የበልግ ግብርና ቀሪ ስራዎችን በትኩረት በመምራት የግብርና ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑን የጎፋ ዞን ግብርና መምሪያ ገለፀ
የጎፋ ዞን መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
ቀን 2022-04-18
የጎፋ ዞን ግብርና መምሪያ የ 90 ቀን እቅድ እና የበልግ አፈፃፀም ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያደረገ ይገኛል። የጎፋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አብረሃም ዞራ በውይይት መድረኩ እንደገለፁት ከህዝብ የተነሱ ጥያቄዎች ለመፍታትና የተረጋጋ ገበያ ለመፍጠር ተጨባጭ የግብርና ተግባራት በዞናችን በጊዜ ገደብ ተገድቦና በተጠያቂነት መንፈስ እየተፈጸመ ይገኛል ብለዋል። በውይይቱ የሁሉም መዋቅሮች የበልግ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ በጥንካሬ እና በድክመት በተለዩ ጉዳዮች ላይ በጥልቀት በመወያየት የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ላይ መክረዋል። በዋናነት በውይይቱ ከተነሱ ሀሳቦች የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ፣ በከተማ ግብርና ሥራዎች ፣ የአፈርና የውሃ ጥበቃ ሥራዎች ፣ የእንሰሳትና ዓሣ ሀብት ተግባራት ፣ በቡናና ቅመማ ቅመም ምርት የተሠሩ ተግባራትና በሌሎች የግብርና ተግባራት ላይ በጥልቀት ተወያይተዋል። በተጨማሪም በዶሮ ሀብት ልማት ያሉ ምርጥ ተሞክሮዎችን ለማስፋትና የነበሩ ማነቆዎች የሚፈቱበት መንገድ ላይ በመወያየት ዶሮና የዶሮ ውጤቶች በማሳደግ የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጥቅሞችን ከፍ ለማድረግ የ 5_10_25 የዶሮ ልማት ፕሮጀክት ውጤታማ ለማድረግ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ በውይይቱ ተጠቁሟል። በመጨረሻም በቀሪ 3 ወራት በጥራት እና በጊዜ የለንም ስሜት በመታገል ከህዝቡ የሚነሱ መሰረታዊ የኑሮ ጥያቄዎችን እና መሬት ላይ ያሉ ተጨባጭ ችግሮችን በትግል መፍታት መፍታት የሚያስችል የ 90 ቀናት እቅድ መዘገጀቱና ወደ ተግባር ምዕራፍ መሻገራቸውን አቶ አብረሃም ዞራ ገልፀዋል።
በጦርነትና ግጭት ውስጥ ሆነው የተፈተኑና የማለፊያ ነጥብ ያላመጡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከ2014 ዓ.ም መደበኛ ተፈታኞች ጋር እንዲፈተኑ ውሳኔ ተላለፈ።
የጎፋ ዞን መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
ቀን 2022-04-18
ትምህርት ሚኒስቴር ከክልል እና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች ጋር ተከታታይ ውይይት በማድረግ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል። በመግለጫው የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና እርማት በተመለከተ ያጋጠመ ችግር አለመኖሩን ሚኒስቴሩ አስታውቋል። በአብዛኞቹ ክልሎች ያጋጠመ የውጤት መቀነስ መኖሩን እና ትምህርት ሚኒስቴር አማራጮችን የማየት ስራ መስራቱንም በመግለጫው ተነስቷል። በዚህም በጦርነትና ግጭት ውስጥ ሆነው የተፈተኑ አካባቢዎች እና የማለፊያ ነጥብ ያላመጡና ወደ መንግስት ዩኒቨርስቲ መግባት ያልቻሉ ተማሪዎች በ2014ዓ.