በጎፋ ዞን በደምባ ወረዳ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ሆኖ የቆየው የሎጤ ቶዣ-ውርጪ ላይማ- ፃንጋ ደራራ 21 ኪ.ሜ የመንገድ ግንባታ ሥራ በይፋ ተጀመረ
የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
ቀን 2022-01-13
የክልል፣ የዞን እና የወረዳ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ሉዑካን ቡድን አባላት በተገኙበት በጎፋ ዞን ደምባ ጎፋ ወረዳ የሎጤ ቶዣ-ውርጪ ላይማ- ፃንጋ ደራራ 21 ኪ.ሜ የመንገድ ግንባታ ሥራ በይፋ ተጀምሯል። የደቡብ ክልል ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር አክሊሉ አዳኝ፣ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈሪ አባተ፣ የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር ጌትነት በጋሻው፣ የዞኑ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ማሩፋ መኩሪያ እና የደምባ ጎፋ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አንዳርጌ አራታ ተገኝተው የመንገዱን ግንባታ ሥራ በይፋ አስጀምረዋል። የጎፋ ዞን ዋና አስተዳደሪ ዶክተር ጌትነት በጋሻው በአጠቃላይ በዞኑ ከመንገድ ጋር ተያይዞ ጥያቄ ከሚነሳባቸው መዋቅሮች መካከል አንዱ የደምባ ጎፋ ወረዳ የሎጤ ቶዣ-ውርጪ ላይማ- ፃንጋ ደራራ መንገድ መሆኑን ገልጸዋል። ዋና አስተዳዳሪው አክለውም የመንገዱ ግንባታ ሲጠናቀቅ የአካባቢውን ማህበረሰብ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊና በፖለቲካዊ ዘርፎች ተጠቃሚ እንደሚያደርጋቸውም ተናግረዋል። የደምባ ጎፋ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አንዳርጌ አራታ እንደገለጹት፣ በወረዳው የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ሆኖ ከቆዩ መንገዶች መካከል አንዱ የሎጤ ቶዣ-ውርጪ ላይማ- ፃንጋ ደራራ መንገድ መሆኑን ተናግረዋል። ይህ መንገድ ለአካባቢው አርሶአደሮች፣ ለነጋዴው ማህበረሰብ፣ ለጤናና ትምህርት ተቋማት ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዳለው በመጠቆም፣ ለአካባቢው ነዋሪዎች እንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። የመንገዱ ግንባታ በክልሉ መንገዶች ባለስልጣን እንደሚሰራም የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ጠቁመዋል። ያነጋገርናቸው የአካባቢ ነዋሪዎች የመንገዱ ያለመሰራት በተለያዩ ዘርፎች ተጠቃሚ እንዳይሆኑ ማድረጉን በመጠቆም፣ መንግሥት በሰጣቸው ምላሽ መደሰታቸውን ተናግረዋል። የመንገዱ ግንባታ እስኪጠናቀቅ ድረስ አስፈላጊውን ተሳትፎ እንደሚያደርጉም ነው ነዋሪዎቹ የገለጹት። በመጨረሻም ሉዑካን ቡድኑ በወረዳው የቶዣ ሲቤ ቀለቤ ችግኝ ጣቢያ ሰርቶ ማሳያ የበጋ መስኖ ስንዴ ማሳ ጉብኝት አድርገዋል።
የጎፋ ዞን አስተዳደር አመራሮች ቀደም ሲል ዞኑን ላገለገሉ አመራሮች የሽኝት ፕሮግራም ማካሄዳቸው ተገለጸ
የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
ቀን 2022-01-11
ጥር 7/2014 ዓ.ም ሣውላ፡ የጎፋ ዞን አስተዳደር የዞን አመራሮች የሽኝት ፕሮግራም በዛሬው ዕለት ያካሄዱ ሲሆን የቀድሞው የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ለነበሩት ለአቶ መስፍን ስለሺ፣ የቀድሞው የዞኑ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ለነበሩት ለአቶ ጋሽያለው ጋላ እና ለቀድሞው የከተማ ልማት መምሪያ ኃላፊ ለነበሩት ለአቶ ካሳሁን ሰለሞን የዞኑ አጠቃላይ አመራሮች በተገኙበት የምስጋናና የሽኝት ፕሮግራም ተካሄዷል። አመራሮቹ ፓርቲ የተሻለ ኃላፊነትና ስምሪት ተሰጥቷቸው እንዲሁም በቤተሰብ ችግር ምክንያት የተሸኙ ሲሆን አቶ መስፍን ስለሺ በአመራርነት ወደ ደቡብ ክልል፣ አቶ ጋሽያለው ጋላ የፌዴራል ህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባል እንዲሆኑ በህብ በመመረጣቸው እና አቶ ካሳሁን ሰለሞን በቤተሰብ ምክንያት ወደ አዲስአበባ በመዛወራቸው ነው። ቀደሚሰል በዞኑ በነበራቸው የአመራርነት አበርክቶ እና አስተዋጽኦ እውቅናና ምስጋና የተቸራቸው ሲሆን ለሦስቱም የቀድሞው የዞኑ አመራሮች የወርቅ የአንገት ሀብል የስጦታ ተበርክቶላቸዋል። በሄዱበት መልካሙን ሁሉ እንዲገጥማቸው የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ጌትነት በጋሻው እና የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ማሩፋ መኩሪያ አጠቃላይ አመራሩን በመወከል የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፈዋል። በመጨረሻም አመራሮቹ በሄዱበት ሁሉ ለዞኑ ህዝብ ተጠቃሚነት እና ዕድገት መስራት እንደሚጠበቅባቸው ትልቅ ኃላፊነት እና ሀደራ የተሰጣቸው ሲሆን በሄዱበት ሁሉ አሁን ያለውን የዞኑን አመራር በሀሳብ እንዲደግፉ በድጋሜ ሀደራ ተጥሎባቸዋል።
በሣውላ ከተማ የጥምቀት በዓልን ያለምንም የፀጥታ ስጋት ለማክበር እየተሠራ መሆኑ ተገለፀ።
አቶ አለሙ አረጋ
ቀን 2022-01-17
በሣውላ ከተማ አስተዳደር የጥምቀት በዓልን ያለምንም የፀጥታ ሥጋት ለማክበር ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ የሣውላ ከተማ ሠላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለሙ አረጋ ጠይቀዋል። የሣውላ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ታረቀኝ አጥናፉ በበኩሉ ይህንን ታላቅ ህዝባዊና ኃይማኖታዊ በዓል ካለምንም የፀጥታ ችግር ተከብሮ እንዲያልፍ የፀጥታ አካላት ከምንም ጊዜ በላይ ዝግጁ እንዲሆኑ ገልጿል። በውይይቱ የከተማው ፓሊስ ፤ ሚሊሻ ፤ ተቀናናሽ ሠራዊት አባላት እና ህዝባዊ ሠራዊት አባላት ተገኝተዋል በውይይቱ ተሳታፊ የፀጥታ ኃይሎች አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዳጠናቀቁና የከተራው ቀንና የጥምቀቱን ቀን ያለምንም የፀጥታ ስጋት ለማሳለፍ መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል።
ያግኙን
☏046-777-1536
ተዛማጅ ሊንኮች
Copyright © 2021-2025 Gofa Zone Adminstration.All Rights Reserved
Gofa,Ethiopia