የሀልኦ ብልቦ ፀበል በዛላ ወረዳ በጎፋ ዞን ውስጥ ከሚገኝ
ቀን 2021-08-11
ይህ አስደናቂ የተፈጥሮ መስህብ በጎፋና በጋሞ ዞኖች መካከል በ202 Km2 ላይ በሚገኘው የማዜ ብሔራዊ ፓርክ ክልል ውስጥ በሰተ ሰሜን አቅጣጫ ይገኛል፡፡ የሀልኦ ብልቦ አቦዬ ፊል ውሃ (በተለምዶ በአከባበው ህብረተሰብ አቦዬ ፀበል ( የአቦየ ፀበል) ተብሎ የሚጠራዋ የተፈጥሮ ፊል ውሃ እጅግ አስገራሚና አስደናቅ በአከባቢው የሚገኘ ተፈጥሮ የቸሬው ገፀ በረከት ነው ፡፡ የሀልኦ ብልቦ አቦዬ ፀበል የሚገኘበትን አከባቢ የሚያዋስኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ፡- የፃሣ ቀበሌ በስተ ሰሜን ከካንባ ወረዳ በጋሞ ዞን ፣ የጋይሳ ቀበሌ በስተምዕራብ ፣ የሸለ ጋናዜ ቀበሌ በስተደቡብ ምዕራብ ከጎፋ ዞን ስሆን፡፡ የውህ የብልቦ ፊል ውሃ የሚገኚበት አከባቢ (የመልካአ ምድር) አቀማመጥ ለጎፋ ዞን ዛላ ወረዳ ለጋይሳና ለሸሌ ቀበሌዎች በቅርበት የሚገኘ ስሆን የሆልኦ ብልቦ አቦየ ፀበል የባህል ሥርዓት ፈፃሚ ከጎፋ ዞን ዛላ ወረዳ ሸለ ጋናዜ ቀበሌ ብታንቴዎች በስፍራው በየጊዚው በመገኘት በባላዊ መንገድ የአምልኮ ሥርዓቶችን በመፈፀም ከጥንት ጊዜዎች ጀምሮ በዛላ ወረዳ ብታንቴዎች በሸሌ ጋናዜ ኢሊሊ ካዎ ሹቻ (ድንጋይ) ላይና በሆኦ ብልቦ አቦየ ፊል ውሃ ፀበል ባህላዊ የአምልኮት ሥርዓቶችንና በባህላዊ መንገድ ለሚያመልኩት አምልኮ መስዋዕት እንደምያቀርቡ በሀልኦ ብልቦ አቦ ፀበል አጠገብ በሚገኙ የመስዋዕት ማቅረቢያ ቦታዎች ላይ የሚታዩ የተለያዩ የስለት ግንዘቦች ፣ ብር ፣ ናሀስ ፣ ወርቅ ፣ አልባሣትና ልዩ ልዩ ነገሮች ለዚሁ ማሳያዎች ናቸው ፡፡ ይህ ከዚህ ከፍ ስል በፎቶ ግራፍ የተመለከተው ምስል እንደምያመለክተው በሀልኦ ብልቦ አቦዬ ፀበል የተፈወሱ ልዩ የሥጋ ዴዌ ህመም የሚሰቃዩ ሰዎች የብልቦ አቦዬ ፀበል የፈዋሽነት ኃይል የሰሙ ህሙማን ወደዚህ አከባቢ በመምጣት በባህላዊ መንገድ ወደ አቦዬ ፀበል ስገቡ በተለምዶ በጎፍኛ ወይም በጋሙኛ ‹‹ ዶቻ!›› ትሪጓሜውም ‹‹ ቀዝቅዝ ቀዝቅዝ አትጉዳኝ›› እደማለት ነው ፡፡ ይህን በባህላዊ መንገድ እያሉ ምንም ተንኮል የሚባል ነገር በውስጣቸው ሳይዙ ወደ ሀልኦ ብልቦ አቦዬ ፀበል ከገቡ ይፈወሳሉ ፡፡ በአከባቢው ያገኘናቸው የተለያዩ ግለሰቦች እና ከዚህ በፊት በሥጋ ዴዌ ህመም ስሰቃዩ ከነበሩት የሀልኦ ብልቦ የአቦዬ ፀበልን