ም በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና እንደ መደበኛ ተማሪ እንዲፈተኑ ውሳኔ ተላልፏል። ከዩኒቨርስቲዎች ጋር ውይይት በማድረግ ተጨማሪ የቅበላ አቅም እንዲኖር ከስምምነት ላይ መደረሱን እና ተጨማሪ የቅበላ አቅም በፍትሀዊነት በጦርነቱ ምክኒያት ለተጎዱ ክልሎችእንዲከፋፋል ውሳኔ ተላልፏል። የፈተና ውጤት ማሳወቅን በተመለከተም በሁለት ዙር ፈተና በመሰጠቱ አጋጥሞ የነበረው ችግር መታረሙ በመግለጫው ተገልጿል። በመጀመሪያው ዙር ተፈታኞች በስነ-ዜጋ ትምህርት ካጋጠመዉ ችግር ውጪ ሌሎች ችግሮች ባለማጋጠማቸው የሌሎች ትምህርት ዓይነቶችን ውጤት ውድቅ ለማድረግ አሳማኝ የውጤት ትንተና አለመኖሩም ነው የተገለፀው ። በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ቅበላ የሚያገኙትን በተመለከተ በቀደምት ዓመታት ከመሰናዶ ትምህርት በኋላ ከሚፈተኑ ጋር በማነፃፀር የተፈጠረ አለመረዳት መኖሩንም ሚኒስቴሩ ገልጿል። በቀጣይም እንደዚህ አይነት ችግሮች እንዳይፈጠሩ የተጠናከረ ስራ ለመስራት ከስምምነት ላይ መደረሱ ተገልጿል።
ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የማህበረሰቡን ችግር ሊፈቱ የሚችሉ የፈጠራ ሥራዎች ላይ ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ የጎፋ ዞን ቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ሥልጠና መምሪ
የጎፋ ዞን መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
ቀን 2022-04-15
የጎፋ ዞን ቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ሥልጠና መምሪያ የ2014 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ፣ የቀጣይ ወራት የትኩረት አቅጣጫዎች እንዲሁም አዲስ መደበኛ ሰልጣኞች ቅበላ የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል። በንቅናቄው መድረክ ላይ የሣውላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ግንዳ ባህሩን ጨምሮ የሁሉም ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ዲኖች እና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትም ተሳትፈውበታል። አዲስ ሰልጣኞች ቅበላ ቅድመ ዝግጅት፣ አጫጭር ገበያ ተኮር መስኮች ላይ ማሠልጠን፣ ስልጠናቸውን አጠናቅቀው የሚመረቁ ሰልጣኞችን ከስራ ጋር ማስተሳሰር፣ ሁሉም ኮሌጆች ስልጠናዎችን በተቀመጠላቸው ጊዜ በማጠናቀቅ ተማሪዎችን ማስመረቅ እንደሚገባቸው በውይይት መድረኩ ተገልጿል። የኮሌጆችን የውስጥ ገቢያቸውን በማሳደግ አቅምን ማጎልበት እና ኮሌጆች ስራዎቻቸውን በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች ማስተዋወቅ እና በሌሎች መስኮች ላይ ሁሉም ኮሌጆች የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ በማድረግ ሊሰሩ እንደሚገባቸውም ነው በሪፖርቱ የተገለጸው። የጎፋ ዞን ቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ሥልጠና መምሪያ ኃላፊ አቶ አብራሃም አልዬ እንደገለጹት፣ ሁሉም ኮሌጆች ከመማር ማስተማር ተግባራት በተጨማሪ የማህበረሰቡን ችግር ሊፈቱ የሚችሉ የፈጠራ ሥራዎች ላይ ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ ገልጸዋል። ሁሉም ኮሌጆች የተቋሙን ራዕይ እውን ለማድረግ እንዲሁም ተልኮውን ለማሳካት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተው በመስራት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ የመምሪያው ኃላፊ አቶ አብራሃም አልዬ ተናግረዋል። የውይይቱ ተሳታፊ የነበሩ ባለድርሻ አካላት በበኩላቸው ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የተጣለባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ እንዲሁም ራዕያቸው እውን እንዲሆን ከኮሌጆች ጋር በቅንጅት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
ያግኙን
☏046-777-1536
ተዛማጅ ሊንኮች
Copyright © 2021-2025 Gofa Zone Adminstration.All Rights Reserved
Gofa,Ethiopia