የሽሌ ጉራ ቅ/ሚካኤል ቤተክርስቲያን ዛላ ወረዳ የሚገኝ
ቀን 2021-11-09
የሽሌ ጉራ ቅ/ሚካኤል ቤተክርስቲያን በአጭሩ የሽሌ ጎራ ቅ/ሚካኤል ጥንታዊ ቤተክረስቲያን በዛላ ወረዳ ውስጥ ከምገኙ ሀይማኖታዊ ቋሚ ቅርሶች መካከል የምመደብ ቅርስ ነው ፡፡ ይህ ቅርስ በዛላ ወረዳ በሽሌ ቀበሌ የሚገኘ ኦርቶዶክስ ጥንታዊ ቤተክርስቲያን ነው የቤተክርስቲያኑን ታሪክ ቀንጨብ አድርገን ስንመለከትው እንደምከተለው ቀርቧል ፡፡ የሽሌ ጎራ ቅ/ሜካኤል ጥንታዊ ቤተክርስቲያን የተመሰረተበትን ዓ/ም በውል ማወቅ ባይቻልም በአፈታርክ ከቀድመው ዕድሜ ጠገብ አባቶች የተነገረው ፣ ሽሌ ደምባ ዝጋ ከተባለበት አሁን የጥምቀት ከተራ በዓል ከሚከበርበት እንደነበር አባቶች ይናገራሉ፡፡ ይህ ቦታ በአከባቢው ነዋሪ አጠራር አንቄነአ ዱቤ ዋጋ ዝጋ እንደምባል ያወሱት አባቶች ቤተክርስቲያኑ እጅግ አስገራም ረጅም ዓመት ታሪክ እንዳለው እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ግራኝ መሐመድ በአንድ ወቅት ቤተክርስቲያን በምያቃጥልቤትና በምያጠፋበት ጊዜ የቤተክርስቲያን የሀይማኖት አባቶች የቃልኪዳን ታቦት እና ነዋዬ ቅዱሳትን በመያዝ እግዚአብሔር በፈቀደ ቦታ እየኖሩ በዋሻ ውስጥ ጽላት ይዘው በመደበቅ ዛን ጊዜን እንደምያሳልፉ አባቶች በአፈታሪክ የምወራውን በማውሳት ፣ ይህም የሽሌ ጉራ ቅ/ሚካኤል ቤተከርስቲያንም አባቶች በጥንት ጊዜ ከዋሻ ውስጥ አውጥተው በሣር በተሰራ ቤተመቅደስ ውስጥ በማኖር እንደምቀድሱ የሽሌ ጉራዊ ቅ/ሚካኤል ታቦት ታዓምረኛ እንደሆነ በተለይ በአከባቢው ምዕመናን ተስለው ያጡትን የሚያገኙበት ፣ ታቦቱ የሰዎችን ውስጥ የሚያውቅ የተለያዩ ታዓምራን እየሰራ የሚገኘ እንደሆነ በማስረዳት በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ተንቀሳቃሽ የቤተክርስቲያኑ ቅርሶችም እንዳሉ ይናገራሉ ፡፡ቤተክርስቲያኑ በግምት ከ200 ዓመት በላይ ዕድሜ ያስቆጠረ እንደሆነና ጥናትና ምርምር ብደረግበት ብዙ የሚጠቅሙ ነገሮች ልገኙበት ይችላሉ ፡፡ የሽሌ ጉራ ቅ/ሚካኤል ቤተክርስቲያን ተንቀሳቃሽ ቋሚ ቅርሶች ተንቀሳቃሽ ቅርሶች 1. የብራሃና መጽሐፊት ፡- • ድርሳነ ሚካኤል • ካባዎች • ታዓምሬ ማሪያም • የብሬት መቆምያ • ቅዳሴ መጽሐፊት • የናሐስ ደወል • ዳዊት • የናሐስ መስቀል • ማህደር (ከቆዳ የተሰራ) • ጽዋ (ከሸክላ የተሰራ) • የምኒሊክ ኩባያ • ከአንድ ዋንዛ እንጨት የተፈለፈለ የታቦት መንበር ( አራት በሮች መስኮቶች ያሉት ) በሽሌ ጉራ ቅ/ሚካኤል ጥንታዊ ቤተክርስቲያን የሚገኙ ቋሚ ቅርሶች በዚህ ጥንታዊ ቤተክርስቲያን ከሚገኙ ቋሚ ቅርሶች መካከል ጥቅቶችን ለመጥቀስ ያክል ፡- • ፊርስራሽ ህንፃዎች እና እድሜ ጠገብ ዛፎች ይጠቀሳሉ ፤ • በጥንት ጊዜ በዛላ አከባቢ የነበረውን የኪኔ-ህንፃ ጥበብ ቁልጭ በማድረግ የመያሳዩ ፊርስራሽ ይጠቀሳል፡፡ ከሽሌ ቅ/ሚካኤል አድሱ ህንፃ በስተሰሜን ምስራቅ በኩል ፈርሶ የሚገኘው ከድንጋይ ከጭቃ የተሰራው የቤተክርስቲያኑ የሚስጥር ቤት ተብሎ የምጠራው ቤተልሔም ይገኛል፡፡የበተልሔም ዛን ጊዜ ውቤት አሁን ላይ ወደ ኃልት በምንቃኝበት ጊዜ እጅግ ውብና አስገራም ይሆን ነበር ያስብላል፡፡ የደብሩ አስተዳደር የሆኑት ቅርሶችን በምያስገበኙን ጊዜ እንደገለጹልን የሚትመለከቱት የቤተልሔሙ ቤት የሚስጥር ቤት ተብሎ ይታወቃል እናም እኔ ከመወለደ በፊትም ይህ ድንጋይ ህንፃ በዚህ ቦታ አምሮና አሸብርቆ ነበር ፡፡ እዚሁ ቦታ ድቁንን ተቀበልኩኝ፡፡ አሁንም እዚሁ ቦታ ቅስናን ተቀበልኩኝ፡፡ እንደምታዩኝ ይሄው እንድመዬን በሙሉ በዚሁ ቦታ ነው ቤተክርስቲያኑን እያገለገልኩኝ ያለሁት፡፡ የዚህ ህንፃ እድሜ ረዥም ነው ፡፡ በማለት ከዚሁ ከጥንታዊው የህንፃ ፊርስራሽ ወደ 18ሜትር በስተሰሜን አቅጣጫ በረጃጅም ዛፎች ጥቅጥቅ ባሌ ደን መሀል ከወሰደን በኃላ አንድ ለላ የህንፃ ፊርስራሽ አሳዩን፡፡ የሽሌ ጌራ ቅ/ሚካኤል ቤተክርስቲያን ተንቀሳቃሽ ቅርሶች ከአንድ እንጨት ተቦርቡሮ የተሰራው የታቦት መንበር (መቀመጫ)የጉራ ቅ/ሚካኤል ታቦት (ጽላት) ለመጀመሪያ ጊዜ በሽሌ ቤተክርስቲያን ታነጸለት የመጀመሪያው ቅዳሰም በዚህ መንበር ላይ እንደተካሄደ የሽሌ ጉራ ቅ/ሚካኤል ቤተክርስቲያን የደብሩ አስተዳደር የሆኑት መ/ር ደመቄ ቶና ቶሮ ያስረዳሉ፡፡ ይህ ከጠንካራ አንድ ትልቅ ዋንዛ እንጨት ምንም የፋቭርካ ውጤት ሳይገባበት በጥንት ጊዜ (ከዛሬ 200 ዓ/ም) በፊት የነበሩየዛላ አከባቢ የሀይማኖች አባቶች በልዩ ጥበብና ዕውቀት የታቦቱ ማደሪያ በሦስት ደረጃዎች በአራት መስኮቶች እና በመጨረሻም አናት (ጫፍ) ላይ ልክ እንደ ቋሚምው ቅርስ ቤተክርስቲያን ጉልላት፣ ታቦቱ መንበር አባት ላይ ጌልላት በማበጀት ሠርተዋል፡፡ ይህ የታቦት መንበር በአሁኑ ሰዓት የጉራ ቅ/ሚካኤል ቤተክርስቲያን እንደ ቅርስ ጠብቀው ይገኛሉ፡፡ • የእያንዳንዱ በር ስፋት 50 በ80 (50X80CM) ወይም 1 ሜትር • የመንበር ቁመት ከመሬት ወደ ላይ ሁለት ሜትር ተኩል 2m½ • ለላኛው ተንቀሳቃሽ ቅርሶች መካከል በቅ/ሚካኤል ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚገኘው የናሐስ ደወል ነው ፡፡ የናሐሱ ደወልክብደት 15Kg በደወሉ ላይ የተቀመጠው መግለጫ (ጀዋጁ ኩፓኒያ ኢትዮጵያ) የሚል አማርኛ ጽሑፍ ነው ፡፡ • የምኒልክ ኩባያ (የድሮ ኩባያ) ብዛት 1 ስሆን በኩባያው ላይ የተቀመጠው መግለጫ (ማብራሪያ) ዳግማዊ ሚልልክ የምል ሆኖ የዳግማዊ ምኒልክ ፎቶ ግራፍ ይገኝበታል ፡፡ በኩባያው ላይ የተሰጠው መግለጫ በአማርኛ ቋንቋ የተፃፈ ነው ፡፡
