ጎፋ ዞን ጤና መምሪያ
አቶ ማርቆስ ማኖቴ ጤና መምሪያ ኃላፊ
የሴክተሩ ራዕና ተልዕኮና እሴቶች
ቀን 2021-09-05
ተልዕኮ /mission • ባልተማከለና ዲሞክራሲያዊ በሆነ የጤና አገልግሎት ሥርዓት አማካይነት፤ በጤና ማበልፀግ፤ በመከላከል፤ በመሠረታዊ የፈውሰ ህክምናና በመልሶ ማቋቋም ላይ ያተኮረ የጤና አገልግሎት አጠቃላይ ፓኬጁ በመሰጠትና በመቆጣጠር፤ ህመምን (Morbidity)ሞትን (mortality) እና ሰንኩልነትን (disability)መቀነሰና የወረዳውን ህዝብ የጤና ሁኔታ ማሻሻል፡፡ ራዕይ (vision ጤነማ፤ ምርታማና የበለፀገ የወረዳው ሕብረተሰብ ተፈጥሮ ማየት እሴቶችና እምነቶች (core vaues) • ተገልጋይ ተኮር አሠራር እንከተላለን • ለሙያ ሰነምግባር ተገዥ እንሆናለን • ተቀናጁቶ በቡድን መሥራትን ባህላችን እናደርጋለን • ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት አሠራር እንከተላለን • መልካም አርአያ ሆነን እንገኛለን • በራሰ የመተማመን ባህል እናዳብራለን • አዳዲሰ ዕውቀቶችን መሻትን፤ መማርንና መለወጥን • ባህላችን እናደርጋለን
የጎፋ ዞን ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ
አቶ ተመስገን ጌታቸው ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ
የመምሪያው ራዕይ፣ ተልዕኮ እና እሴት
ቀን 2021-09-03
ራዕይ • በ2017 ዓ/ም የሥራ ሥምርት የተሰፋፋበት ፤ሠላማዊ የሥራ ሁኔታ የተረጋገጠበትና፤ የማህበራዊ ጥበቃ አገልግሎት የተሰፋፋበት ዞን ሆኖ ማየት ፤ የተቋሙ ተልዕኮ የሥራ ሰምርት አገልግሎት እንድሰፋፋ ፤የኢንዱሰትሪ ሠላም እንዲሰፋን ፤ የሠራተኛውን ጤንነትና ደህንነት እንድጠበቅ ፤የሥራ አካባቢዎች እንድሻሻልና ዜጎች ማህበራዊ ጥበቃ አገልግሎት እንድያገኙ ማድሪግ እሴቶች • ታማኝነት • ግልፅኝነትና ተጠያቂነት • ፋታዊነትና ዕኩልነት • አሳታፈነት • ተባብሮ መሥራት • ቀጣይነት ያለውን መሻሻል • በዕውቀት መሥራት • ውጤታማነት
ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት መምሪያ
አቶ አካሉ አምቦ ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ኃላፊ
ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት መምሪያ ኃላፊነትና ተግባር፣ ራዕይ፣ ተልዕኮና እሴቶች
ቀን 2021-09-22
• የዞኑ መንግስት ፐብሊክ ሰርቪስ ብቃት ያለውና ውጤታማ መሆኑን ያረጋግጣል፣ • የዞኑ መንግት ሠራተኞች ምልመላና መረጣ በብቃት ላይ የተመሠረተ እንዲሆን ያደርጋል፣ • የፐብለክ ሰርቪሱ የሰው ኃይል በቀጣይ በሚለማበት ጥቅም ላይ የሚውልበትን ስልት ይቀይሳል፣ ትግበራራዊነቱንም • ይከታተላል፣ • ለፐብሊክ ሰረቫንቱ በብቃትና በአፈፃፀም ውጤታማነት ላይ የተመሠረተ የክፍያና የማበረታቻ ሥርዓት እንዲዘረጋ ያደርጋል፣ ውጤታማነቱን ይገመግማል አስፈላጊውን የማሻሻያ እርምጃ ይወስዳል፣ • የዞኑ መንግስት ሠራተኞች ሥነ ምግባር መከታተያ ሥርዓት እንዲዘረጋ ያደርጋል፤ አፈፃፀሙንም ይከታተላል፣ • የዞኑ መንግስት ሠራተኞች አስተዳደር ህጎች በትክክል ሥራ ላይ መዋላቸውን ይከታተላል፣ያረጋግጣል፤ • የመንግስት ዘርፍ አቅም ግንባታ ሥራዎችን ያስተባብራል፣ የመንግስት ዘርፍ አገልግሎት በቀጣይነት የሚሻሻልበትና ውጤታማ የሚሆንበትን ስልት ይቀይሳል ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፤ ይገመግማል፤ • የዞኑ መንግስት መ/ቤቶች አደረጃጀት አግባብነትን ይመረምራል፣ በአደረጃጀት ማሻሻያ ጥናቶች ላይ አስፈላጊውን ድጋፍ ይሰጣል፤ • በዞኑ መንግስት መ/ቤቶች የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ ፣ የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ሥርዓት መዘርጋቱንና ተግባራዊ መሆኑን ያረጋግጣል፣ • የፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሀብት አመራርና የተቋማዊ መረጃዎች ሥርዓት በወጥነት እንዲዳበርና እንዲተገበር ያደርጋል፤ማዕከላዊ የመረጃ ምንጭ ሆኖ ያገለግላል፣ • የዞኑ የመንግስት መ/ቤቶችን የሰው ሀብት አስተዳደር በበላይነት ይመራል፣ የሥራ አመራር መመሪያዎችና አፈፃም መስፈርቶ ያዘጋጃል ያስፈፅማል፤ • የመንግስት ሠራተኞችን የደመወዝ የልዩ ልዩ አበሎችና ጥቅማጥቅሞች ማሻሻያ ያጠናል ሲፈቀድም ሥራ ላይ ያውላል፤ • በህግ መሠረት የክልሉ መንግስት ሠራተኞችን ከጡረታ ዕድሜ ክልል በአገልግሎት ላይ ስለማቆየት በሚቀረቡ ጥያቄዎች ላይ ውሳኔ ይሰጣል፣ • በየደረጃው የሚታዩ የመልካም አስተዳደርና የኪራይ ሰብሳቢነት ችግሮችን በጥናት መለየት ለተለዩ ችግሮች ስልት መንደፍ፣ የአፈታት ሂደት መከታተልና መደገፍ፣ የፋይዳ ጥናት በማድረግ የህዝብ እርካታን ማረጋገጥ፣ • የመንግስት ሠራተኞች አስተዳደር ፍርድ ቤት ያቋቁማል፣ያደራጃል፣አግባብ ባለው ህግ መሠረት እንዲመራ ያደርጋል፣ • ዓላማውን ለማስፈፀም የሚረዱትን ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡ ራዕይ፣ ተልዕኮና እሴቶች የተቋሙ ራዕይ • በ2017 ዓ.ም ተልዕኮውን በብቃት መፈፀም የሚችል በሥነ - ምግባሩ የተመሰገነ ሲቪል ሰርቪስ ተፈጥሮ ማየት፣ ተልዕኮ • በዞኑ የመንግስት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎችን በብቃት ለመፈፀም የሚያስችሉ አሠራሮችን በመዘርጋት የሠራተኛውን አመለካት በመለወጥና ብቃቱን በማሳደግ፣ ህዝብን በቅንነትና በታማኝነት የሚያገለግል ጠንካራና ውጤታማ ሲቪል ሰርቫንት መፍጠር ነው፡፡ እሴቶች • በዕቅድ መመራት • ተጠያቂነት • ውጤታማነት • ፈጣን ምላሽ መስጠት • በጋር መሥራት • ሁሌም መማር • አገልጋይነት • ምሳሌ መሆን • ወጪ ቆጣቢነት መሪ ማነው? /Who is a Leader?/ • መሪ ባለ ራዕይ ነው፣ • መሪ ሞዴልና ግንባር ቀደም ነው፤ • መሪ ለተልዕኮ ስኬት ዘወትር የሚተጋ ነው፣ • መሪ ተከታዮችን በአንድ ዓላማ በማሰለፍ ሠርቶ የሚያሠራ ነው፣ • መሪ የሚመራውን ተቋም ሥራና አሠራር ጠንቅቆ የሚረዳና ሌሎች ስለ ሥራና ተቋሙ ጠንቅቀው እንዲያውቁ የሚያደርግ ነው፣ • መሪ የማያውቀውን ከሌሎች ለመማርና ለመተግበር ዝግጁ የሆነ ማለት ነው፣ • መሪ የፈጠራ ሥራን የሚያበረታታ ነው፣ • መሪ ውጤታማነትን ለይቶ ዕውቅና የሚሰጥ ነው፣ • መሪ ለአቅም ግንባታ ተልዕኮ ስኬት ቅድሚያ በመስጠት የሚሠራ ነው፣ • መሪ አሳታፊ ነው፣ • መሪ የችግሮችን መንስኤ በማጥናት መፍትሄ የሚሰጥ ነው፣ " መሪነት ጥበብ ነው፡፡"
ያግኙን
☏046-777-1536
ተዛማጅ ሊንኮች
Copyright © 2021-2025 Gofa Zone Adminstration.All Rights Reserved
Gofa,Ethiopia