ወርባ እንዲ ወምዖ / የተፈጥሮ ዋሻ/
ቀን 2021-09-09
በኦይዳ ወረዳ ከሸፊቴ ከተማ በ6ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚትገኘው ቃምኦ ሾምባ ቀበሌ ውስጥ ስሆን የሚታወቀው በዉስጥዋ ታሪካዊና ተፈጥሮአዊ መስህቦች በያዘቻቸው ውብና ድንቅ የተፈጥሮ ሀብቶች ነው፡፡ ይህች ቀበሌ ከያዛቻቸው በርካታ የቱሪስት መስህብ ከሆኑ ሀብቶች መካከል ወርባ እንድ ወምኦ ዋሻ አንዱ ነው፡፡ ይህ ዋሻ ወደ ዉስጥ ስገባስፋቱ በግምት 5.5m2 በላይ ስሆን ይህንን ዋሻ ታሪክ የሀገር ሽማግሌዎች ስናገሩ ቃላቱ የተዋቀረው ከሦስት ዋና ዋና ቃላት ስሆን ይኼውም 1. ወርባ፡- ነብር 2. እንዶ፡ስጠቃለል የነብር እናት ዋሻ ማለት ነው፡፡ 3. በጣሊያ በሌሎችም መሰል ውጊያ ጊዜ ለአከባቢው ህብረተሰብ መሸሸ ጊያ ሆኖ እንደገለገሌ እያስረዱ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በወጣቶች ና ሙሽረኞች /ጫጉላ/ መዝናኛ አገልግሎት እንደሚሰጥ - እናት 4. ወምዖ፡- ዋሻ የሀገሩ ሽማግሌዎች ያስረዳሉ፡፡
ቦምባር ዋሻና ፏፏቴ
ቀን 2021-09-07
ይህ ዋሻና ፏፏቴ የሚገኘዉ በኦይዳ ወረዳ ሻላ ባሪንዴ ቀበሌ ኮሶሎ ንዑስ የሚገኝ ስሆን ይህ ዋሻ ከዋናዉ ከተማ ማለትም ከሸፊቴ 28 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ዋሻዉ በጥንት ጊዜ ሰዎች በኢጣሊያን ወረራ ለመሸሸግ የሚጠቀሙበት እንደነበረ የዕድሜ ባለፀጋዎች በግምት እስከ 1000 ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል አደራሽ አለዉ፡፡ ዋሻዉ በአጣቃላይ 4 ክፍሎች ያለዉ ስሆን፡- 1. የባላባት ክፍል፡- የነበረ ስሆን ስፋቱ 4 ሜ ቁመት 4 ሜ እና ርዝመቱ 4 ሜ እንደሆነ ይገመታል፡፡ 2. የእናቶች ክፍል ቁመቱ 4 ሜ ስሆን ሥፋት 8 ሜ እና ርዝመቱ 6 ሜ ይኖረዋል፡፡ 3. የወንዶች ክፍል ስሆን ቁመት 4 ሜ ስፋቱ 15 ሜ ያለዉ ስሆን ርዝመቱ በዉል ልታወቅ አልተቻለም፡፡ዋሻዉ በዉስጡ ግርግዳዉም ሆነ ጣሪያዉ ድንጋይ ንጣፍ ያለዉና በዋሻዉ አናት ላይ ፏፏቴ ይገኛል፡፡ ይህ የፏፏቴ ርዝመት 80 ሜ ነዉ፡፡ 4. ከብቶች የሚኖሩበት ክፍል ስሆን የበሩ መግቢያ ቁመት 4 ሜ ስፋቱ 8 ሜ ርዝመቱ 10 ሜ ያህል ነዉ፡፡
የወምባ ፏፏቴና ዋሻ
ቀን 2021-09-04
ከደምባ ጐፋ ወረዳ ዋና ከተማ ሳውላ 12 ኪ.ሜ ወደ ምዕራብ ከተጓዙ ካርጮ ሜላ ቀበሌን ያገኛሉ፡፡ቀበሌው በውስጡ ለዘመናት ድንቅ ዉበቱን እና ታሪኩን ሸሽጎ የተቀመጠ መሆኑን ስመለከቱ ይገርሞታል፡፡ ዋሻና ፏፏቴን በአንድ አጣምሮ የያዘ ቀልብን የሚገዛ መስህብ ባለቤት ነው፡፡ካርጮ ሜላ ፡፡ካርጮ ሜላ ቀበሌውን ደርሰው ወደ ፏፏቴው መንገድ ሲያቀኑ ከሩቅ በአስገራሚ ድምጽ የወምባ ፏፏቴ የአንኳን ደህና መጡ መልእክቱን ያሰሞታል፡፡ ፏፏቴው ከሩቅ ሲታይ አረንጓዴ ተራራ ከቋጥኝ ጋር እየተለተመ በሚፈጥረው ግርማ ሞገስ ባለው ድምጽ እየተደመሙ ከ100 ሜትር በላይ ቁልቁል የሚወርደውን ሀጫ በረዶ የመሰለ ንጣቱን እያደነቁ ለተወሰነ ደቂቃዎች እጅዎን በአፍዎ ላይ ጭነው የፈጣሪን ተአምረኛ ሥራ ያደንቃሉ፡፡ በፏፏቴው መሣጭ ድባብ ውስጥ ሆነው በሀሴት ሲዋኙ በፏፏቴው መሃል ከ500 (አምስት መቶ) ሰው በላይ ማሰተናገድ የሚችል ዋሻ ብያገኙስ ምን ይሰሞታል? ዋሻው በቀኝና በግራ በኩል በትናንሽ ዋሻዎች የታጀበ ሲሆን በመሀል ያለው ትልቁ ዋሻ ስፋቱም ሆነ ርዝመቱ በቀላሉ የሚገመት አይደለም፡፡ ለምሳሌ ርዝመቱን ስንመለከት እዚው ሰዎች በጦርነት ጊዜ ተደብቆ ምግብ ስያበስሉ ያነደዱት ጪስ ብዙ ርቀት ከውስጥ ከሄደ በኋላ በአንኮ ሌፌ በሚባል ንዑስ ቀበሌ እንደሚወጣ የአከባቢ ነዋሪ የሆኑትና የእድሜ ባለጸጋ የሆኑት አዉዛንቶች ይናገራሉ፡፡ፏፏቴው የዋሻውን በር እንደ መጋረጃ ጋሪዶ እይታን ይማርካል፡፡ ታዲያ ይህንን የሚመስል መስህብ ከመስማት ያለፈ ደርሶ መመለከት ምነኛ የስደስታል ወደ ቦታው ካቀኑ በደስታ የተነከረውን የክብር ካባ አጥልቀው እንደምመለሱ ጥርጥር የለውም፡፡
ያግኙን
☏046-777-1536
ተዛማጅ ሊንኮች
Copyright © 2021-2025 Gofa Zone Adminstration.All Rights Reserved
Gofa,Ethiopia