በመጠጣትና በፊል ውሃው በመታጠብ የተፈወሱና ለሌች በሥጋ ዴዌ ህመም ስሰቃዩ ከነበሩበት ስፈወሱ ያዩ የዓይንና የጆሮ እማኞች የሀልኦ ብልቦ አቦዬ ጸበል ፈዋሽነቱ ነወ ይላሉ፡፡ካነጋገርናቸው ግለሰቦች መካከል አድማሱ አዘና ከጻሳ ቀበሌ እንዲህ ስሉ ተናገሩ ‹‹ እኔ በአንድ ወቅት እጅግ በጣም የሥጋ ዴዌ ህመም ውስጥ ወድቀ ነበር ፡፡ ህመሙ ከታች እግሬ ጥፍር ጀምሮ እስከ አናቴ ድረስ ቆስሎ ለማየት እራሱ በሚያስፈራ መልኩ፣ ፀጉሬ ሁሉ ተራግፎ በጣም ታምመ ነበር ህመሙ እየበረታ እየበረታ ስሄድ ወደ ወላይታ ክርስቲያን ፊፈር ተጽፎልኝ ሄድኩኝ፡፡ እዛ ሀኪሙ ስመረምረኝ እንዲህ አለኝ ‹‹ አንተ ለምን የፈላ ውሃ ውል ጊዜ ትጠጣለህ?›› ብሎ ጠየቀኝ እኔም የሀኪሙ ጥያቄ ገረመኝ ፡፡ እንደት እኔ የፈላ ውሃ አዞትሬ እንደምጠጣ አወቀ ብዬ እኔ ማሳዬ ውስጥ በእርሻ ሥራ ላይ ስለምውል አከባቢውም እጅግ በረሃማ ከመሆኑ የተነሳ ምንም ውሃ የሚባል ነገር ስለሌሌ የብልቦ ሀልኦ አቦዬን ፀበል ቀድቼ ወስጀ አቀዝቅዠ ዞትር ማሳዬ ላይ እጠጣው ነበር፡፡ ፊል ውሃውም ከቀዘቀዘ በኃላ ምንም እንደ ለላው ውሃ ጣዕምም የለውም ውሃ፣ ውሃ እራሱ አይልም፡፡ አፍ ውስጥ እንደ ውሃም አይከብድም፡፡ እናም ለካ እኔ ሳላውቅ ውሃ መስሎኝ ስጠጣው ቆይቼ ሀልኦ ብልቦ የአቦዬ ፀበል ተቆጥቶኝ ስጠጠው የነበረው ፊል ውሃ ሰውነተን አደረቀው፣ ቁስል በቁስል አደረገኝ በህልመም ላይ ወደኩኝ እዛው ከወላይታ ህክምና ቦታ ሰውነትህ ደም የለውም ደም ማነስ አለብህ ብሎኝ ምንም ሳይሻለኝ ወደ ቤተ ወደ ጸሣ ቀበሌ መጣሁ፡፡ በድጋም የሀልኦ ብልቦ አቦዬን ፊል ውሃ ፀበሉን ወስጀ በባህላዊ መንገድ ዶቻ ዶቻ ብዬ ስታጠብ ከሥጋ ዴዌዬ ዳንኩኝ! ታምሩ ብዙ ነው የዚህ ፊል ውሃ ፡፡ በማት ምስክርነቱን ተናገረ አርሶ አደሩ፡፡
የኢሊሊ ካዎ ሹቻ ታሪክ (የኢሊሊ ንጉስ ድንጋይ ታሪክ) በዛላ ወረዳ በጎፋ ዞን ውስጥ ከሚገኝ
ቀን 2021-08-02
ኢሊሊ ካዎ ሹቻ የተባለበት ከአከባቢው የሀገር ሽማግሌዎች እንደተረዳነው በጨንቻ ቦርዜ አንድ ታዋቅ ንጉስ ነበሩ ሥሙም ኢሊሊ ካዎ ይባላል፡፡ ይህ ንጉስ በአስተዳደራዊ ሥርዓት ጨካኝና ጠንካራ ንጉስ ነበሩ ፤ በምያስተዳድሩበትም ጊዜ ብዙ በጭካኔ ትዕዛዛትን ለምያስተዳድሩት ህዝብ ይሰጥ ነበሩ ፤ ይህ ንጉስ ከባባድ ትዕዛዞችን ስሰጥ ኖሮ ከዕለታት አንድ ቀን ህዝቡን ሰብስቦ በኮደ ደቤ ንዑስ መንደር ላይ በሚገኘው ትልቅ የድንጋይ ቋጥኝ ላይ አንድ ትልቅ ድንጋይ በአንድ ጣታቸው ብቻ እየገፉ በትልቁ ቋጥኝ ላይ እንድያወጡ አዘዛቸው ፡፡ ህዝቡም ይህ የንጉስ ትዕዛዝ አስፈሪና ካልተፈፀመ የንጉስ ጠንካራ ቅጣት ስለምጠብቃቸው የንጉሱን ትዕዛዝ በምፈጽሙበት ጊዜ የብዙ ሰዎች ህይወት አለፈ ፤ የብዙ ሰዎች ደም እንደጎርፍ መፍሰስ ጀመረ ፡፡ ንጉሱ ኢሊሊ ካዎ ጭካነውን አላቋረጠም ፡፡ አሁንም ይህን ትልቅ ድንጋይ ሰዎች በአንድ ጣታቸው እላይ በትልቁ ድንጋይ አናት ላይ እንድያስቀምጡ አዘዛቸው፡፡ ንጉሱ ይህን በማዘዙ የንጉሱ ምስት የነበረችው ጎዳቴ( የኢሊሊ ካዎ ሚስት) ንጉሱ የህዝቡን ስቃይና መከራ በዓይኑ ተተክሎ እየተመለከተ ለህዝቡ መፈናፈኛ አሳጥቶ በጭካኔ እያዘዘ ስለነበረ ፣ ጎዳቴ ህዝቡን ለመርዳት አስባ የንጉሱኑ ትኩረት ለማሳት ሆን ብላ የለበሰችሁን ቀምስ ቅማል እንደምትለቅም አስመስላ ጭኑዋን ስታሳይ ፤ ከህዝቡ አንድ ሰው በድንገት የጎዳቴን ሁኔታ ያይና ‹‹ኤረ ጎዳቴ ምን እየሆነች ነው?›› በማለት ድምጹን ከፍ አድርጎ ስያሰማ ንጉስ ኢሊሊ ካዎ ይህን ይሰሙና ፍታቸውን ወደ ባለበታቸው (ጎዳቴ) ዞር አድርጎ ‹‹ አንቺ ምን እየሆንሽ ነው?! እርቃንሽን ሸፍኝ !›› ብሎ ሳያበቃ ፣ በአንድ ጣታቸው ድንጋዩን በቋጥኙ ላይ ለማውጣት ስሰቃዩ የነበሩ ሰዎች ይህን እንደ ምቹ አጋጣም በመጠቀም በሙሉ እጃቸው ድንጋዩን በአንድነት ሆ! ብለው በቋጥኙ አናት ላይ አስቀመጡ ይባላል፡፡ ህዝቡም የንጉሱን ትዕዛዝ ፈጽመናል እያሉ ስፍራውን በዕልልታ አቀለጡም ይባላል፡፡ ህዝቡ ይህን ከፈፀሙ በኃላ ወደ ንጉሱ ዘንድ ቀርበው እንዲህ አሉ፣ ‹‹ንጉስ ሆይ! ትዕዛዝህን ፈጽመናል፡፡ ቀጣይ ምን እንድንሰራልህ ትወዳለህ?›› ስሉ ንጉሱን ጠየቁ ፡፡ ንጉሱም እንዲህ አላቸው ‹‹ አሁን በሰማይ ላይ ቤት ስሩልኝ›› ብሎ አዘዛቸው ፡፡ የንጉስ ሁለተኛወ ትዕዛዝ ለሰው ልጅ ፈጽሞ የሚቻል አልነበረምና ፣ ህዝቡም ተጨንቀው የኢሊሊ ካዎ ሚሰት ጎዳቴ ለህዝቡ እሩሩና አዛኝ ስለነበረች እርሷን እንዲህ ስሉ አማከሯት ‹‹ አሁን ንጉስ በሰማይ ቤት ስሩልኝ ብለወ አዘዙን ፡፡ ንግሥትም እንዲህ ብላ መከረቻቸው ‹፣ ነሰርና አሞራ ያዙና በእግራቸው ላይ ጭድ አስራችሁ እሳት ለኩሳችሁ ወደ ሰማይ ላኩ›› ብላ መከረቻቸው ፡፡ ህዝቡም እንዲህ አሉሞት ‹‹ እሽ ንግሥት (ጎዳቴ) ያልሽውን እንፈጽማለን ነገር ግን ያልሽንን ከፈጸምን ንጉስ ኢሊሊ ከጠየቀን ምን እንበል?