የገልጣ ቅድስት ማርያም ጥንታዊ ቤተክርስቲያን የ200 ዓመት ታሪክ ዛላ ወረዳ የሚገኝ
ቀን 2021-11-02
በጎፋ ዞን ከሚገኙ ወረዳዎች የከተማ አስተዳደሮች መካከል የበርካታ ታሪካዊ ፣ ባህላዊና ሀይማኖታዊ ተንቀሳቃሽና ቋሚ ቅርሶች ክምችት በብዛት ከሚገኙበት የዞናችን አከባቢዎች የዛላ ወረዳ ይጠቀሳል ፡፡ በሀይማኖታዊ ቋሚና ተንቀሳቃሽ ቅርስ ስርጭት በዛላ ወረዳ ከሚገኙ ቀበልያት የጋልጣ ቀበሌ ይገኝበታል፡፡ ገልጣ ከዛላ ወረዳ ዋና ከተማ ጋልማ በስተምዕራብ በ12 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚትገኘ ጥንታዊ ዛላ አከባቢ ከተሞች ተርታ የምትመደብ ከባህር ጠለል በ1800 ሜትር ከፊታ ላይ የሚትገኘ የአየር ፀባዩዋ ወይና ደጋ እና ገልጣ በጎፋ ዞን ካሉት አከባቢዎች በአሪት ምርት በብዛት የሚትታወቅ እና ለሎች የእህል ሰብሎችም የምመረቱበት የሰው ልጅ በአከባቢው ለመኖር ተስማሚ የሚባል አየር ፀባይ ያላት በከፍታ ሥፍራ በሜዳማ ቦታ ነዋሪዎቿ ከትመውባት የሚገኑባት እና የመንግሥት ተቋማት ለህብረተሰቡ አገልግሎት ከማድረስ አኳያ በገልጣ ከጁነር እስከ ሀይስት ትም/ት ቤቶች፣ ጤና ከላዎች ፣ ጤና ጣቢያ ፣ የግብርና ጣቢያዎች እና የምርምር ማዕከላት በጋልጣ በተለያዩ አቅጣጫዎች መኖራቸው ለህብረተሰቡ ኑሮ እንደ ጥሩ አጋጣሚ ስሆን የገልጣ ቀበሌ የመሰረተ ልማት ተጠቃሚ ከሆነ ውሎ ስንብቷል ፡፡ የመንገድ ፣ እንድሁ የመጠጥ ውሃ አገልግሎትና መብራት የጋልጣ ቀበሌ ነዋሪዎች ከሚጠቀሙት የመሠረተ ልማት ዓይነቶች ጥቅቶቹ ናቸው፡፡ በገልጣ የምከትም አልያም አቋርጧት የሚያልፉ መንገደኛ በቀላ የሻይ ቡና አገልግሎት እንዲያገኘ በመንገድ ዳር አልያም ገባ ብሎ በመንደሮች ለእንግዳ አገልግሎት ልሰጡ የሚችሉ የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አለመኖራቸው ወደ ታሪካዊቷ ጋልጣ በየዓመቱ ጥር 21 ቀን የአስተሪዮ ማርያም በዓል ለማክበር ከተለያዩ ቦታዎች የሚጎርፉ እለቱ ታዳሚ እና ጎብኚ ይህን አገልግሎት ለማግኘት መቸገሩ የተለመደ ጉዳይ ሆኗል፡፡ ገልጣ ቅድስት ማርያም ጥንታዊ ቤተክርስቲያን በጎፋ ዞን ከሚገኙ እድሜ ጠገብ ቤተክርስቲያኖች ተርታ ይመደባል፡፡ ከዛሬ ሁለት መቶ ዓመት በፊት በ1812 ዓ/ም ዛላ አከባቢ አንድ ትልቅ ዜና ሰማ፡፡ የገልጣና ዑባ አከባቢዎች አስተዳደር የነበሩ ካዎ ታንጋ አይሣ (ንጉስ ታንጋ አይሣ) (King Taniga Ayissa) በዚያን ጊዜ የገልጣ አከባቢ ህዝብ ከፍተኛ ጥያቄ የነበረው በገልጣ አንድ የኦርቶዶክስ እምነት ተቋሚ እንድገነባ እና በሚገነባው