ከ77 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እየተገነባ የሚገኘው የላሃ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ሕንፃ ግንባታ እየተጠናቀቀ መሆኑ ተገለጸ
የጎፋ ዞን መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
ቀን 2022-08-19
በደቡብ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ከ77 ሚሊዮን 600 መቶ ሺህ ብር በላይ ወጪ እየተገነባ የሚገኘው የላሃ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ሕንፃ ግንባታ እየተጠናቀቀ መሆኑ ተገልጿል። በዚህ ፕሮጀክት ከ100 በላይ የሚሆኑ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ መሆናቸው በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል። የጎፋ ዞን ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና መምሪያ ኃላፊ አቶ አብርሃም አልዬ፣ የዞኑ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ኃላፊ ኢንጂነር ተመስገን ጣሰው እና የላሃ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሰለሞን ስብሐቱ የኮሌጁ ሕንፃ ግንባታ ያለበትን ደረጃ የመስክ ምልከታ አድርገዋል። የመምሪያው ኃላፊ አቶ አብርሃም አልዬ በጉብኝቱ ወቅት የላሃ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ሕንፃ ግንባታ በ2007 ዓ.ም የመሠረተ ድንጋይ የተቀመጠ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች እየተጎተተ መቆየቱን ገልጸዋል። መምሪያው ከክልሉ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ጋር በመቀናጀት ባደረገው ድጋፍና ክትትል በአሁኑ ሰዓት የፕሮጀክቱ ግንባታ 98 በመቶ መድረሱን አቶ አብርሃም ተናግረዋል። የግንባታው ቀሪ ሥራዎች ሲጠናቀቁ የክልልና የጎፋ ዞን ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በቅርቡ እንደሚመረቅና በ2015 ዓ.ም የማሰልጠን ተግባሩን በይፋ እንደሚጀምር አስታውቀዋል። አቶ አብራሃም አያይዘውም የመሎ ኮዛ ወረዳ እና የላሃ ከተማ አስተዳደር ላደረጉት ድጋፍና ክትትል እንዲሁም ግንባታውን እያከናወነ የሚገኘው ብርሃነ ኃይሌ ጠቅላላ የሕንፃ ሥራ ተቋራጭ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የፕሮጀክቱ ግንባታ በተያዘለት ጊዜና ጥራት እንዲከናወን እያደረገ ላለው ጥረት በመምሪያው ሥም ምስጋና አቅረበዋል። የዞኑ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ኃላፊ ኢንጂነር ተመስገን ጣሰው የፕሮጀክቱ አፈፃፀም የደረሰበትን ደረጃ በገመገሙበት ወቅት የፕሮጀክቱ ግንባታ በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የፕሮጀክቱ ቀሪ ሥራዎች በተጀመረው ፍጥነትና ጥራት ማጠናቀቅ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ከተቋራጩ ኃላፊ ጋር ውይይት አካሂደዋል። በዞኑ በሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የተጀመሩ ሌሎች ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜና ጥራት እንዲጠናቀቁ መምሪያው ክትትል እያደረገ መሆኑን ኢንጂነር ተመስገን ተናግረዋል። የላሃ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሰለሞን ስብሃቱ በበኩላቸው በአካባቢው በግንባታ ላይ ከሚገኙ ፕሮጀክቶች መካከል የላሃ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ አንዱ መሆኑን ገልጸዋል። የፕሮጀክቱ ግንባታ በተያዘለት ጊዜና ጥራት እንዲጠናቀቅ ድጋፍና ክትትል በማድረግ የበኩላቸውን ድርሻ እየተወጡ ለሚገኙ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
