የአገኒ አባ ጥብቅ ደን
ቀን 2021-09-03
የአገኒ አባ ጥብቅ ደን ይህ ጥብቅ ደን ጐፋ ዞን ደምባ ጐፋ ወረዳ በፃንጋ ደራራ ቀበሌ የሚገኝ ስሆን ከወረዳ ማከል 53 ኪ/ሚ የምርቅ እና 2ዐ ኪ/ሜ በመኪና እስከ ሎጤ ዛዳ ዶላ ቀበሌ ክልል ቀርቦ በእግር/ በበቅሎ 33 ኪ/ሚ ያስከሄዳል፡፡ አዋሳኝ ቦታዎች በምስራቅ ወይደ ዳርግንሣ በምዕራብ ገዜ ጐፋ ወረዳ በሰሜን ኦሞ ወንዝ በደቡብ ፃንጋ ቀበሌ ያዋስናል፡፡ የደን ሽፋን 11,115125 ሄክታር ስሆን ሦስት የአር ንብርቶች ይተከፈለ ነው፡፡ ጥቅጥቅ ያለ ደጋማው የአየር ንብረት 6669 ሄ/ር መካከለኛው ወይነደጋው 1111.6 ሄ/ር ቆላማው አካባቢ 3334.5 ሄ/ር በመሆን በተለያዩ በተጨማሪ በውስጡ የተለያዩ የዱር እንስሳት አንበሳ፣ ነብር፣ ዝንጀሮ፣ ጦጣ፣ ጅብ፣ ከርከሮ፣ ጐሽ፣ አሣማ፣ ጉረዛ፣ ዳልጋአንበሳ፣ አነር፣ ሚዳቆ፣ ቆርኬ፣ ተኩላ፣ ድኩላ፣ ጥርኝ፣ ጃርት፣ ቀበሮ፣ ሸለመጥማጥ፣ ጥንቸል የመሳሰሉት ናቸው፡፡ አዕዋፍ አይነቶች ጭልፍት፣ ዳክዬ፣ ግንድቆርቆሮ፣ ድንብጥ፣ የሌልት ወፍ፣ ጉጉት፣ ጭልፍት፣ ቁራ፣ አሞራ፣ ጥንብ አንሣ የመስከረም ወፍ፣ ጊሪሳ፣ ጭላሾ የመሳሰሉት አዕዋፋት የሚገኙ በመሆኑ በሆድ ተሳቢ እንስሳት ዘንዶ፣ ኮበራ፣ አሜ፣ እፉኝት፣ ካፎሆተኤ፣ ጥቁር እበብ፣ አደዩ፣ ዶርባ፣ ሐሶ፣ቡሌ - - - ወዘተ የዕጽዋት አይነቶች የተሸፈነ ነው፡፡ ለምሣሌ ለገበያ ቀጥታ አርሶ አደሩ የምጠቀማቸው ዕጽዋት፣ ጫት፣ ገሾ፣ ኮሮርማ፣ ዝንጅብል፣ ዘንባባ፣ - - - ወዘተ ስሆን እንድሁም አርሶ አደሩ በርቀቱ የተነሳ ብዙ ተጠቃሚ ባይሆንም የበርሃ እጣን ዛፍ ምርት እየሰጠ መሆኑን በበጋ ወቅት መጠቀም ይቻላል፡፡ እንደገና ለቤት መሥሪያና ለማገዶ የሚጠቀሙት ወይባ፣ ቱንቃለ፣ ሾላ፣ ድሞ፣ ዱልኦ፣ ጨሌ፣ ሐሶ፣ ዳንጋርሣ ሐላኮ፣ ፑቶ፣ ቃርጭቶ፣ ኦንጋፊሬ፣ ገበላ፣ አራደ፣ ፑሎ፣ ላደ፣ ሐስቴ፣ ኦቻ፣ ሺሻ፣ ጋይለ፣ ማፆቴ፣ አምቤ፣ ፃይሶ፤ ቡርጉደ፣ ሙዝጌ፤ ሶሊዜ፣ ጋራ፣ ካናካስለ፣ ቡራ/ግራር፣ ቦርቶ፣ ፃላሄ ሃላኮ፣ ፃደ፣ ቆታ፣ ቀታ፣ ሻዥላ፣ ሚሲምሎ፣ ጋርቾ፤ ቃርባ፣ ቃልቃሎ፣ ዳላሜ፣ ባርኤ፣ ፓራንቾ፣ ሳንገኖ፣ ኦካንሶ፣ ዳጋ፣ ፋራንቶ፣ ጉጉሰ፣ ዋራ ቱኬ፣ ሾንጋላቻ - - -ወዘተ ደኑ ውስጡ የሚገኙ ዛፎች ከዕድሜ ብዛት የተነሳ ከቅጠላቸውና ከቅርጫፋቸው እስከ ግንዳቸው ድረስ የሻጋታ ድሮችን አነስንሰውና ለብሰው የዕድሜ ካባውን ደርቦ ለተመልካች ልዩ ተመስጦን ይፈጥራሉ፡፡ ለአከባቢ ኀብረተሰብ ለወረዳው ህዝብ ኩራት ሆኖ ይገኛል፡፡ በተለይ ደኑ በተለያዩ ተራራዎች የቡይጋንድ ዋሻ እስከ አሁን መታየት ያልተቻለው ማዕድናት ጭምር ያለ መሆኑን በጣም ማራኪ ተፈጥሮ ስለሆነ መጥተው ይጐበኙ እንላለን፡፡