ህንፃ (ቤተክርስቲያን) ጽላት (ታቦት) ገብቶ ህዘበ ክርስቲያኑ መንፈሳዊ አገልግሎት እንድያገኝ የሚል ጥያቄ ነበር ፡፡ ይህ የህዘብ የዘመናት ጥያቄ የከነከናቸው ንጉስ ታንጋ ለት ተቀን በጉዳየ ዙሪያ ማሰብ መጨነቅ ተያያዙ ፤ሰ ከሃይማኖት አባቶችና ከታዋቅ ግለሰቦች ጋርም ስለዚህ ጉዳይ ይመክራሉ፡፡ ንጉስ ታንጋ በገልጣ የሀገር ሽማግሌዎችን ታዋቅ ግለሰቦችን ሰብስበው በጉዳየ ላይ ከመከሩ በኃላ አንድ ታሪካዊ ውሳነ ላይ በመግባባት ውሳነውን አፀኑ፡፡ የገልጣ አከባ ህዝብ (ምእመን) የራሱ የሆነ ቤተ አምልኮ ስፍራና ቤተክርስቲያን እንደምታነጽ ፣ በምታነፀው ቤተክርስቲያን ውስጥ ታቦት (ጽላት) እንደምገባ ፤ ቤተክርስቲያኑን የሚያገለግል ካህን ዲያቆንና ሙነክሰ እንደሚያስፈልግ ንጉሱ ብልህ ነበሩና ቅድመ ዝግጅት ሥራን በአግባቡ ከጠናቀቁ በኃላ ጥያቄው ህዝባዊ መሠረት(የገልጣ) አከባቢ ህዝብ (ምእመን)ጥያቄ እንደነበር በማውሳት በወቅቱ ኢትዮጵያን ከሚያስተዳደሩ ንጉሰ ነገስት ቀዳማዊ ምኒልክ ዘንድ የገልጣ ህዝብ ጥያቄ አንድ ቤተክርስቲያን እንድታነጽላቸው ከፍተኛ ፊላጎት እንዳለ በማውሳት ጥያቄው በንጉሱ ዘንድ እንድቀርብ አደረጉ፡፡ ንጉሰ ምኒልክም በዛላ ገልጣ ንጉስ የቀረበላቸውን ጥያቄ ካዩ በኃላ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ጥያቅያቸውን ተገብና ምላሽ የምሰጥበት እንደሆነ በመግለጽ አንድ ቄስና መኖክሰ በመመደብ ንጉሰ አይሣ ወደ ጎፋ ገልጣ ከአዲስ አበባ ስመለሱ አንድ የማሪያም ጽላት (ታቦት) እና የተለያዩ ነዋዬ ቅዱሳትን መምህር (ካህን) ክዳኔ ወልድንና መኖክሰ የነበሩትን አባ ዜናን በመመደብ እጅግ ፈታኝና አድካም የሆነውን ረዥም ጉዞ ከአዲስ አበባ እስከ ጎፋዋ ገልጣ ድረስ ቀን ለት በጓዝ የማርያምን ጽላት (ታቦት) በመያዝ ንጉስ ታንጋ ወደ ምያስተዳድሩዋት ገልጣ ደረሱ፡፡ ንጉሱ ታቦቱንና ነዋዬ ቅዱሳትን ከእኔ አገልጋይ ካህንና መኖክሰ ጋር ይዘው ገልጣ ስገቡ የገልጣ አከባቢ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ ምእመን በነቅስ በመውጣት ታቦቴ ህጉን በእልልታና በምስጋ በመቀበል ንጉሱ አከባቢውን ነዋሪ ምላሽ እንዳሰገኙ በማመሰገን እጅግ በጉጉትና በናፍቆት የሚጠብቁ ምእመኖች ለእርሳቸው ያላቸውን ድጋፍና ምስጋና አበረከቱ፡፡ የገልጣ ቅድስት ማርያም (Gesha Gella7o Marriyamo) ጽላት (ታቦት) ከእኔ ሙሉ ነዋዬ ቅዱሳት ጋር በንጉስ ምኒልክ ሙሉ ፍቃድ አግኝቶ ከአዲስ አበባ ወደ ጎፋዋ ጋልጣ የመጣው በ1812 ዓ/ም ነው ፡፡ የገልጣ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን በሸዋ ክፍለ ሀገር