የጎፋ ዞን ሕዝብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር መርሃግብር 9ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ የቋሚ ኮሚቴዎችን ሹመት በማፅደቅ ተጠናቀቀ።
የጎፋ ዞን መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
ቀን 2022-04-08
ለፉት 2 ቀናት ሲካሄድ የቆየው የጎፋ ዞን ሕዝብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር መርሃግብር 9ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ የቋሚ ኮሚቴ ሹመት በማፅደቅ በዛሬው ዕለት ተጠናቀቀ። በዚህም መሠረት የጎፋ ዞን ህዝብ ምክር ቤት ህግ ፍትህ እና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ በመሆን የተሾሙት 1. የተከበሩ አቶ ቦረና ቦኖ --- ሰብሳቢ 2. የተከበሩ አቶ ዘለቀ ዶሳ 3. የተከበሩ ወ/ሮ ሃና ጋንቲሶ 4. የተከበሩ ወ/ሮ መኪያ እንዲሪስ 5. የተከበሩ አቶ ልዑል ሰገድ ገመዳ የኢኮኖሚ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ በመሆን የተሾሙት 1. የተከበሩ ወ/ሮ አለምገነት ላቀው --- ሰብሳቢ 2. የተከበሩ አቶ ገብረመድህን ጫመኖ 3. የተከበሩ ወ/ሮ እመቤት በዛብህ 4. የተከበሩ አቶ ግርማ ዋሼ 5. የተከበሩ አቶ እድሬ እርኮ በሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ በመሆን የተሾሙት 1. የተከበሩ ወ/ሮ ሃብታምነሽ ግራአዝማች --- ሰብሳቢ 2. የተከበሩ አቶ ታምራት ተሰማ 3. የተከበሩ አቶ በላይነህ ባህሩ 4. የተከበሩ ወ/ሮ ጊስታኔ ግርማ 5. የተከበሩ ወ/ሮ አማረች በየነ በመሆን የተሾሙ ሲሆን የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች ቃለ-መሐላ ፈፅመዋል።
የጎፋ ዞን ህዝብ ምክር ቤት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ም/ ፕሬዚዳንት ሹመት እና የከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ፕሬዚደንቶች ሹመት አፀድቋል።
የጎፋ ዞን መ/ ኮሙኒኬሽን
ቀን 2022-04-08
በዚሁ መሠረት :- 1. አቶ ፀጋዬ ፅጌ ዳዲኖ የጎፋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዚዳንት 2. አቶ አንድሰው አጋ ሌፎ የላሃ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት 3. አቶ ምትኩ ጌታቸው ወርቁ የበቶ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት 4. አቶ ሰብስቤ ዛውካ ዘርይሁን ለዑባ ደ/ ፀሃይ ወረዳ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት በመሆን ተሹመዋል።
የጎፋ ዞን ህዝብ ምክር ቤት የተለያዩ የካብኔ ሹመቶችን አፀደቀ
የጎፋ ዞን መ/ ኮሙኒኬሽን
ቀን 2022-04-08
4ኛ ዙር መርሃ-ግብር 9ኛ ዓመት ዘመን 4ኛ መደበኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ የሚገኘው የጎፋ ዞን ህዝብ ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን አፀደቀ። በዚሁ መሰረት፡- 1. አቶ ግርማ ዋሼ :- የጎፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ 2. አቶ ተክለማርያም በቀሌ :- ፕላንና ኢኮኖሚ መምሪያ ኃላፊ 3.አቶ ድንበሩ ደርቤ :- የጎፋ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ 4. አቶ ካሣሁን አባይነህ :- የጎፋ ዞን መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዩች መምሪያ ኃላፊ 5. አቶ ሞገስ መኩሪያ :- የጎፋ ዞን ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት መምሪያ ኃላፊ 6. አቶ ዳንኤል ደግፌ :- የጎፋ ዞን ሳይንስና ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ በመሆን ተሹመዋል ተሿሚዎቹ ከወረዳ ጀምሮ በተለያዩ የስራ ኃላፊነቶች ላይ የሰሩና ልምድ ያካበቱ መሆናቸው ተገልጿል።
ያግኙን
☏046-777-1536
ተዛማጅ ሊንኮች
Copyright © 2021-2025 Gofa Zone Adminstration.All Rights Reserved
Gofa,Ethiopia