ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ
አቶ አወቀ አለሙ
ራዕይ፣ ተልዕኮ፣እሴቶች፣ሥልጣንና ተግባር
ቀን 2022-01-12
ራዕይ “በ2014 የዞኑ ወጣቶች ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና፣ ፖለቲካዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ተረጋግጦ ስፖርትን ባህሉ ያደረገ ጤናማ ህብረተሰብ፣ መልካም ስብዕና ያለው ወጣት፣ ተወዳዳሪና ውጤታማ የሆኑ ስፖርተኞች ተፈጥረው ማየት፡፡ ተልዕኮ የዞናችን ወጣቶች ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ምቹ ሁኔታ በመፍጠርና ህዝባዊ መሰረት ያለውን ስፖርት በማስፋፋት የዜጎችን አካላዊና አእምሮአዊ ብቃት በመገንባት የዞንና የክልል ብልፅግና ማረጋገጥ፣ እሴቶች • አሳታፊነትና ፍትኃዊነት፣ • ግልጽነትና ተጠያቂነት፣ • ፈጠራን ማበረታታት፣ • ቅልጥፍናና ውጤታማነት፣ • የአገልግሎት ጥራት፣ • ለለውጥ ዝግጁነት፣ • በቡድን መስራት፣ • ህዝባዊነት፣ የወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ሥልጣንና ተግባር የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ህዝቦች ክልላዊ መንግሥት ስራ አስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 192/2014 መሠረት ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡- • የወጣቶች መብትና ጥቅም በማስከበር ዙሪያ ግንዛበና ንቅናቄ እንድፈጠር ያደርጋል • የወጣቶችን ሁኔታ የሚያመላክቱ ዝርዝር መረጃዎችን ይሰበስባል ያደራጃል በሚመለከታቸው ሁሉ እንዲታወቅ ያደርጋል • ወጣቶች በዞኑ የኢኮኖሚና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ለመሳተፍና ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችላቸው እድሎች የተመቻቸላቸው መሆኑን ያረጋግጣል • ወጣቶች እንደ ፍላጎታቸውና እንደ ችግሮቻቸው ተደራጅተው ለመብቶቻቸው እንድታገሉና ችግሮቻቸውን ማስወገድ እንዲችሉ ያበረታታል ሁኔታዎችን ያመቻቻል • ወጣቶች በልማት፣ መልካም አስተዳደርና ዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ላይ ንቁ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ስልት ይቀይሳል ድጋፍ ይሰጣል • የወጣቶች አደረጃጀቶችን አቅም ለማጎልበት የሚያስችሉ ጥናቶችን ያካህዳል፣ ስልጠናዎችን ይሰጣል፣ የስልጠና አገልግሎት የሚሰጥበትን አሰራር ያመቻቻል፣ ያስተባብራል • በዞናችን የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን ተግባራትን ያስተባብራል፣ ይመራል ፣ጥናት ያደርጋል በመላው ህዝባችን ዘንድ ባህል ሆኖ እንዲወጣ ጥረት ያደርጋል • ወጣቶች በስነምግባር የታነጹና አውንታዊ አመለካከት እንዲያጎለብቱ የስብዕና ግንባታ ስራዎች ይሰራል፣ያስተባብራል አሉታዊና መጤ ባህሎች እንዲጠበቁ ይሰራል • ወጣቶች ማዕከላትን በማስፋፋት ወጣቶች ተገቢውን መረጃ እንዲያገኙ እምቅ ችሎታቸውንና ዝንባለያቸውን እንዲያወጡበት ድጋፍ ያደርጋል፣ይከታተላል፣ ያስተባብራል • በዞኑ ለሚንቀሳቀሱ ስፖርት ማህበራት ፈቃድ ይሰጣል፣ ይሰርዛል፣ ፕሮግራማቸውን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል • የስፖርት ውድድሮች እንዲዘጋጅ ያደርጋል ያስተባብራል • በዞኑ ስፖርት ማህበራት መካከል የሚነሱ ክርክሮችን በስፖርት ምክርቤት እንዲዳኝ ያደርጋል • የባህል ስፖርት እንዲታወቅና እንዲዘወተር ያደርጋል • የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል • የስፖርት ትምህርትና ስልጠና እንዲስፋፋ ያደርጋል • በግል ለሚቋቋሙ የስፖርት ስልጠና ማዕከላት ፈቃድ ይሰጣል፣ ይመዘግባል፣ ይሰርዛል • ለስፖርት ልማት ዕድገት የሚሆን የገቢ ምንጭ እንዲፈጠር የተለያዩ ስልቶችን ይቀይሳል • ዞናዊ የውድድርና የስፖርት ማህበራት ደንብና መስፈርት ያዘጋጃል • የስፖርት ጉዳይን በሚመለከት መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ አካላት ጋር የሚደረጉ ግንኙነቶችን ያስተባብራል፣ • ዓላማውን ለማስፈፀም የሚረዱ ሌሎች ተግባሮችን ያከናውናል፡፡
ያግኙን
☏046-777-1536
ተዛማጅ ሊንኮች
Copyright © 2021-2025 Gofa Zone Adminstration.All Rights Reserved
Gofa,Ethiopia