ወደ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ዛላ ወረዳ ጋልጣ ቀበሌ በምመጣበት ጊዜ በገልጣ ምንም ተገንቢቶ የነበረ ቤተክርስቲያን እንዳልነበሬ ታሪክ ተናጋሪዎች ያስረዳሉ ፡፡ የገልጣ ቅድስት ማርያም ጽላት ከሚኖርበት ከአዲስ አበባ በንጉስ ታንጋ እና በቤተ እምነቱ የሀይማኖት መሪዎች ታጅቦ ገልጣ ከገባ በኃላ በድንኳን ውስጥ ጽላቱ ለአንድ ዓመት ያክል እንደኖሬ ታሪክ ተናጋሪዎችና የሃይማት መሪዎች በማስረዳት ቤተክርስቲያኑ ዛሬ ካለቤት ቦታ በ1812 ዓ/ም ላይ አንድ ትልቅ እጅግ ጉዙፍ የሆነ የጽድ ዛፍ እንደነበረ በማስረዳት በድንገት ምንም የዝናብ ምልክት ሳይኖር ከእለታት አንድ ቀን ከፍተኛ የሆነ ነጎድጓድ ተስምቶ ከሰማይ ሀይለኛ ድምጽ ያሰማ መብረቅ በመወረድ ያን የጽድ ዛፍ ይመታዋል ፡፡ ጽዱን መብረቅ በምመታበት ጊዜ የጽዱ ሥር ምረቅ ነቅሎ ከጣለ በኋላ ቦታውን እራሱ ልክ ሰው አውቆና አስቦ ቤት ለመስራት እንደምደለድል (እንደምያስተካክል) በማስተካከል የቤተክርስቲያኑን መሰረት መጣያ ቦታ እራሱ እንደ መረጠ የታሪክ አዋቅዎች በማስረዳት የሆነውን ይተሪካሉ፡፡ ይህን የተመለከቱ የአከባቢው ነዋሪዎችና ንጉስ ታንጋ ይህን ቦታ የመረጠውና ያዘጋጀው ፈጣሪ እንጅ ሰው አይደለም እናም የቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን መሰረተ የምያለው በዚህች ቦታ ነው ፡፡ ይህ ቦታ መቅደሱ የምሰራበት በእግዚአብሔር የተመረጠ ቦታ ነው በማለት ይደመድማሉ ፡፡ ህዝቡም የመሪያቸውን ሀሳብ በመጋራት የቤተክርስቲያኑ መሠረት የሚያርፍቤት ቦታን ይረዳሉ፡፡ ንጉስ ታንጋ በምያስተዳድሩት አከባቢ የምገኙ ነዋሪዎች በሙሉ በአንድነት በነቅስ በመውጣት የቤተክርስቲያኑ መስሪያግብአት እንድያቀርቡ ጥሪ ያስተላልፋሉ ፡፡ በንጉሱ የተላለፈው መልዕክትና የሥራ ጥሪ እጅግ ይከበር ነበርና ሁሉም ሰው ወደ ታዘዘው ተግባር ላይ እንደተሰማራ የታሪክ ተናጋርዎች ያስረዳሉ፡፡ የገልጣ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ለማነጽ ከፍተኛ የሆነ የሰው ኃይል እንደተሳተፈና እጅግ ወድ ዋጋ ያላቸው የቤት መስሪያ ግብአቶች በቤተክርስቲያኑ ግንባታ ላይ እንደዋሉ ታሪክ ያስረዳል፡፡ ቤተክርስቲያኑን ለመገምባት ግብአት ሰቀርብባቸው የነበሩ ቦታዎች ዑባ ሁሉም ቀበሌዎች ፣ ዑባ ደብረ ፀሐይ ፣ አሪ አሚፒ ከጃውላ እና ከኦይዳ አከባቢዎች ቤተክርስቲያኑን ለማነጽ የተለያዩ ውድና በዋጋ የማይተመኑ ግብአቶች በልዩ ጥንቃቄ ከእነዚህ ከተጠቀሱት ቦታዎች እስከ ጋልጣ ድረስ ስጓጓዝ እንደነበር ታሪክ ይናገራል፡፡ የገልጣ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ለመስራ ከዛሬ 200 ዓ/ም በፊት የጎፋ አከባቢ የስነ እዕምሮ ውጤት ታክሎበት ህንፃውን በልዩ ጥበብ ለማነጽ ይረዳሉ የተባሉ አከባቢው ውድ የቤት መስሪያ ግብአቶች ተብለው የተጠቀሱት ፡- • የጽድ እንጨት ለጣሪያው ተሸጋጋሪ እና እንደ ወራጅ የተወሰደ፤ • ሻማሆ (ወይራ) ለግድግዳው ሙሉ ሥራ የተወሰደ፤ • ቀርከሀ (ለጣሪያ ሥራ) ከጃውላ የተጓጓዘ የጽድ እንጨት የጽድ እንጨት ከአሪ አምኜ አከባቢ ለጣሪያው ተሸጋጋሪ እንደ ወራጅና ማገር በመሆን እንድያገለግል ተብሎ የመጣ ስሆን፡፡ ሻማሆ (ወይራ) የወይራ እንጨት (ሻማሆ) በምንም አይነት መንገድ በቀላሉ ማይጎዳ እጅግ ጠንካራ እንቸት ተደርጎ ስለተመረጠ ለሙሉ ግድግዳ ሥራው የወይራ እንጨት አገልግሎት ላይ ውሏል፡፡ ቀርከሀ ከቀርከሀም እንደለሎች ጠንካራና አደጋን መቋቋም የሚችል ከመሆኑ የተነሳ ቤተክርስቲያኑ በምሰራበት ጊዜ ለጣሪያው ማገርና ውስጥ ደግሞ ለቅድስቱ ክፍል ግድግዳ ሥራ ላይ ውሏል፡፡ በልዩ ጥበብ የዛን ዘመን ሰዎች በጭንቅላታቸው ውስጥ የነበረውን ዕውቀት በመጠቀም የጣሪያው ዲዛይን እንድህ በማረና ቀልብ ሳቢ በሆነ መልኩ በአከባቢ ምርት አሸብረቀውታል፡፡ ገመድ (ጎላ ወዶሮ) ይህ የቤተክርስቲያንቱ ጣሪያና ግርግዳ ምስማር በሌለበት ወቅት ከዛሬ 200 ዓመት በፊት ቤተክርስቲያንቱን ሥሰሩ የነበሩ ልዩ ችሎታ ያላቸው የዛ ዘመን ማሐንዲሶችና ጥበበኞች ይህን ቤተክርስቲያን እንዲህ ጠንካራና ለዓይን ማራክ እንድሆን አድርገው በምሰሩበት ጊዜ ምንም የፋብርካ ውጤት ሳይጠቀሙ በሚያንጹበት ወቅት ቃጫ ገመድ (ጎላ ወዶሮን) እንድ ሚስስማርና ማስዋቢያ እንድያገለግል በማድረግ እጅግ በጥንቃቅ የተገመደ በድርና በነጠላ ተገምዶ ጥንካሬ እንድሮረው ተደርጎ ታስቦ በተገመደ ገመድ (ጎላ ወዶሮን) እንዲህ በመጠፈር ቤተሰርዎች ቤቱን አቁመዋል፡፡ የግድግዳ ጭቃ አፈር የግድዳውን ጭቃ እጅግ በርካታ ምእመን በጉልበት ሥራ ላይ ተስማርተው ጭቃው ጥንካሬ እንድኖሬው በጤፍ ጭድ ተረግጦ ጭቃው ጉዱንሶ ሻፋ ተብሎ በተለምዶ ከምጠራበት ሥፍራ በሰው ኃይል ተጓጉዞ የቤተክርስቲያኑ ግድግዳ በጭቃ የመለጠፍ ሥራ ተጠናቋል ይላሉ የታሪክ ተናጋር የሀገር ሽማግሌዎችና የእምነቱ ተከታዮች እና የሃይማቱ መሪዎች፡፡ በተጨማሪም ይቤተክርስቲያን በምታነጽበት ጊዜ የግድግዳው ጭቃ እጅግ የጠነከረና ረጅም ዕድሜ እንድኖረው ፣ ምስጥ እና ሌሎች ባዕድ ነገሮች እንዳይጎዳው ተደርጎ በእንቁላል ጭቃው እንደተረገጠ የታሪክ ተናጋሪ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሀይማኖት መሪዎች ያስረዳሉ፡፡ የቤተክርስቲያንቱ ጣሪያ አሰራርና የተሰራበት ግብቸት የቤተክርስቲያኑ ጣሪያ የተሰራበት ውድ ከሆኑ እንጨቶች (ከጽድ ፣ ቀርከሀ እና