በጎፋ ዞን ከ 130 ሺህ በላይ ወጣቶች እየተሣተፉበት የሚገኘው የክረምት ወራት በጎ ፍቃድ አገልግሎት በ አንድ ወር ጊዜ ከ 81.5 ሚሊዮን ብር በላይ ማዳን መ
የጎፋ ዞን መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
ቀን 2022-08-16
በጎፋ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ከ 130 ሺህ በላይ ወጣቶች እየተሣተፉበት የሚገኘው ዞናዊ የክረምት ወራት በጎ ፍቃድ አገልግሎት አፈፃፀም ተገምግሟል። የጎፋ ዞን የመንግሥት ረዳት ተጠሪ አቶ ጳውሎስ ፋይሌ ወጣቶች በክረምት ወራት በተለያዩ የትኩረት መስኮች ላይ ወጣቶች አበረታች የበጎ ፍቃድ አገልግሎት እየተሠጡ ሲሆን ይህም ህብረተሰቡን በከፍተኛ ደረጃ እያገዘ መንግሥትንም ከወጪ እያዳነ እንደሆነ ገልፀዋል። በጤናው መስክ 150 ሺህ ብር የሚገመት የጋራ መፀዳጃ ቤት ግንባታ ፣ ለ 121 ሺህ የህብረተሰብ ክፍሎች ተላላፊና ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ፣ 110 ዩኒት የደም ሊገሳ የተደረገ ሲሆን በአጠቃላይ በጤናው ዘርፍ በገንዘብ ሲተመን 10,760,250 ብር መሆኑ ተገልጿል። በትምህርት ዘርፍ ለቅድመ መደበኛ እና ማጠናከሪያ ለ 17159 በመንግሥትና በግል ትምህርት ቤቶች አገልግሎት እና የትምህርት ቁሳቁስ ጥገና የተሠራ ሲሆን በአጠቃላይ በዘርፉ 2,147,500 ብር የሚተመን ሥራ ተሠርቷል። በአጠቃላይ በደን ልማትና አከባቢ ጥበቃ ፣ በማህበራዊ ደህንነት ድጋፍና እንክብካቤ አገልግሎት ፣ በከተሞች ጽዳትና ውበት ፣ የወጣት ማዕከላትን በማስዋብና በማጠናከር ፣ በመንገድ ደህንነትና ትራፊክ ፣ በስፖርትና ኪነ-ጥበባት ፣ የወጣት አደረጃጀቶችን ማጠናከር ፣ በግብርና ልማት ፣ በሠላም እሴት ግንባታ አገልግሎት ፣ የገቢ አሰባሰብ ፣ የንግድና ግብይት ጥራት ፣ የዓባይ ግድብ ድጋፍ ቦንድ ግዥ ፣ ውሃና ፈሳሽ ፣ ኦሞ ማይክሮ ፣ ህብረት ሥራ ዘርፎች ላይ በገንዘብ ሲተመን 68.6 ሚሊዮን ብር የሚገመት አገልግሎት ተሰጥቷል። የጎፋ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ አወቀ አለሙ የወጣቶችን አፈፃፀም እየገመገሙ በጥንካሬ እና በጉድለት በመገምገም የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ እየተሠራ እንደሚገኝ ገልጿል። በቀጣይ ቀሪ ቀናት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ትኩረት ሰጥተው ተግባሩን ወደ ተሻለ አፈፃፀም ለማድረስ መሥራት እንዳለባቸው ተገልጿል።
የሶዶ-ሣውላ-ሸፍቴ አስፋልት መንገድ ግንባታ አሁን ካለበት የአፈፃፀም መጓተት ተላቆ ስራውን ማቀላጠፍ በሚቻልበት ጉዳዮች ዙሪያ ከቤጂንግ ዓርባን ኮንስትራክሽን
የጎፋ ዞን መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
ቀን 2022-08-15
