የሸሌ ጋናዜ ታሪክ በዛላ ወረዳ በጎፋ ዞን ውስጥ ከሚገኝ
ቀን 2021-08-20
የሽለ ጋናዜ ድንጋይ አምድ በሸሌ ቀበሌ ዶላ በተባለ ንዑስ መንደር የሚገኘ በባህላዊ መንገድ አምልኮ ሥርዓት የሚፈፀምለት ፣ የድንጋይ አምዱን የሚጠብቁና የሚንከባከቡ በአከባበው በባህላዊ ሥርዓት ፈፃሚ ተብለው የሚታወቁ ‹‹ ብታንቴ›› የተባሉ ግለሰብ አሉ፡፡ ይህ የድንጋይ አምድ የሴት ቅርጽ ያለው ሲሆን የንጉስ ሚስት የነበረች ጎዳቴ እንደሆነች ይነገራል፡፡
የሸሌ ጋናዜ ታሪክ በዛላ ወረዳ በጎፋ ዞን ውስጥ ከሚገኝ
ቀን 2021-08-20
የሽለ ጋናዜ ድንጋይ አምድ በሸሌ ቀበሌ ዶላ በተባለ ንዑስ መንደር የሚገኘ በባህላዊ መንገድ አምልኮ ሥርዓት የሚፈፀምለት ፣ የድንጋይ አምዱን የሚጠብቁና የሚንከባከቡ በአከባበው በባህላዊ ሥርዓት ፈፃሚ ተብለው የሚታወቁ ‹‹ ብታንቴ›› የተባሉ ግለሰብ አሉ፡፡ ይህ የድንጋይ አምድ የሴት ቅርጽ ያለው ሲሆን የንጉስ ሚስት የነበረች ጎዳቴ እንደሆነች ይነገራል፡፡
የሀልኦ ብልቦ ፀበል በዛላ ወረዳ በጎፋ ዞን ውስጥ ከሚገኝ
ቀን 2021-08-11
ይህ አስደናቂ የተፈጥሮ መስህብ በጎፋና በጋሞ ዞኖች መካከል በ202 Km2 ላይ በሚገኘው የማዜ ብሔራዊ ፓርክ ክልል ውስጥ በሰተ ሰሜን አቅጣጫ ይገኛል፡፡ የሀልኦ ብልቦ አቦዬ ፊል ውሃ (በተለምዶ በአከባበው ህብረተሰብ አቦዬ ፀበል ( የአቦየ ፀበል) ተብሎ የሚጠራዋ የተፈጥሮ ፊል ውሃ እጅግ አስገራሚና አስደናቅ በአከባቢው የሚገኘ ተፈጥሮ የቸሬው ገፀ በረከት ነው ፡፡ የሀልኦ ብልቦ አቦዬ ፀበል የሚገኘበትን አከባቢ የሚያዋስኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ፡- የፃሣ ቀበሌ በስተ ሰሜን ከካንባ ወረዳ በጋሞ ዞን ፣ የጋይሳ ቀበሌ በስተምዕራብ ፣ የሸለ ጋናዜ ቀበሌ በስተደቡብ ምዕራብ ከጎፋ ዞን ስሆን፡፡ የውህ የብልቦ ፊል ውሃ የሚገኚበት አከባቢ (የመልካአ ምድር) አቀማመጥ ለጎፋ ዞን ዛላ ወረዳ ለጋይሳና ለሸሌ ቀበሌዎች በቅርበት የሚገኘ ስሆን የሆልኦ ብልቦ አቦየ ፀበል የባህል ሥርዓት ፈፃሚ ከጎፋ ዞን ዛላ ወረዳ ሸለ ጋናዜ ቀበሌ ብታንቴዎች በስፍራው በየጊዚው በመገኘት በባላዊ መንገድ የአምልኮ ሥርዓቶችን በመፈፀም ከጥንት ጊዜዎች ጀምሮ በዛላ ወረዳ ብታንቴዎች በሸሌ ጋናዜ ኢሊሊ ካዎ ሹቻ (ድንጋይ) ላይና በሆኦ ብልቦ አቦየ ፊል ውሃ ፀበል ባህላዊ የአምልኮት ሥርዓቶችንና በባህላዊ መንገድ ለሚያመልኩት አምልኮ መስዋዕት እንደምያቀርቡ በሀልኦ ብልቦ አቦ ፀበል አጠገብ በሚገኙ የመስዋዕት ማቅረቢያ ቦታዎች ላይ የሚታዩ የተለያዩ የስለት ግንዘቦች ፣ ብር ፣ ናሀስ ፣ ወርቅ ፣ አልባሣትና ልዩ ልዩ ነገሮች ለዚሁ ማሳያዎች ናቸው ፡፡ ይህ ከዚህ ከፍ ስል በፎቶ ግራፍ የተመለከተው ምስል እንደምያመለክተው በሀልኦ ብልቦ አቦዬ ፀበል የተፈወሱ ልዩ የሥጋ ዴዌ ህመም የሚሰቃዩ ሰዎች የብልቦ አቦዬ ፀበል የፈዋሽነት ኃይል የሰሙ ህሙማን ወደዚህ አከባቢ በመምጣት በባህላዊ መንገድ ወደ አቦዬ ፀበል ስገቡ በተለምዶ በጎፍኛ ወይም በጋሙኛ ‹‹ ዶቻ!