ሌሎች ጠንካራ የእንጨት አይንቶች( ስሆን የቤተክርስቲያኑ ጣሪያ እጅግ ረዥም በሆነ ሰንበለጥ (ሣር) በጎፋ አከባቢ ቤት በምሰራበት ጊዜ የቤት ጣሪያ ኪዳን በጥሩ ችሎታ መክደን ይችላሉ ተብለው ባለ ልዩ ችሎታ ባለቤቶች ናቸው በሚባሉ እውቅ የቤት ጣሪያ ከዳኞች እጅ ነው የጋልጣ ቅድስት ማሪያም ቤተክርስቲያን ጣሪያው የተከደነው ፡፡ የቤተክርስቲያኑጣሪ በሚከደንበት ጊዜ በልዩ ጥንቃቀ ዝናብ እንዳያሳልፍ በቀላሉ በንፋስ እንዳይነሳና ምንም አደጋ እንዳይኖር በልዩ ጥንቃቀ በምከደንበት ጊዜ በሰንበለጥ ሣር ውስጥ ማጠናከሪያ ወደ 40 (አርባ) ቁና ጤፍ ማለትም ወደ 2 ሁለት( ኩንታል የሚጠጋ ንጹሁ ጤፍ በሰንበለጡ ሣር መሐል የቤት ከዳኞች እንድጨመሩ ታሪኩን የምተርኩ አዋቅዎች ያስረዳሉ ፡፡ የሰንበለጡን ሳር ጫፉን ወደታች በመዘቅዘቅ የሣሩን ቅጥ ወደላይ ወደ ቤተክርስቲያኑ ጉልላት በመመለስ በመሐል በሣሩ ውስጥ ጤፉን በመጠቅጠቅ ምንም ክፍተት (ብርሃን) የሚባል ነገር በሣሩ አልፎ ወደ ቤተክርስቲያኑ መቅደስ እንዳይገባ ተደርጎ ጣሪያው በልዩ ጥንቃቄ እንደተከደነም ታሪኩን የሚያስረዱ አዋቅ ሰዎች ያስረዳሉ፡፡ በተጨማሪም የጣሪያው ኪዳን እንቁላል በጣሪያው ላይ እንደተጨመረም ይናገራሉ፡፡ በጣሪያው ሣር ኪዳን ውስጥ እንቁላል ተጨመረውሰጣሪያው ልዩ ጥንካሬ እንድኖረው እና የጣሪያውን ኪዳን አጥብቆ እንድይዝ ታስቦ እንደነበረም ታሪኩን የምተርኩልን የሀገር ሽማግሌዎች ያስረዳሉ፡፡ የቤተክርስቲያኑ የጣሪ ኪዳን ስራ እንደተጠናቀቀ ዙሪውን በማሳመር ልዩ ውቤት በማሪ ከዳኞች ከጣሪያው ላይ ይወረዳሉ፡፡ የገልጣ ቅድስት ማርያም ቤትክርስቲያን ውሳጣዊ ክፍል በልዩ ጥንቃቅ ተመርጎ የተጠናቀቀወ ግድግዳ የቤተክርስቲያኑ ጣጣውን የጨረሰው ጣሪ በውስጥ እጅግ የወቅቱ ጠብባን ተጠበው የውቤት ስራን ስርተውበታል ፡፡ ግድግዳው ላይ በጥንት ጊዜ የተሳሉ የቅዱሳን መልዕክት ምስልና የፃድቃን አባቶች ምስል በየኮርነሩ በመቅደሱ ውስጥ ተሰቅሎ ስለመከቱ አግራሞትን ከመጫሩ፣ ባለፈ ምስሎቹ የሆነ ነገር በቅርበት በአካል የምመለከቶት ነገር እየመሰለ ልዩ ስሜት ይጭርቦታል፡፡ጣሪያውን ሽቅብ አንጋጠው ስመለከቱ በጥታዊ ጃኖ በሚባል ልብስ ኮርኒሱ አሸብርቋል፡፡ ጣሪያው በሥስቱ ቀለማት ( በነጭ በቀይና በጥቁር) ቀለም ባሸበረቀ ጃኖ ጨርቅ ደምቆ እውነት የዛን ጊዜ የነበረውን የማስዋብያ ዜደና ለማስዋቢያነት አባቶች ስጠቀሙበት የነበሩ የግብዓት አይነቶች በምናቦ ይቃኛል፡፡ በገልጣ ቅድስት ማሪያም ጥንታዊ ቤተክርስቲያን በደብሩ አስተዳደር ካህንና በጥቅት የቤተክርስቲያኑ አገልጋዮች ብቻ በልዩ ሚስጥ ተደብቀው የሚገኙ ተንቀሳቃሽ ከ200 ዓመት ዕድሜ በላይ ያስቆጠሩ ነዋዬ ቅዱሳትና ቅርሶችን በጥቅቱ ለመጥቀስ ያክል፤ • ብራሃና መጽሐፊት • ታምረ ማሪያም • የወርቅ መስቀል • ግንዘት • የብር መስቀል • መጽሐፊቴ ዱጓዋ • የብር ስዕል • ቅዳሴ ለማሪያም • የናሐስ ደወል • ክርስትና መፀሐፍ • መጎናጸፊያዎች (ካባዎች) • የናሐስ ጽናጽል (የተሰባበሩ ብዛት አምስት ) • አራቱ ወንጌል…..ወ.ዘ.ተ
