የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው እና የደቡብ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ከበደ በሀላባ ዞን የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት አስጀ
የጎፋ ዞን መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
ቀን 2022-11-22
የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው፣ የደቡብ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ከበደ፣የክልል እና የዞን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ስራ የተጀመረው። በክልሉ ባለፈው ዓመት 5ሺ 191 ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ ስንዴ በማልማት ከ152ሺ ኩንታል በላይ ምርት መገኘቱን ከክልሉ ግብርና ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በተያዘው በጀት ዓመት 862 ሚሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱን የጎፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ አስታወቀ
የጎፋ ዞን መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
ቀን 2022-11-18
የጎፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ "የአፈፃፀም ክፍተቶቻችንን በማስወገድ ለዞኑ ልማት አስተማማኝ ገቢ እንሰበስባለን"! በሚል መሪ ቃል የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ፣ የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ እና የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ እያካሄደ ይገኛል። የመምሪያው ኃላፊ ወ/ሮ ጥሩነሽ ወዛ ባስተላለፉት መልዕክት በ2014 በጀት ዓመት መደበኛና ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ገቢ 528 ሚሊዮን 342 ሺህ 141 ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 543 ሚሊዮን 488 ሺህ 684.28 ብር መሰብሰብ መቻሉን ተናግረዋል። የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ ለማሳካት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር የነበረው ቅንጅታዊ አሠራር ለዕቅድ መሳካት አበርክቷል ብለዋል። በ2015 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት 215 ሚሊዮን 500 ሺህ ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 163 ሚሊዮን 790 ሺህ 866.91 ብር ገቢ መሰብሰብ መቻሉን አክለዋል። በተያዘው በጀት ዓመት 862 ሚሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱን የገለጹት ወ/ሮ ጥሩነሽ፣ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቁርጠኝነት ወደ ተግባር መግባት ይጠበቅብናል ሲሉ አሳስበዋል። የጎፋ ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አብርሃም ዞራ የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት ባለፉት ዓመታት የዞናችን ኢኮኖሚ ከሚያመነጨው ሀብት ሊገኝ የሚችለውን ገቢ አሟጦ ለመሰብሰብ የሚያስችሉ ተግባራትን ለመፈጸም የሚያስችሉ ሥራዎችን በማከናወን ሰፊ ትኩረት ተሰጥቶ ሲሰራ መቆየቱንም ተናግረዋል። በተጠናቀቀው ዓመት ከዕቅድ በላይ ማሳካት መቻሉን የገለጹት አቶ አብርሃም፣ ለውጤታማነቱ በየደረጃዉ የሚገኙ መዋቅራችን አመራሮችና ባለሞያዎች ጉልህ ሚና መጫወታቸውን ተናግረዋል። የአካባቢው ኢኮኖሚ ከሚያመነጨው ሀብት የሚገኘውን ገቢ አሟጦ በመሰብሰብ ከህዝቡ የሚነሱ የመሠረተ ልማት ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ ምላሽ በመስጠት ተጠቃሚ ማድረግ የግድ የሚል ነው ብለዋል። በምክክር መድረኩ የጎፋ ዞን የመንግሥት ረዳት ተጠሪና የርዕዮተ ዓለም ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጳውሎስ ፋይሌ፣ የመምሪያ ኃላፊዎች፣ የወረዳ ዋና አስተዳዳሪዎች፣ የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎችና የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች፣ የሁሉም ገቢዎች ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችን ጨምሮ የማኔጅመንት አካላት እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላትም ተሳታፊ ሆነዋል።
