የፍትህ አሰጣጡን ቀልጣፋና ዘመናዊ ከማድረግ አኳያ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን የጎፋ ዞን ፍትህ መምሪያ ገለጸ
የጎፋ ዞን መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
ቀን 2022-11-17
መምሪያውን የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ ክንውን ዙሪያ ከባለድረሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል። የዞኑ ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደመላሽ ብላቴ በሩብ ዓመቱ የታዩ ጉድለቶችን ለማረም እየተሠራ በመሆኑ በተለይም ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ ከመስራት አኳያ የታየው ክፍተት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት የሚሰራ ተግባር ነው ብለዋል። የፍትህ መምሪያው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀረቦ በተሳታፊዎችና ባለድርሻ አካላት ውይይት ተደርጎበታል። ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከል አቶ አንዱዓለም ጀማል፣ አቶ ዳግማዊ ዘሪሁን እና ዳዊት አፋሼ በጋራ እንደገለጹት የፍትህ አሰጣጡን ተደራሽ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ እንዲሁም ጥፋት የፈጸሙ ግለሰቦች አፋጣኝ የፍርድ ውሳኔ እንዲያገኙ ከማድረግ አኳያ በዐቃቤ ህግ በኩል መሻሻል መታየቱን አንስተዋል። በተለይ ሙስናና የረቀቁ የሌብነት ወንጀሎችን እልህ አስጨራሽ ትግል በማድረግ ተገቢውን የፍርድ ውሳኔ እንዲያገኙ እየተደረገ ያለው ጥረት የሚበረታታ ነው ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ ለቀጣይ ከሚመለከታቻው ጋር በመተባበር መሰል ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቁመዋል።
የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ በቢሾፍቱ ከተማ የሌማት ትሩፋትን አስጀመረ ።
የጎፋ ዞን መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
ቀን 2022-11-17
የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ሥራ አስፈጻሚ በቢሾፍቱ ከተማ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት "የተመጣጠነ ምግብ እመገባለሁ ሁሉንም በደጄ አመርታለሁ" በሚል መሪ ሀሳብ የሌማት ትሩፋት መርሀ ግብርን አስጀመረ። መርሀ ግበሩ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስትትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ የከተማና መሠረተ ልማት ሚንስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ፣ የብልጽግና ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነትና አለም አቀፍ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሳዳት ነሻ እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል። የሊጉ ፕሬዚዳንትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዓ ወይዘሮ ዛራ ሁመድ በምግብ ራስን በመቻል ድህነትን ታሪክ ለማድረግ ሁሉም የበኩሉን ጥረት እንዲያደርግ ጠይቀዋል። በምግብ ራስን ለመቻል በሚደረገው ጥረት ለከተማ ግብርና ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥ የተናገሩት ደግሞ የከተማና መሠረተ ልማት ሚንስትሯ ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ ናቸው። የከተማ ግብርና በቦታ ስፋትና ጥበት ሳይገደብ ውጤታማ መሆንን ከቢሾፍቱ ከተማ ልምድ መቅሰም ጠቃሚ መሆኑን አስገንዝበዋል። ከልማቱ ጎን ለጎን ለሰላማችን ተገቢው ትኩረት መሰጠት የሁሉም ኃላፊነት መሆኑን የጠቆሙት ደግሞ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጉዳይ ሚንስትሯ ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ናቸው። የግጭት ግንባር ቀደም ሰለባዎቹ ሴቶች፣ አቅመ ደካሞችና ሕጻናት ናቸው ብለዋል ሚኒስትሯ። ጠንካራ የሴቶች አደረጃጀቶች በመፍጠር ሴቶች በሰላምና በልማት ተጠቃሚ እዲሆኑ ሚንስቴር መሥሪያ ቤቱ የተለያየ እንቅስቃሴ ላይ መሆኑንም አመልክተዋል። በመርሀ ግብሩ በከተማ ግብርና ተሰማርተው ውጤታማ የሆኑ ሴቶች የልማት እንቅስቃሴዎቻቸው ተጎብኝቷል። በሰላም ማስከበሩ ሂደት የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱት ሴቶች እውቅናና ሽማት እንደሚሰጥም ይጠበቃል።
ልማታዊና ዲሞክራሲያዊ ፖለቲካል ኢኮኖሚ ለመፍጠር የምክር ቤቶች ሚና የጎላ መሆኑ ተገለጸ
የጎፋ ዞን መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
ቀን 2022-11-17
የደቡብ ክልል ምክር ቤት ከክልሉ አመራሮች፣ የዞን ፣ የወረዳ አፈ_ጉባኤ ጋር በጋራ በወላይታ ሶዶ አየመከሩ ነው። በዚሁ ወቅት የደቡብ ክልል አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ሰርሞሎ እንደተናገሩት የክልላችን ምክር ቤት የሕዝብ ሉዐላዊነት መገለጫ የዲሞክራሲ የዜጎች ስርዓት መጎልበቻና የልማትና የመልካም አስተዳደር ተጠቃሚነትን ማሳያ ተቋም መሆኑን ገልፀዋል። ኃላፊዋ አክለውም ምክር ቤቶች የሕግ የበላይነት እንዲሰፍን ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ ዕድገቶች እንዲፋጠኑና የዜጎች ብልፅግና እንዲረጋገጥ ወደር የለሽ አስተዋፅኦ እያበረከቱ ይገኛሉ። ወ/ሮ ፋጤ አያይዘውም ለዘላቂ ሰላም መንግስታችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ማቋቋሙ ይታወቃል በመሆኑም የታለመው ዓላማ ከግብ ለማድረስ በወሳኝ ጉዳዮች ሀገራዊ መግባባት አስኪፈጠር ድረስ በየደረጃው ያሉ ምክር ቤቶች የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል። በመጨረሻም 6ኛው ዙር የስራ ዘመን የጋራ የምክክር ፎረም በይፋ መከፈቱን አበስረዋል። የወላይታ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። የምክክር መድረኩ ለሁለት ቀን እንደሚቆይም ተጠቁሟል።
ያግኙን
☏046-777-1536
ተዛማጅ ሊንኮች
Copyright © 2021-2025 Gofa Zone Adminstration.All Rights Reserved
Gofa,Ethiopia