ዣውሻ ተራራ ፡-
ቀን 2021-09-02
በኦይዳ ወረዳ ከሚገኙ ተፈጥሮአዊ የቱሪስት መስህቦች አንዱ ነው፡፡ ይህ ተራራ ከወረዳው ዋና ከተማ ሸፊቴ 4 ኪ/ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን 2500-3000 ሜትር ከባህር ጠለለ በላይ ከፍታ አለው፡፡ ከተራራው አናት ስወጡ መላው የከተማውን ክፍልና ሌሎች አከበቢዎችም ማየት ይቻላል፡፡ ከዚህም የተነሳ በአካባቢው ቋንቋ ሳዓ-ጉልኣ የሚል ስያሜ አግኝቷል፡፡ትርጉሙም የመሬት እንብርት ማለት ነዉ፡፡ ዣውሻ ተራራን በሸፊቴ ከተማ ማኀል ላይ ሆኖ ማየት የሚቻል ከመሆኑም በላይ ቀጥ ብሎ የቆመ መሆኑ ለየት ያደርገዋል፡፡ ይህ ተራራ ለዘመናት የሀገር ሀብት ሆኖ የቆየ ብሆንም በህዳር 23/2009ዓ.ም የሀገር ሀብት ሆነው ለቱሪዝም ገበያና ለአካባቢ ጥበቃ መዋል አለበት በሚል ዓላማ ቃለ-ጉባኤ ተይዘዉ ህጋዊ ዕውቅና አግኝቷል፡፡ ህጋዊ ዕውቅና አግኝተው ራሱን ካስከበረበት ገና አንድ ዓመት ያህል ዕድሜ ቢያስቆጥርም በዉስጡ በርካታ የዱር እንስሳት ዝሪያዎችን ፣ የእጽዋትና የአዕዋፍት ዝሪያዎችን ይዟል፡፡ በዉስጡ ከያዛቸው እጽዋት ዝሪያዎች ጥቅቶቹ ዋርካ፣ ሾላ፣ ወይበታ፣ ቁጥቋጦ፣ ሰንበለጥና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡ ከእንሳሳት ዝሪያዎች ደጋሞ ጦጣ ፣ዝንጀሮ ፣ ጅብ ፣ እባብና ሌሎችም የሚገኙበት ነው፡፡
የፊታውራሪ አባይነህ ፊኖ ቤተ-መንግሥት በዛላ ወረዳ በጎፋ ዞን ውስጥ ከሚገኝ
ቀን 2021-08-23
የፊታውራሪ አባይነህ ፊኖ አባት ፊኖ አማዶ ናቸው በትውልድ አከባቢያቸው የዛላ ካዎ ወይም የዛላ ንጉስ ፊኖ ከአባታቸው ከአማዶ ስልጣን ያገኙት በ1901 -1922 ዓ/ም ድረስ ነበር ፤ ፊኖ ከ1923-1928 ዓ/ም ነግሶ በጣሊያን ጦሪነት ምክንያት ስሞቱ ታናሽ ወንድማቸው ፊታውራሪ አባይነህ ፊኖ ንግሥና ስረዓታቸውን ተቀበሉ፡፡ የፊታወራሪ አባይነህ ፊኖ ንግሥና ዘመን ከ1929-1967 ዓ/ም እስከ አብዮት ፍንዳታ ድረስ ዛላን ስያስተዳድሩ ነበር፡፡ ይህ ቤተ-መንግሥት በዛላ ወረዳ ባዶቦጭ ባና ቀበሌ የሚገኘ ሲሆን የቆዬበት ጊዜ ከ1905-1909 ዓ/ም ስሆን የተሰራበት ቁስ ጣሪያው በግፍዝ በቀይ በነጭ በኘቁ የተለያዩ ቀለም ባላቸው የከፍት ቆዳ ነው ፡፡ የቤቱ ኪዳን የተከደነው ደግሞ በጠፍ ነዶ በጭድና በአከባበው በጭቃ ስሰራ ቤተመንግሥቱን ለመስራ ቀኝ አዝማች ፊኖ ባለሙያዎች ከአዲስ አበባ እንዳመጡ ይነገራል፡፡

ያግኙን
☏046-777-1536
ተዛማጅ ሊንኮች
Copyright © 2021-2025 Gofa Zone Adminstration.All Rights Reserved
Gofa,Ethiopia