በጎፋ ዞን ህዝብ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ጠንክር ጠንካ የተመራ የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ አባላት በኦይዳ ወረዳ በበጋ መስኖ የተዘሩ ስንዴ እና ሌ
አቶ ጠንክር ጠንካ
ቀን 2021-11-17
ታህሳስ 12/2014 ዓ.ም ኦይዳ ወረዳ ሸፊቴ: ግብርናችንን ለማዘመን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግና የምግብ ዋስትናችንን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ የጎፋ ዞን ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ጠንክር ጠንካ አሳሰቡ። የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ አባላት በጉብኝቱ ወቅት እንደገለፁት የግብርና ዘርፍ ለዞናችን ብሎም ለሀገራችን የኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት በመሆኑ ይህንን ዘርፍ ለማዘመንና ለማሳደግ በርካታ ስራዎች መሰራት እደሚገባቸው ተናግረዋል። የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ አባላት አክለውም ሰፊ የውሃ ሀብት እንዲሁም ሰፊ በመስኖ የሚለማ ማሳያ እያለን ባለመስራታችን በዘንድሮ በቁጭት ለመተግበር በቁርጠኝነት መነሳት ተገቢ ነው ብለዋል። በመጨረሻም ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ጠንክር ጠንካ እንደገለፁት ለልማትና ዕድገት ወሳኝ የሚባሉ የተፈጥሮ ሀብቶች መሬት ጉልበትና የውሀ ሀብት በእጃችን እያለ ስለምግብ ዋስትና ችግር ማውራትና በዕርዳታ ስም ተንበርካኪ ሊያደርጉን የሚሹ የእጅ አዙር ቀኝ ገዢዎችን ደግመን ደጋግመን ይበቃል ልንላቸው ይገባል ብለዋል።
ውድ የዞናችን ህዝቦች፣ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፦
ዶ/ር ጌትነት በጋሻው፦ የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ
ቀን 2021-12-08
ከታህሳስ 1-3/2014 ዓ.ም በአጎራባች ደቡብ ኦሞ ዞን ተገኝተን የተለያዩ መርሃግብሮች አከናውነን ተመልሰናል። ታህሳስ 1/2014 ዓ.ም ጂንካ ከተማ ተገኝተን በዞኑ ከሚገኙ 16 ብሔር ብሔረሰቦች መካከል አንዱ የሆነው የአሪ ብሔረሰብ ባህላዊ እሴት የሆነውን ዲሽታ ጊነ የዘመን መለወጫ በዓል ለብሔረሰቡ አባላትና ለመላው የደቡብ ኦሞ ዞን ህዝቦች በጎፋ ዞን አስተዳደር ስም የእንኳን አደረሳችሁና አጋርነት መልዕክት በማስተላለፍ በዓሉን በአብሮነትና ወንድማማችነት መንፈስ አክብረናል። ደቡብ ኦሞ ዞን እና ዞናችን የሚዋሰኑ ከመሆናቸው አንጻር በአብዛኛው በአዋሳኝ መዋቅሮቻችን ያሉ ነዋሪዎች ለዘመናት የዘለቀ በአዎንታዊ መልኩ የሚገለጽ መልካም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶች፣ ትስስሮችና እሴቶች ያላቸው መሆኑ ይታወቃል። ሆኖም በውስን አዋሳኝ አካባቢዎች በተለይ በደቡብ ኦሞ ዞን ሳላማጎ ወረዳ በኩል ወደ ዞናችን መሎ ኮዛ ወረዳ አንዳንድ ቀበሌያትና ሰፈራ መንደሮች በመምጣት ለአመታት የዘለቀ በአርብቶ አደሮች የሚፈጸም ጥቃትና ዝርፊያ መኖሩን በተደጋጋሚ ያስተዋልነው፣ በተለያዩ ጊዜያትም ስለመፍትሄው የተመከረበት ጉዳይ ነው። አጎራባች የባስኬቶ ልዩ ወረዳም የአርብቶ አደሮቹ ጥቃት ሰለባ መሆኑ ይስተዋላል። በመሆኑም በሁለተኛው ቀን ቆይታችን ከችግሩ አሳሳቢነት አኳያ ወንድማማችነትና መልካም ግንኙነትን መሰረት ያደረገ ለጋራ ችግራችን የጋራ መፍትሄ ለመፈለግ በደቡብ ኦሞ ዞን ጅንካ ከተማ የደቡብ ኦሞ ዞን፣ ጎፋ ዞን እና ባስኬቶ ልዩ ወረዳ የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት በሶስትዮሽ መድረክ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል። በውይይታችንም ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ መስጠት እንዲያስችለን በጋራ የምናከናውናቸው ቀጣይ ተግባራት ላይ የጊዜ ሰሌዳ ጭምር በማስቀመጥ መድረኩን በተግባቦት አጠናቀናል። በሦስተኛው ቀን ቆይታችን ለወገን ደራሽ ወገን ነውና በክልሉ መንግስት በኩል በቀረበልን ጥሪ መሠረት በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ በተፈጥሮና ሰው ሠራሽ ምክንያቶች በሰውና እንስሳት ላይ የተከሰተውን እጅግ አሳዛኝ መፈናቀልና የድርቅ አደጋ ለመቋቋም የዞናችንና ህዝባችን አቅም በፈቀደ መጠን ያዘጋጀነውን 95 ቶን የእንስሳት መኖ (ሣር) እና ለተፈናቀሉ ወገኖች እንዲውል የተወሰነውን 192 ኩንታል ስኳር በወረዳው ኦሞ ራተ ከተማ ተገኝተን ድጋፍ አድርገናል። ወደ ዞናችን ተመልሰን በዛሬው እለት ታህሣስ 4/2014 ዓ.ም በሣውላ ከተማ አስተዳደር አዘጋጅነት የከተማው ህዝብ (መንግስት ሰራተኛው፣ የንግዱ ማህበረሰብና ባለሀብቶች፣ አነስተኛ ገቢ ያላቸው የከተማው ነዋሪዎች፣ አርሶአደሮች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች፣ ልዩ ልዩ ተቋማት፣ ወዘተ) በአምስት ተከታታይ ዙሮች ከ8 ሚሊዮን ብር በላይ ሀብት በገንዘብና በአይነት ለሀገር መከላከያ ሠራዊት በመስጠታቸው እንዲሁም በጉልበትና ሞራል እያደረጉ ስላሉት ድጋፍ ምስጋናና ዕውቅና ለመስጠት በተዘጋጀው መርሃ ግብር ላይ በመገኘት ምስጋና በማቅረብ በቀጣይም ህዝቡ ስለሚኖረው ሚና መልዕክት አስተላልፈናል። በምስጋናና ዕውቅና መድረኩ እጅግ ያስደመመኝ ደግሞ የከተማው ነጋዴዎች እስከአሁን በግል ካደረጉት ድጋፍ ባሻገር በየሣምንቱ ከሚጥሉት ዕቁብ በመተዳደሪያ ደንባቸው መሠረት በየሣምንቱ ለአባላት ተቀማጭ ከሚያደርጉት ገንዘብ በራሳቸው ተነሳሽነት ለሦስት ሣምንታት ተቀማጭ የሚደረግ የአባላት ድርሻን ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ድጋፍ እንዲውል በጋራ ወስነው በዛሬው ዕለት 361,800 ብር ቼክ ለሣውላ ከተማ እና ዞን አስተዳደር አስረክበዋል። ከተማ አስተዳደሩም ድጋፉ ወደ ሀገር መከላከያ ሠራዊት ድጋፍ አካውንት በዛሬው ዕለት ገቢ እንዲሆን (እንዲተላለፍ) አድርጓል። ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የሚደረግ ድጋፍን በተመለከተ መላው የዞናችን ህዝቦች (አርሶአደሮች፣ የመንግስት ሰራተኞ፣ የንግዱ ማህበረሰብና ባለሀብቶች፣ አነስተኛ ገቢ ያላቸው የከተማና የገጠር ነዋሪዎች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች፣ ልዩ ልዩ ተቋማት፣ ወዘተ) በአምስት ተከታታይ ዙሮች ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ሀብት በገንዘብና በአይነት ድጋፍ በማድረግ እጅግ አኩሪ ታሪክ ሰርተዋል። ሕዝባችን በከፍተኛ ቅንዓትና የሀገር ፍቅር ስሜት ለሠራዊቱ እያደረገ ያለው ቁርጠኛ ድጋፍ፣ እየሰጠ ያለው ሞራልና አለኝታ፣ በግንባር የተሰለፉ ወንድምና እህቶቻችን እየፈጸሙ ያለው ተጋድሎ ብሎም አዲስ ምልምል ወጣቶች ከሠራዊቱ ጎን ለመቆም ያሳዩት ተነሳሽነት በቃላት ከሚገለጽ ምስጋናና ዕውቅና በላይ ነው። የሀገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች ታሪክን በማስታወስ በምክር፣ በፀሎት፣ በምርቃትና አለኝታ ሁሌም ከጎናችን በመሆን አባታዊና መንፈሳዊ ሚናቸውን በታላቅነት እየተወጡ ይገኛሉ። ፈጣሪ ረጅም እድሜና ጤና እንዲሰጣቸው ዘወትር እመኝላቸዋለሁ!!! በአጠቃላይ የህዝባችን ቁርጠኛ ድጋፍ፣ የባለሀብቱ አለኝታ፣ የአመራራችን ርብርብና ተጋድሎ እጅግ የሚያኮራና የሚያስደምም ነው። የእስከአሁኑ ሂደት ህዝባችን ዛሬም እንደ ትናንት አባቶቹ፣ አያት ቅድመ አያቶቹ ለሀገር ህልውናና አንድነት እየከፈለ ያለውን ዋጋ የሚያሳይ፣ ታሪክም የሚዘከረው አኩሪ ደጀንነትና ጀግንነት መሆኑ ጥርጥር የለውም። ቸር እንሰንብት!!! ዶ/ር ጌትነት በጋሻው፦ የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ
ያግኙን
☏046-777-1536
ተዛማጅ ሊንኮች
Copyright © 2021-2025 Gofa Zone Adminstration.All Rights Reserved
Gofa,Ethiopia