በዞኑ የመንገድ ተደራሽነት ሽፋንን ለማሳደግ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በጋራ ሊረባረቡ እንደሚገባ ተገለጸ
የጎፋ ዞን መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
ቀን 2022-11-17
የጎፋ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ "የላቀ ትራንስፖርት አገልግሎትና የመንገድ ተደራሽነት ለብልጽግና ጉዟችን" በሚል መሪ ቃል የ2014 በጀት ዓመት አፈፃፀም ግምገማ፣ የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ እና የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ ዙሪያ ሁሉም ባለድርሻ አካላትና ተጠሪ ተቋማት በተገኙበት ሲያካሂድ የነበረው ሴክቶሪያል ጉባኤ ተጠናቋል። የጉባኤው ተሳታፊ የነበሩ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በአንዳንድ መዋቅሮች የተጀመሩ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች በተለያዩ ምክንያቶች በተያዘላቸው ጊዜ ባለመጠናቀቃቸው የተነሳ በህብረተሰቡ ዘንድ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ እየፈጠሩ መምጣቸውን ገልጸዋል። የጎፋ ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አብርሃም ዞራ በሰጡት ምላሽ እንደ ዞናችን የመንገድ መሠረተ ልማት ሽፋን ዝቅተኛ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የሆነ የሕዝብ የመልማትና ፍላጎትና ጥያቄ ያለበት በመሆኑ የህዝቡን የመልማት ጥያቄ ለመመለስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በጋራ ሊረባረቡ ይገባል ሲሉ ገልጸዋል። አቶ አብረሃም አክለውም የመንገድ መሠረተ ልማት ሥራ ከፍተኛ በጀት የሚጠይቅ በመሆኑ ፣ በመንግሥት ወጪና ሕብረተሰቡን በማሳተፍ የሚፈፀም ተግባር ሊሆን እንደሚገባ ተናግረዋል። የመምሪያው ኃላፊ አቶ ጃኬቴ ዛይሴ በበኩሉ በየመዋቅሩ በትራንስፖርትና መንገድ ልማት ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታትና ሕዝቡ ለሚያነሳቸው ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በትራንስፖርትና መንገድ ልማት ዘርፍ በ2014 በጀት የላቀ አፈፃፀም ያስመዘገቡና ፊት የወጡ መዋቅሮች፣ ማህበራትና የሥራ ሂደቶች የእውቅናና ምስጋና ሰርቲፍኬት ተበርክቶላቸዋል። በዚሁ መሠረት በትራንስፖርት ልማት ዘርፍ የሣውላ ከተማ አስተዳደር፣ መሎ ላሃ፤ የቡልቂ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤቶች መናኸሪያ በማልማት፣ በክትትል፣ ቁጥጥርና ቅንጅታዊ ሥራ እንዲሁም ሌሎች የትራፊክ ፖሊስ መመሪያና ሕጎችን በማስከበርና የተጣለባቸውን ኃላፊነት በመወጣት የእውቅናና ምስጋና ሰርቲፍኬት ተበርክቶላቸዋል። በመንገድ ልማት ዘርፍ የመሎ ኮዛ፣ ዑባ ደብረ ፀሐይ እና ገዜ ጎፋ ወረዳዎች የተሻለ አፈፃፀም በማስመዝገብ የእውቅናና ምስጋና ሰርቲፍኬት ተሰጥቷቸዋል። የትራፊክ ሕጎችና ደንቦችን ተግባራዊ በማድረግ የሣውላ ከተማ አስተዳደር፣ የደምባ ጎፋ ወረዳ እና የቡልቂ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት የትራፊክ ቁጥጥር ዋና ሥራ ሂደት የእውቅናና ምስጋና ሰርቲፍኬት ተበርክቶላቸዋል። በተመሳሳይ የተጣለባቸው ሀገራዊ ኃላፊነት በታማኝነትና በቅንነት የተወጡ ማህበራት ማለትም ባራንቼ ደረጃ-2 እና ዱዛ ደረጃ-1 የሕዝብ ማመላለሻ ማህበራት እውቅና ተሰጥቷቸዋል። በመጨረሻም የመንገድ ሥራ ተቋራጭ ማህበራት ማለትም ሲና ኮንስትራክሽን ማህበር፣ ቢ ዋይ ዲ ማን ኮንስትራክሽን ማህበር እና ጂ ኤም ዋይ ኮንስትራክሽን ማህበር የእውቅናና ምስጋና ሰርቲፍኬት ተበርክቶላቸዋል።
ያግኙን
☏046-777-1536
ተዛማጅ ሊንኮች
Copyright © 2021-2025 Gofa Zone Adminstration.All Rights Reserved
Gofa,Ethiopia