›› ትሪጓሜውም ‹‹ ቀዝቅዝ ቀዝቅዝ አትጉዳኝ›› እደማለት ነው ፡፡ ይህን በባህላዊ መንገድ እያሉ ምንም ተንኮል የሚባል ነገር በውስጣቸው ሳይዙ ወደ ሀልኦ ብልቦ አቦዬ ፀበል ከገቡ ይፈወሳሉ ፡፡ በአከባቢው ያገኘናቸው የተለያዩ ግለሰቦች እና ከዚህ በፊት በሥጋ ዴዌ ህመም ስሰቃዩ ከነበሩት የሀልኦ ብልቦ የአቦዬ ፀበልን በመጠጣትና በፊል ውሃው በመታጠብ የተፈወሱና ለሌች በሥጋ ዴዌ ህመም ስሰቃዩ ከነበሩበት ስፈወሱ ያዩ የዓይንና የጆሮ እማኞች የሀልኦ ብልቦ አቦዬ ጸበል ፈዋሽነቱ ነወ ይላሉ፡፡ካነጋገርናቸው ግለሰቦች መካከል አድማሱ አዘና ከጻሳ ቀበሌ እንዲህ ስሉ ተናገሩ ‹‹ እኔ በአንድ ወቅት እጅግ በጣም የሥጋ ዴዌ ህመም ውስጥ ወድቀ ነበር ፡፡ ህመሙ ከታች እግሬ ጥፍር ጀምሮ እስከ አናቴ ድረስ ቆስሎ ለማየት እራሱ በሚያስፈራ መልኩ፣ ፀጉሬ ሁሉ ተራግፎ በጣም ታምመ ነበር ህመሙ እየበረታ እየበረታ ስሄድ ወደ ወላይታ ክርስቲያን ፊፈር ተጽፎልኝ ሄድኩኝ፡፡ እዛ ሀኪሙ ስመረምረኝ እንዲህ አለኝ ‹‹ አንተ ለምን የፈላ ውሃ ውል ጊዜ ትጠጣለህ?›› ብሎ ጠየቀኝ እኔም የሀኪሙ ጥያቄ ገረመኝ ፡፡ እንደት እኔ የፈላ ውሃ አዞትሬ እንደምጠጣ አወቀ ብዬ እኔ ማሳዬ ውስጥ በእርሻ ሥራ ላይ ስለምውል አከባቢውም እጅግ በረሃማ ከመሆኑ የተነሳ ምንም ውሃ የሚባል ነገር ስለሌሌ የብልቦ ሀልኦ አቦዬን ፀበል ቀድቼ ወስጀ አቀዝቅዠ ዞትር ማሳዬ ላይ እጠጣው ነበር፡፡ ፊል ውሃውም ከቀዘቀዘ በኃላ ምንም እንደ ለላው ውሃ ጣዕምም የለውም ውሃ፣ ውሃ እራሱ አይልም፡፡ አፍ ውስጥ እንደ ውሃም አይከብድም፡፡ እናም ለካ እኔ ሳላውቅ ውሃ መስሎኝ ስጠጣው ቆይቼ ሀልኦ ብልቦ የአቦዬ ፀበል ተቆጥቶኝ ስጠጠው የነበረው ፊል ውሃ ሰውነተን አደረቀው፣ ቁስል በቁስል አደረገኝ በህልመም ላይ ወደኩኝ እዛው ከወላይታ ህክምና ቦታ ሰውነትህ ደም የለውም ደም ማነስ አለብህ ብሎኝ ምንም ሳይሻለኝ ወደ ቤተ ወደ ጸሣ ቀበሌ መጣሁ፡፡ በድጋም የሀልኦ ብልቦ አቦዬን ፊል ውሃ ፀበሉን ወስጀ በባህላዊ መንገድ ዶቻ ዶቻ ብዬ ስታጠብ ከሥጋ ዴዌዬ ዳንኩኝ! ታምሩ ብዙ ነው የዚህ ፊል ውሃ ፡፡ በማት ምስክርነቱን ተናገረ አርሶ አደሩ፡፡
ያግኙን
☏046-777-1536
ተዛማጅ ሊንኮች
Copyright © 2021-2025 Gofa Zone Adminstration.All Rights Reserved
Gofa,Ethiopia