የመጀመሪያ ወርቃ ካዎ አርሼ ከወርቅ የተሠራዉ ዘዉድ (ካላቻ)
ቀን 2021-12-14
የጎፋ የመጀመሪያዉ ወርቃ ካዎ የሚል ስም በማግኘት የንግሥና ስልጣነ መንበሩን በመያዝ፤ የጎፋን ግዛት ከወይዴ ዉርኪ እስከ አሪ ጎይቢ ድንበር ድረስ በማስፋፋት በገዜ ጎፋ ከንቾ በተባለ ሥፍራ ላይ የጎፋ የመጀመሪያዉ የወርቅ ንጉሥ ( ወርቃ ካዎ አርሼ ) የንጉሡን ቤተመንግሥት በመስራት የንግሥና ሥርዓቶችን በዚያዉ ቦታ እየተፈፀመ እንዲኖር በመወሰን፤ ከመጀመሪያዉ ወርቃ ካዎ አርሼ እስከ መጨረሻዉ ካዎ ሲንሳ ድረስ ይህ ሥርዓት በጎፋ እንደ ነበር የሀገር ሽማግሌዉ (አቶ ኡታ ዳፋርሻን) ይነግሩናል፡፡ ከመጀመሪያዉ ካዎ አርሼ ዘመን እስከ ካዎ ስንሳ ድረስ የነበሩ ካላቻዎች ዛሬም ድረስ በቅርስነት በሕዝብ ባለቤትነት በቀበሌ ደረጃ ተቀምጠዉ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ቅርሶች ከ 500 እስከ 1000 ዓመት እድሜ ያስቆጠሩ እንደሆኑ በቦታዉ ደርሰን በዓይናችን ተመልክተናል፡፡ ቅርሶች የአንድን ሕዝብ ታሪክ፤ የአኗኗር ዘይቤን እና የአስተዳደር ሥርዓትን ወደ ኃላ እንድንቃኝ ከማድረጋቸዉ ባለፈም፤ ቅርሱ የጎፋን የጥንት ጀግንነት እና የሕዝቡን ጥንካሬ ቁልጭ በማድረግ እንድንረዳ ያደርገናል፡፡ (ምንጭ፡-የገዜ ጎፋ ወረዳ ባ/ቱ/ስ/ጽ/ቤት፤ በኬንቾ ቀበሌ ቅርሱን ጠብቀዉ ያቆዩ አባት (አቶ ኡታ ዳፋርሻን) እና የዞን ባ/ቱ/ስ/መምሪያ ባለሙያ በዮሓንስ ኢትዮጵያ) ሕዳር 2013ዓ.ም.
ያግኙን
☏046-777-1536
ተዛማጅ ሊንኮች
Copyright © 2021-2025 Gofa Zone Adminstration.All Rights Reserved
Gofa,Ethiopia