የጎፋ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ የ2014 በጀት ዓመት አፈፃፀም ግምገማ፣ የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ እና የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ ዙሪያ ሴክቶሪ
የጎፋ ዞን መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
ቀን 2022-11-15
የጎፋ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ "የላቀ ትራንስፖርት አገልግሎትና የመንገድ ተደራሽነት ለብልጽግና ጉዟችን" በሚል መሪ ቃል የ2014 በጀት ዓመት አፈፃፀም ግምገማ፣ የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ እና የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ ዙሪያ ሁሉም ባለድርሻ አካላትና ተጠሪ ተቋማት በተገኙበት ሴክቶሪያል ጉባኤ እያካሄደ ይገኛል። የመምሪያው ኃላፊ አቶ ጃኬቴ ዛይሴ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ለአንድ ሀገር ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ እድገት ላይ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ እንደመሆኑ መጠን ተቋሙ የትራንስፖርት ዘርፉን ቀልጣፋ፣ ፍትሐዊና ለተገልጋዩ ሕብረተሰብ ተደራሽ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ ኦየሰራ ይገኛል ብለዋል። በዞኑ የመልካም አስተዳደር ችግር ሆኖ የቆየውን የትራንስፖርት ታሪፍን ለማሻሻል ባለድርሻ አካላት በማሳተፍና ጥናት በማድረግ ሕጋዊ የታሪፍ ማሻሻያ በማድረግ በዘርፉ የሚስተዋለው ችግር መፈታቱን ተናግረዋል። የጎፋ ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አብርሃም ዞራ የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት በትራንስፖርትና መንገድ ልማት ዘርፍ ለሕብረተሰቡ የሚሰጡ አገልግሎቶችንና የመሠረተ ልማት ግንባታዎችን አቀናጅቶ በመምራት ፍትሐዊ፣ ሕጋዊና ደህንነቱ የተጠበቀ ፈጣንና ዘላቂ የትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል የዞኑ መንግሥት በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን ተናግረዋል። አቶ አብርሃም አያይዘውም መንገድ ከመሠረተ ልማት አውታሮች አንዱና ዋነኛው መሆኑን ገልጸው፣ በገጠር ተደራሽ መንገድ በዩራፕ ፕሮግራምና በመደበኛ መንገድ ፕሮግራም የመንገድ መሠረተ ልማት ግንባታን ተደራሽ ለማድረግ ጥረት እየተደረገና ውጤት እየተገኘበት ይገኛል ብለዋል። በጉባኤው የዞኑ የመንግሥት ረዳት ተጠሪና የርዕዮተ ዓለም ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጳውሎስ ፋይሌ፣ የዞኑ ካቢኔ አባላት፣ የወረዳ ዋና አስተዳዳሪዎች፣ የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎችና የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች፣ የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችና የማኔጅመንት አካላትና ሌሎች ባለድርሻ አካላትም ተሳታፊ ሆነዋል።
የጎፋ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ "የንግድና ገበያ ሥርዓትን በማዘመንና ፍትሐዊ በማድረግ የሸማቹን ማህበረሰብ ተጠቃሚነት እናረጋግጣለን" በሚል መሪ ቃል
የጎፋ ዞን መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
ቀን 2022-11-07
የጎፋ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ "የንግድና ገበያ ሥርዓትን በማዘመንና ፍትሐዊ በማድረግ የሸማቹን ማህበረሰብ ተጠቃሚነት እናረጋግጣለን" በሚል መሪ ቃል የ2014 አፈፃፀም፣ የ2015 ዕቅድ እንዲሁም የ2015 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት ክንውን ሪፖርት እንዲሁም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ የሚያስቀምጥ ዞናዊ ሴክቶሪያል ጉባኤ እያካሄደ ይገኛል። የመምሪያው ኃላፊ ወ/ሮ ትዝታ አብርሃም የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት በሀገራችን የመጣውን ሠላም አስጠብቀን እንደ ሀገር ብሎም እንደ ዞናችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየናሬ የመጣውን የኑሮ ውድነት የምናረጋግጥበትን ሁኔታ በመፍጠር ሕዝባችን በምግብ ራሱን እንዲችል የጀመርነውን የልማት ፕሮግራም አጠናክረን ማስቀጠል ይኖርብናል ሲሉ ገልጸዋል። በተጠናቀቀውና በ2015 በጀት ዓመት በርካታ ተግባራት በተቋም ደረጃ መከናወኑን የገለጹት