›› አሉዋት፡፡ ንግሥትም (ጎዳቴም) እንዲህ ብላችሁ ንገሩ ‹‹ ይሄው በሰማይ ቤት ተስርቶ በሰማይ ባለው ቤት ላይ ሰዎች እሳት እያነደዱ ይገኛሉ ብላችሁ ›› ንገሩ አለቻቸው፡፡ ንጉስ ኢሊሊ ሚስት ይህን ሁሉ ተረድታ ስለነበረች ባሏጋ ‹‹ በቃ አሁን ህዝቡ ቤት ሰርተዋል ወደ ሰማይ ህድና በተሰራልህ ቤት ግባ! ›› አለችው ይባላል፡፡ ንጉሱም‹‹ እሺ ነገር ግን እንደት አርገ ወደ ሰማይ ልህድ? ሰማይ አይደረስልኝም›› በማለት ለምሰታቸው ለጎዳቴ መለሱ ይባላል፡፡ ጎዳቴም እንዲህ አለችው ‹‹ ያንተ ሀያልነት ፣ ጉብዝናህ ይህ ነው? ጉብዝናህ እስከዚህ ድረስ ነው መሄድ ካቻልክ ላንቴ ፓሮ (አውራርስ) ይምጣልህ? በአውራርስ ጀርባ ላይ ተቀምጠህ ወደ ተሰራልህ ሰማያዊ ቤትህ ትሄዳለህ? ›› በማለት ባሏን ኢሊሊን ጠየቀች ይባላል፡፡ ንጉሱም ለህዝቡ የእኔን ጉብዝናዬን አሳያለሁ በማት ህዝቡን በመጥራ እንዲህ አላቸው ‹‹ህዝቤ ሆይ! ለእኔ አውራርስ የምባል እንስሳ ይዛችሁ አቅርቡልኝ!›› አላቸው ፡፡ ህዝቡም የንጉሱን ትዕዛዝ ለመፈፀም ከጫካ የዱር እንስሳ የሆነውን ፓሮ (አውራርስ) ይዘው ወደ ንጉሱ አቀረቡ፡፡ ንጉሱም በቀረበው አውራርስ ጀርባ ላይ ጠፍረው አስረው እንድምንም አድርገው ወደ ላይ ከመንደሩ ከፍታ ቦታ በሆነው በተለምዶ ‹‹ ሞሮ መዳ ተብሎ በምጠራ ሥፍራ ወስደው ለቀቁ፡፡ አውራርሱም በዱር በገደሉ እየጋለበ ንጉስ ወደ ምፈልገበት መንገድ ሳይሆን ለራሱ በተመቸው ምንገድ እየፈረጠጠ ስሄድ የንጉስ ሰውነት (አካል) እየተበጣጠሰ እየሄደ እታች መዳማውን ቦታ ስደርስ የንጉሱ ጭንቅላት (የራስ ቅል) ተበጥሶ በወደቀው ቦታ ላይ የንጉስ ደም ፈሰሰ፡፡ በዛ ስፊራ ላይ ወዲያውኑ ፊልና ቀዝቃዛ ውሃ ፈለቀ ፡፡ ይህ ቦታ ከዛን ጀምሮ ‹‹ ሀልኦ ብልቦ›› ተብሎ ይጠራል፡፡ በጎፍኛ ቋንቋ ሀልኦ ብልቦ ማለት ትሪጓማው እጅግ በጣም ሀሩር የበዛበት ከፍተኛ ሙቀት ያለበት ስፍራ ወይም በረሀ ማለት ነው ፡፡ የንጉስ ጭንቅላት ወድቆ በተበጠሰበት እና ደሙ በፈሰሰበት ቦታ ላይ የፈለቀው ፊልና ቀዝቃዛ ውሃ ከዛ ጊዜ ጀምሮ በአከባቢውና ከተለያዩ ቦታዎች የዚህን ስፍራ ታዓምር ሰምቶ በልዩ ልዩ የስጋ ዴዌ ለሚሰቃዩ ሰዎች ከፍተኛ ፈዋሽ ሆኖ ቀሬ፡፡

ያግኙን
☏046-777-1536
ተዛማጅ ሊንኮች
Copyright © 2021-2025 Gofa Zone Adminstration.All Rights Reserved
Gofa,Ethiopia