘርፍ የተጀመሩ የኢንቨስትመንት ስራዎች ለዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማምጣት ሚናቸው የጎላ
የጎፋ ዞን መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
ቀን 2022-10-06
የጎፋ ዞን ሴቶች አደረጃጀቶች 4 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ሰንባች ምግብ ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ማስረከቡን የሰንባች ምግብ የሀብት አሰባሰብ ኮሚቴ አስታወቀ። በዚህም መሠረት 336 ማዳበሪያ በሶ በገንዘብ ሲተመን 3 ሚሊዮን 564 ሺህ እንዲሁም 11 ኩንታል ስኳር በገንዘብ ሲተመን 121 ሺህ ሲሆን በአጠቃላይ በገንዘብ ሲተመን 3 ሚሊዮን 685 ሺህ ብር የሚሆን የሰንባች ምግብ ለመከላከያ ሠራዊት አስረክበዋል።
ያግኙን
☏046-777-1536
ተዛማጅ ሊንኮች
Copyright © 2021-2025 Gofa Zone Adminstration.All Rights Reserved
Gofa,Ethiopia