የጎፋ እድገትና ብልጽግና ማህበር የህዝቡን የልማት ፍላጎት ለማሟላት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑ ተገለጸ
የጎፋ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
ቀን 2022-03-07
የጎፋ እድገትና ብልጽግና ማህበር በማህበሩ እንቅስቃሴ ዙሪያ ለጎፋ ዞን ወጣቶች ፌዴሬሽን፣ ማህበራትና ሊግ አመራሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷቸዋል። የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ አቶ ደግፌ ኃ/ማሪያም የማህበሩን ራዕይ እውን ለማድረግና ተልዕኮውን ለማሳካት ለወጣቶችና ሴቶች የሚሰጡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች የማይተካ ሚና ይጫወታል ሲሉ ተናግረዋል። የጎፋ ህዝብ በዞን መዋቅር የመደራጀት ጥያቄ ምላሽ ባገኘበት ማግስት በይፋ የተመሠረተው የጎፋ ዕድገትና ብልጽግና ማህበር ህዝባዊ መሠረት እንዲኖረው ለማስቻል ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ማህበሩ ከ300 ሺህ በላይ አባላት መኖራቸውን የጠቆሙት የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ አቶ ደግፌ፣ የማህበረሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ ከአንድ ሚሊዮን በላይ አባላትን ለማፍራት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል። የህዝቡን የልማት ፍላጎት ለማሟላት ከሚሰሩ ስራዎች ባለፈ አካባቢውን የማስተዋወቅ ስራ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ አቶ ደግፌ ኃ/ማሪያም ተናግረዋል። የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ሊግ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወንድም ኪሩቤል ይስሐቅ በበኩላቸው በየመዋቅሩ የወጣቶች አደረጃጀት በማጠናከርና ስለልማት ማህበሩ ግንዛቤያቸውን በማሳደግ ራዕዩን እውን ለማድረግ እንደሚሰራም ተናግረዋል። በስልጠና መድረኩ ተሳታፊ የነበሩ ወጣቶች በበኩላቸው ልማት ማህበሩ እንዲጠናከርና የሚጠበቀውን ውጤት ለማምጣት የጎፋ ዞን ተወላጆችና ምሁራን አንድነት ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል። የማህበረሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ ከልማት ማህበሩ ጋር በቅንጅት እንደሚሰሩ የገለጹት ሰልጣኞቹ፣ ከማህበሩ ጎን በመቆም አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
የጎፋ ዞን የሀይማኖት ፎረም አመራሮች ከዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ጌትነት በጋሻው ጋር በዘላቂ ሰላም ግንባታ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ።
የጎፋ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
ቀን 2022-03-02
የጎፋ ዞን የሀይማኖት ፎረም አመራሮች ከዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ጌትነት በጋሻው ጋር በዘላቂ ሰላም ግንባታ እና በቀጣይ የፎረሙ ተግባራት ዙሪያ ውይይት አካሄዱ። በመድረኩ እስካሁን በፎረሙ የተከናወኑ ተግባራት በፎረሙ አመራሮች ዝርዝር ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በቀጣይም ከመንግስትና ከባለድርሻ አካላት በመቀናጀት በሰላም ዙሪያ የግንዛቤና የአስተምሮት ሥራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልፀዋል። የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ጌትነት በበኩላቸው የሀይማኖቶች የጋራ ፎረም አመራሮች ባከናወኗቸው ተግባራት ምስጋና አቅርበው የሀገራችንን ብሎም የዞናችንን ሠላም የሚያደፈርሱ ኃይሎች መኖራቸውን ተናግረው የሀይማኖት ተቋማት ያለልዩነት ለሠላም የሚተጉ፣ የሠላም ሰባኪዎች፣ የሠላም አስተማሪዎችና ተምሳሌቶች በመሆናችሁ የሚከሰቱ ግጭቶችንና አለመግባባቶችን በዘላቂነት በመፍታት የበኩላቸውን ድርሻ አጠናክራችሁ ልትወጡ ይገባል ብለዋል፡፡ በውይይቱ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪው አክለውም በዞናችን በርካታ ሀይማኖቶችና ቤተ-እምነቶች የሚገኙበት ዞን መሆኑንና ለበርካታ ዘመናት ተከባብረውና ተደጋግፈው እንደሚኖሩ አስተዳዳሪው ተናግረው በዞናችን በተለያዩ አካባቢዎች የሚከሰቱ አለመግባባቶችና ግጭቶች ለመፍታት የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በሠላም ዕሴት ግንባታ ዙሪያ በርካታ ሥራዎችን በመስራት ያበረከቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው ለዝህም አክብሮትና ምስጋና እንደሚገባቸው ገልፀዋል።
የጎፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የአመራር ግንባታ መድረክ ዛሬ ማካሄድ ጀመረ።
የጎፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት
ቀን 2022-02-07
የጎፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ "መመረጥ ተለውጦ ሀገርን ለመለወጥ" በሚል መሪ ቃል ዞናዊ የአመራር ግንባታ የውይይት መድረክ ጀምሯል። በአመራሮች የአቅም ግንባታ የውይይት መድረክ የተገኙት የደቡብ ክልል የፋ/ኢኮ/ል/ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈሪ አባተ እና የክልሉ ከተማ ልማት ቢ/ም/ኃላፊ አቶ ቶፊቅ ጁሀር እና የጎፋ ዞን ዋና አስተዳደር ዶክተር ጌትነት በጋሻው ሲሆን ማንኛምውም ፍትሃዊነትን የሚያዛቡ አሉታዊ ተግባራትን አጥፍቶ በምትኩ በዘመናዊነት የታገዘ ፍትሃዊ አሰራርን ለመዘርጋት የጠራ አመራር እንደሚያስፈልገው ፓርቲያችን ያምናል በማለት መድረክ በስፋት አስገንዝቧል ። አቶ ተፈሪ አባተ እንደገለጹት ከዛሬ ጀምሮ ለ4 ቀናት "መመረጥ ተለዉጦ ሀገርን ለመለወጥ" በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄደው የአመራር ግንባታ ሥልጠና የህዝቡን አደራ ለመወጣት የሚያስችል አቅም የመገንባት ተልዕኮ ያለዉ ነዉ ብለዋል። አስተዋዩ ህዝብ የዉስጥና የዉጪ ፈተናዎችን ተቋቁሞ፣ ስንከባለል የመጣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮቹን በታጋሽነት ይዞ ብልጽግና ፓርቲን መርጧል። ህዝባችን ፓርቲው በምርጫዉ ወቅት ይዞት የቀረበዉን የአምስት ዓመት ሚኒፌስቶ መሰረት አድርጎ ፓርቲውን ሲመርጥ ህዝቡ ለፓርቲዉ የሰጠዉ አደራና የቤት ሥራ ከፍተኛ መሆኑን ብልጽግና ፓርቲ ይገነዘባል ያሉት አቶ ተፈሪ አባተ ገልጸዋል። የፓርቲው ዓላማና ተልዕኮን ለመፈጸምና ለማስፈጸም አመራሩ የጠራ አቋም በመያዝ ህዝቡና አካባቢን ለመምራት ቁርጠኛ እንዲሆን ይህ መድረክ ወሳኝ በመሆኑ የአመራሩ ዲስፕሊን ተጠብቆ አስተማሪ የሆነ የመገነባባት ጊዜ በማድረግ ልጠቀሙ ይገባል ብለዋል። የጎፋ ዞን አስተዳዳሪ ዶክተር ጌትነት በጋሻው በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጹት ፓርቲው ለህዝብ የገባውን ቃል በተግባር ለመመለስ፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ወሳኝ መድረክ ነው ብለዋል። ዶክተር ጌትነት በጋሻው አክለውም ፓርቲ ህዝቡ በሀገራዊ የምርጫ ወቅት የሰጠዉን አደራ አክብሮና ጠብቆ ለመወጣት ደፋ ቀና እያለ ምላሽ ከመስጠቱም ባለፈ ሰፊዉን ህዝብ ከጎኑ አሰልፎ በሁሉም ዘርፍ ብልጽግናን ለማረጋገጥ እየሰራ ይገኛል። በብልጽግና ፓርቲ የሚመራዉ መንግስት በአንድ በኩል የኢትዮጵያን ለዉጥ ተቃርነዉ የቆሙ እና ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚሠሩ የዉስጥና የዉጪ ጠላቶችን ህዝቡን አስተባብሮ እየመከተ ተደራራቢ ድል ያስመዘገበ በመሆኑ የሚጠናክር አካል መጥራት አለበት ብለዋል። አዳጊ ደሞክራሲያዊ ስርዓት የሚያንኮታኩቱ መጥፎ ልማዶችን በተለይም ሙስና ጎታች አስተሳሰብ፣ ኢመደበኛ አደረጃጀት ወዘተ የመሳሰሉ ፍላጎቶችን ለመበጣጠስ የሚቻለው ጠንካራ ፓርቲና የጠራ አቋም ያለው አመራር ሲገነባ ነው። ያልተገባ የጥቅም ትስስር ያላቸዉን ሰንሰለቶች የመበጣጠስ ተግባር ላይ በተቀናጀና የሪፎረም ሥራውን በሚያሳልጥ መልኩ እንደሚፈፀም አቅጣጫ ተቀምጠዋል አቶ ቶፊቅ ጁሀር ገልጸዋል። በአመራሮች የአቅም ግንባታ የውይይት መድረክ የዞን ከፍተኛ አመራሮችና የወረዳና ከተማ አስተባባሪ አካላት ተገኝተዋል። መድረኩ እስከታችኛው የፓርቲ መዋቅር እስከ አባሉ ድረስ እንደሚወርድ ዋና አስተዳዳሪው አክለዋል።
ያግኙን
☏046-777-1536
ተዛማጅ ሊንኮች
Copyright © 2021-2025 Gofa Zone Adminstration.All Rights Reserved
Gofa,Ethiopia