የቶባ ትክል ድንጋይ
ቀን 2021-12-14
የቶባ ትክል ድንጋይ፡- የሚገኘው በመሎ ኮዛ ወረዳ፤ በቶባ ቀበሌ አርብ ገበያ ላይ ሲሆን፤ ትክል ድንጋዬቹም በ50 ሜትር ርቀት ጎን ለጎን የቆሙ ሲሆኑ፤ በስተቀኝ በኩል ያለው 1 ሜትር ተኩል ከፍታ እና ስምንት ኩንታል ክብደት እንዲሁም በስተግራ በኩል ያለው 1 ሜትር ከ60 ሴ.ሜ ከፍታ እና ስድስት ኩንታል ክብደት እንደሚሆናቸዉ ይገመታሉ፡፡ የአከባቢዉ ታዋቂ የሀገር ሽማግሌ (አቶ አውሳቶ አለደ) እንዲህ ሲሉም ይናገራሉ፡፡ ይህ ታዋቂ ትክል ድንጋይ በማን፤ እንዴት እና መቼ እንደተተከሉ ስንጠይቃቸው፤ እሳቸውም የሰጡት ምላሽ “እኛም አባቶቻችን ሲናገሩ ሰምተናል እንጂ አናወቅም፤ ይላሉ ነገር ግን ይህን ድንጋይ የግራኝ መሐመድ፤ ሻሾ የሚባለዉን ፈረሳቸውንም ለማሠር ሲባል ግራኝ መሐመድ በግራ እጃቸው ተክለዉ ያቆሙዋቸዉ ትክል ድንጋዮች እንደሆኑ ሲናገሩ፤ ግራኝ ይህንን ያደረጉበትም ምክንያት የግራኝ ፈረሳቸው አመለኛ እና ጉልበተኛ ከመሆኑ የተነሳ ወደዚያ አከባቢ በመጣበት ጊዜ በነዚህ ድንጋዮች ላይ ለማሠር የተጠቀመበት እንደነበር የዕድሜ ባለፀጎች ይህ አፈታሪክ ሲወርድ ሲወራረድ እንደመጣ ይናገራሉ”፡፡ ነገር ግን እንደ ጎፋ ዞን ባ/ቱ/ስ/መምሪያ ይህንን ሀሳብ እንዳለ ከመዉሰድ፤ እነዚህ ትክል ድንጋዮች በክልላችን ከሚገኙት ከጥያ ትክል ድንጋዮች ጋር በዓይነት፤ በክብደት፤ እንዲሁም በቁመት የተቀራረበ ተመሣሣይነት ያላቸዉ በመሆኑ፤ የጥያ ትክል ድንጋይም ከዛሬ 800 ዓመት በፊት እንደቆሙ አንዳንድ መረጃዎች ሲያስረዱ፤ በሌላ መላምትም በቅድመ ታሪክ ዘመን እንደተተከሉ ሲያስረዱ፤ የተረጋገጠ መረጃም ባለመገኘቱ የቶባ ትክል ድንገዮችም ተጨማሪ የአርኪዮሎጂ ጥናቶች ለማድረግ ተመራማሪዎች ወደ አከባቢዉ መምጣት እንዳለባቸዉ ጠቋሚ በመሆኑ ወደፊት ከከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት ጋር በመሆን ጠንካራ የምርምር ሥራን መሥራት እንዳለብን እና ልክ እንደ ጢያ የትክል ድንጋዮች በዩኔስኮ የማስመዝገብ ዕድልም እንዳለን መናገር እንደሚቻል ስንገለጽ፤ የጢያ ትክል ድንጋዮችም በዩኔስኮ በ1972 ዓ.ም በዓለም ቅርስነት ተመዝግበዋል፡፡
ያግኙን
☏046-777-1536
ተዛማጅ ሊንኮች
Copyright © 2021-2025 Gofa Zone Adminstration.All Rights Reserved
Gofa,Ethiopia