ካርዛ ዋሻ
ቀን 2021-07-01
ከደምባ ጎፋ ወረዳ መቀመጫ ከሳውላ ከተማ ወደ ሰሜን 12 ኪ.ሜ በሣውላ ሶዶ ዋናው መንገድ ከተጓዙ ካርዛ ቀበሌን ያገኛሉ፡፡ታድያ በካረዛ ቀበሌ ለነዋሪውም ለእንስሳቱም ባለውለታ የሆነ ትልቅና ድንቅ የቱሪስት መስህብ አሉ፡፡ ይህ ተፈጥሮዊ መስህብ ድሮ በአከባቢው ከሚከሰቱ ጦርነቶች የአከባቢውን ነዋሪዎች በሆዱ ሸሽጎ አጋሪነቱን ያሳየ ድንቅ ዋሻ ነው፡፡ ዋሻ ጨዋማ በመሆኑ የአከባብ እንስሳት ውለው እዚየው ነው፡፡ የካርዛ ዋሻ 3 ክፋሎች አሉት፡፡ የአከባቢዊ ነዋሪዎች ለ3ቱም ክፋሎች ስያሜ ሰጥተዋል ዴሻ ጎንጎሎ/የፋየል ዋሻ የመጀመረያው ስሆን 4 ሜትር ስኩዌር ስፋት ያለው ሁለተኛው /ሜሄ ጎንጎሎ/ የከብት ዋሻ 100 ሜትር ስፋት ስኖረው 3ኛውና የመጨረሻው /ዶርሳ ጎንጎሎ/ የበግ ዋሻ 3 ሜትር ስፋት ያለው ነው፡፡ ይህ ዋሻ ምቹ መንገድ ያለው ተፈጥሮዊ መስህብ ነውና መጥተው እንድጎብኙ ተጋብዘዋል፡፡
የፊታውራሪ አባይነህ ፊኖ ቤተ-መንግሥት በዛላ ወረዳ በጎፋ ዞን ውስጥ ከሚገኝ
ቀን 2021-08-23
የፊታውራሪ አባይነህ ፊኖ አባት ፊኖ አማዶ ናቸው በትውልድ አከባቢያቸው የዛላ ካዎ ወይም የዛላ ንጉስ ፊኖ ከአባታቸው ከአማዶ ስልጣን ያገኙት በ1901 -1922 ዓ/ም ድረስ ነበር ፤ ፊኖ ከ1923-1928 ዓ/ም ነግሶ በጣሊያን ጦሪነት ምክንያት ስሞቱ ታናሽ ወንድማቸው ፊታውራሪ አባይነህ ፊኖ ንግሥና ስረዓታቸውን ተቀበሉ፡፡ የፊታወራሪ አባይነህ ፊኖ ንግሥና ዘመን ከ1929-1967 ዓ/ም እስከ አብዮት ፍንዳታ ድረስ ዛላን ስያስተዳድሩ ነበር፡፡ ይህ ቤተ-መንግሥት በዛላ ወረዳ ባዶቦጭ ባና ቀበሌ የሚገኘ ሲሆን የቆዬበት ጊዜ ከ1905-1909 ዓ/ም ስሆን የተሰራበት ቁስ ጣሪያው በግፍዝ በቀይ በነጭ በኘቁ የተለያዩ ቀለም ባላቸው የከፍት ቆዳ ነው ፡፡ የቤቱ ኪዳን የተከደነው ደግሞ በጠፍ ነዶ በጭድና በአከባበው በጭቃ ስሰራ ቤተመንግሥቱን ለመስራ ቀኝ አዝማች ፊኖ ባለሙያዎች ከአዲስ አበባ እንዳመጡ ይነገራል፡፡
ያግኙን
☏046-777-1536
ተዛማጅ ሊንኮች
Copyright © 2021-2025 Gofa Zone Adminstration.All Rights Reserved
Gofa,Ethiopia