የፌዴራል፣ የክልልና የጎፋ ዞን ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የሶዶ-ሣውላ-ሸፍቴ አስፋልት መንገድ ግንባታ በፍጥነት ማጠናቀቅ በሚቻልበት ጉዳዮች ዙሪያ ከቤጂንግ ዓርባን ኮንስትራክሽን ግሩፕ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሂደዋል። የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ጌትነት በጋሻው የሶዶ-ሣውላ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በተያዘለት ጊዜና ጥራት እንዲጠናቀቅ የዞኑ መንግሥት ከፍተኛ ክትትልና አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ መቆየቱን ገልጸው፣ በተለያዩ ምክንያቶች የመንገዱ ግንባታ እየተጓተተ መሆኑን ተናግረዋል። ዋና አስተዳዳሪው አያይዘውም የዞኑ መንግሥት ለመንገዱ ግንባታ ማነቆ የሆኑ ጉዳዮች በመለየት ፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜና ጥራት እንዲጠናቀቅ ከክልሉ መንግሥት፣ ከፌዴራል መንገዶች ባለሥልጣንና ከተቋራጩ ድርጅት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ በልጅጌ ከሀገራዊ ለውጡ ትሩፋቶች አንዱ የሆነው የሶዶ-ሣውላ አስፋልት መንገድ ግንባታ በጥራት ተሰርቶ እንዲጠናቀቅና በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት እንዲጀምር ሁላችንም የበኩላችንን ኃላፊነት እንወጣለን ሲሉ ተናግረዋል። ይህ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የጎፋ ሕዝብ እንደ ዓይን ብሌን የሚመለከተው መሆኑን የገለጹት አቶ ተስፋዬ፣ በግንባታ ወቅት በሚስተዋሉ ችግሮች ምክንያት መስተጓጐል እንዳይፈጠር የሚመለከታቸው አካላት በቅንጅት መስራት አለባቸው ብለዋል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እና በሚ/ር ዴኤታ ማዕረግ በፍትህ ሚ/ር የፍትህና ሕግ ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይ/ር አቶ ዘካሪያስ እርኮላ በበኩላቸው የሕዝብ እንደራሴዎች እንደመሆናችን መጠን ይህ የመንገድ ፕሮጀክት የሕዝባችን የእድገትና ብልጽግና መሠረት በመሆኑ ክትትል የማድረግ እንዲሁም የማስፈፀም ኃላፊነት አለብን ሲሉ ተናግረዋል። ከተቋራጩ ድርጅት በኩል መንገዱን በተፈለገው ጊዜ እንዳይጠናቀቅ ካደረጉ ምክንያቶች መካከል ከመንገዶች አስተዳደር ያልተከፈለ ክፊያ ወይም የገንዘብ እጥረት ፣ 15 ሺ ቶን የኦፒሲ ሲምንቶ አቅርቦት ችግር ፣ ያልተከፈለ የካሳ ክፊያ ፣ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪዎች ፣ የፀጥታ ችግር ፣ በክረምት ወራት ያለው ከፍተኛ የዝናብ መጠን እንደምክንያትነት የቀረበ ሲሆን ይህም መንገዱ መጠናቀቅ ከነበረበት ጊዜ አንድ አመት ተጨማሪ ጊዜ እንደሚወስድ ገልፀዋል። እንደ ስጋት የተነሳው የፀጥታ ጉዳይ (security issue) በተመለከተ ዞኑ በየጊዜው የሚከታተለውና ምንም አይነት ችግር እንደማይገጥማቸው፣ ስጋትና ጥርጣሬ እንዳይገባቸው ሙሉ ሀላፊነት የሚወስድ መሆኑ ተገልጿል። የወሰን ማስከበር ስራ በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣንና በዞኑ የተቀናጀ ጥረት እልባት እንዲያገኝ ይደረጋል። በኮንትራክተሩ በኩል የቀረቡ ሌሎች ጉዳዮች በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣንና በሚመለከታቸው ተቋማት በትኩረት እንዲፈቱ የጋራና የተቀናጀ ጥረት የሚደረግ መሆኑ ተገልጿል።
ያግኙን
☏046-777-1536
ተዛማጅ ሊንኮች
Copyright © 2021-2025 Gofa Zone Adminstration.All Rights Reserved
Gofa,Ethiopia