ወ/ሮ ትዝታ አብርሃም፣ በተለይም የንግድ ምዝገባ ፈቃድና መረጃ አገልግሎት ለማዘመን ታቅዶ በሰባት መዋቅሮች ተግባራዊ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል። በ2014 በጀት ዓመት የኢንስፔክሽን ሥራዎችን በማጠናከር በሕገወጥ መንገድ ስንቀሳቀስ ከተያዙ ምርቶች እንዲሁም ከንግድ ሥራ ፈቃድ እድሳት ቅጣት በድምሩ ከ206 ሺህ ብር በላይ ለመንግሥት ገቢ መደረጉን ገልጸዋል። በሰብልና ግብይት ኤክስፖርት ዘርፍ ለማዕከላዊ ገበያ የተላከ ማሾ 522.7 ቶን፣ ሰሊጥ 1214 ቶን እና ቀይ ቦሎቄ 261 ቶን በማቅረብ 2 ሚሊዮን 744 ሺህ 361.36 ብር ገቢ ማግኘት መቻሉንም የመምሪያው ኃላፊ አስታውቀዋል። በተመሳሳይ በቁም እንስሳትና ግብይት ዘርፍ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ የቀረበ ዳልጋ በግና ፍየል በቁጥር ከ 117,000 ሺህ በላይ መሆኑን የገለጹት ወ/ሮ ትዝታ፣ ከዚህም 8 ሚሊዮን 611 ሺህ 075 ገቢ መገኘቱን ተናግረዋል። የጎፋ ዞን የመንግሥት ረዳት ተጠሪ አቶ ጳውሎስ ፋይሌ በበኩላቸው የንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ተልዕኮው ዘመናዊ የንግድ ሥርዓት በመዘርጋት ጤናማ የሆነ የንግድ ውድድር እንዲኖርና ዜጎችን ከአላስፈላጊ ብዝበዛ በመከላከል ኢኮኖሚው እንዲቋቋም የንግዱ ማህበረሰብ የሚጫወተውን ሚና ለማሳደግ ከፍተኛ ኃላፊነት የተሰጠው ተቋም መሆኑን ተናግረዋል። ይህ ተቋም ከፌዴራል እስከ እያንዳንዱ ወረዳና ከተማ አስተዳደር የተደራጀ የመንግሥት መዋቅር ሲሆን፣ በየደረጃው ያለው የሕብረተሰብ ክፍል ከንግዱ ክፍሌ ኢኮኖሚ ማግኘት ያለበትን አገልግሎት በተሳለጠ ሁኔታ እንዲያገኝ እያደረገ ይገኛል ብለዋል። ዘመናዊ የንግድ ሥርዓት እንድኖር ሁሉም በንግዱ የተሰማሩ አካላት ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ እንዲኖራቸው ማድረግ ሚና አለው ያሉት አቶ ጳውሎስ፣ ይህን ለማረጋገጥ በየዓመቱ በንቅናቄ የሚሰሩ ሥራዎች ውጤት እያመጡ መሆናቸውንም ተናግረዋል። በጉባኤው የጎፋ ዞን ሕዝብ ምክር የኢኮኖሚ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ዓለምገነት ላቀውን ጨምሮ የወረዳ ዋና አስተዳዳሪዎች፣ የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎችና የብልጽግና ፓርቲ ኃላፊዎች፣ የንግድና ገበያ ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች፣ የሥራ ሂደት አስተባባሪዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላትም ተሳትፈውበታል።
በገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ዘርፍ ላይ ጥሩ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች ዕውቅናና ሽልማት ተሰጠ፡፡
የግብርና ሚኒስቴር
ቀን 2022-11-06
በአለም ባንክ በሚደገፈው የአየር ንብረትና የመሬት አያያዝ ፕሮግራም (Climate Action Through Landscape Management Program) ትግበራ በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በደቡብ ክልሎች እውቅና የተሰጣቸው ከክልል እስከ ወረዳ ጥሩ አፈፃፀም ላመጡ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም በፌደራል ደረጃ ደግሞ በግብርና ሚኒስቴር በተለያዩ መልክ ለፕሮግራሙ ድጋፍ እያደረጉ ያሉ ባለሙያዎች ናቸው፡፡ በግብርና ሚኒስቴር የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም መሪ ስራ አስፈፃሚ ትዕግስቱ ገ/መስቀል መድረኩን ሲከፍቱ በሶስቱም ክልሎች የሁለት ዓመት ተኩል በመሬት አጠቃቀምና አስተዳደር ዙሪያ የተሰሩ ስራዎች ላይ ማብራሪያ አቅርበዋል፡፡ በግብርና ሚኒስቴር የተፈጥሮ ሃብት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ፕ/ር እያሱ ኤልያስ በአሁን ሰዓት በፌደራል መንግስት ደግሞ የ2ኛ ደረጃ የመሬት ልኬት፣ ምዝገባና ሰርተፊኬሽን ስርዓት መዘርጋቱ የመሬት ባለይዞታው የመሬት ባለቤትነትን እና ግብርናውን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋዖ እንዳለው ዕውቅናና ሽልማት በተሰጠበት ወቅት ተናግረዋል፡፡ ሚኒስትር ዴኤታው የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ስርዓቱን ለማሳደግ በተለያዩ መልኩ ስራውን ሲደግፉ የነበሩ የመሬት አስተዳደር ሃላፊዎችና ባለሙያዎችን እንዲሁም ዘርፉን እየደገፉ ያሉ አካላትን በተለይም የአለም ባንክ እና የዕውቅና ፕሮግራሙ እንዲሳካ ድጋፍ ያደረገውን የጀርመን ተራድዖ ድርጅት (GIZ) አመስግነዋል፡፡
ያግኙን
☏046-777-1536
ተዛማጅ ሊንኮች
Copyright © 2021-2025 Gofa Zone Adminstration.All Rights Reserved
Gofa,Ethiopia