የጎፋ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ
አቶ ምስክር ምትኩ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ
የመምሪያዉ ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ ዓላማዎችና ዕሴቶች
ቀን 2021-07-05
ተልዕኮ ለዞኑ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ጉልህ አስተዋፅኦ የሚያደርጉ የሳይንስና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስራዎችን ለህብረተሰቡ በአግባቡ በማልማት፣ በመተግበርና በማስፋት ዞናዊ ብሎም አገራዊ የተወዳዳሪነት አቅምና በቴክኖሎጂ የዳበረ የአሰራር ስርዓት መፍጠር ነዉ፡፡ ራዕይ “በ2030 በዞናችን ውጤታማ የሆኑ የሳይንስና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂዎችን በፍጥነት የመማር፣ የማልማት፤ የማላመድ እና የመጠቀም አቅም ተገንብቶ ማየት” እሴቶች • በጎ ህሊናና ቅን ልቦና፣ • የስራ ፍቅርና ትጋት፣ • ያልተገደበ አስተሳሰብና ምናባዊ ጉዞ፣ • ለለውጥ በጋራ መስራት፤ • ውጤታችንም ሆነ ውድቀታችን የጋራችን ነው፤ • ችግር ፈቺነት፤ • የማይረካ የመማር ጥማት፤ • ለትውልድ የሚተላለፍ መሠረት፣ • ቀልጣፋና ውጤታማ አሰራርና ቀጣይነት ያለው መሻሻል፣ ተቋማዊ ፍልስፍና • ዕውቀት ሀብት ነው • ለአዳዲስ ሀሳቦች ዕውቅና እንሰጣለን • ትጋት የአዎንታዊ ለውጥ ሀይል ነው • ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን የአዲሱ ትውልድ ቋንቋ ነው • ኢኖቬሽንን ማበረታታት ለትውልድ ተስፋን መመገብ ነው • የዘመነ ዲጅታል ኢኮኖሚ የዕድገታችን መሰረት ነው
የጎፋ ዞን ትምህርት መምሪያ
አቶ አሸብር ብርሐኑ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ
የመምርያዉ ዓላማ ፣ራእይ፣ ተልዕኮና ዕሴቶች
ቀን 2021-09-10
የትምህርት መምሪያው ራዕይ በ2020 ዓ/ም በመምሪያው ፍትሃዊነቱና ጥራቱ የጠበቀ ትምህርትና ስልጠና በማዳረስ በዕውቀት፣ በክህሎትና በአመለካከት የተስተካከለና ለልማት፣ ለፍትህ፣ ለሰላምና ለዴሞክራሲ ግንባታ የላቀ ሚና የሚጫወትና በገበያ ላይ ብቁ ተወዳዳሪ የሆነ ትውልድ ተፈጥሮ ማየት፤ የትምህርት መምሪያው ተልዕኮ በመምሪያው የተፋጠነ ቀጣይነት ያለው ዕድገትና ልማት እንዲመጣ ዴሞክራሲያዊ ባሕል እንዲዳብር ፍትሃዊነቱ፣ ተገቢነቱ የተረጋገጠና ጥራቱ የተጠበቀ የትምህርት አገልግሎት በማዳረስ ክህሎቱ፣ እውቀቱ እና አመለካከቱ የተስተካከለ ትውልድ ለመፍጠር መደበኛና መደበኛ ያልሆነ የትምህርትና ስልጠና ፕሮግራሞችን በመጠቀም፣ ትምህርትና ስልጠናን በቴክኖሎጂ እንዲሁም በጥናትና ምርምር በማስደገፍ፣ ህብረተሰቡን በባለቤትነት በማሳተፍ፣ አጋር ድርጅቶችን በማስተባበርና የተገኘውን ሃብት በአግባቡ በመጠቀም ትምህርትን ለዜጎች ሁሉ ተደራሽ ማድረግ ነዉ፡፡ እሴቶች • ለሙያዊ ሥነ-ምግባር እንገዛለን • ለጊዜ ዋጋ እንሰጣለን • በሥራ ክቡርነት እናምናለን • ተገልጋዮችን በቅንነት እናገለግላለን • ሙስናን እንጠየፋለን እንዋጋለን • የለውጥ ሀዋሪያ እንሆናለን • ሁሌም እንማራለን
የጎፋ ዞን የባህልና ቱሪዝም መምሪያ
አቶ ኒከሰን ለማ የባህል ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ
የመምርያዉ ዓላማ ፣ራእይ፣ ተልዕኮና ዕሴቶች
ቀን 2021-09-11
የሴክተሩ ራዕይ በ2022 የባህልና ቱሪዝም ዘርፍን በማላቅ ከቀዳሚ የዞን ብልፅግና መሠረቶች አንዱ ማድረግ፣ ተልዕኮ የጎፋና የኦይዳ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ባህላዊ እሴቶች፣ ታሪካዊና ተፈጥሯዊ መስህቦችን/ቅርሶችን በማጥናት፣ በመጠበቅ፣ በማልማትና በማስተዋወቅ፤ የህብረተሰቡን አብሮ የመኖር፣ የመቻቻልና የመደጋገፍ ባህልን በማጎልበት፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓታችንን በማዘመን ዞናችን በስፖርት ዘርፍ ያለውን እምቅ አቅም በህብረተሰቡና በባለድርሻ አካላት ተሳትፎ በላቀ ደረጃ በማሳደግ እና መልካም ገጽታ በመገንባት የክልላችንና ብሎም የአገራችንን ዘላቂ የሆነ ማህበራዊና ምጣኔ ሃብታዊ ብልፅግና ማረጋገጥ፡፡ እሴቶች • ብዝሀነትን ማክበር • እንግዳ ተቀባይነት • ግልጽነት • ተጠያቂነት • ለለውጥ ዝግጁነት • የላቀ አገልግሎት • አሳታፊነት • ህዝባዊነት • ፈጠራን ማበረታታት • ቅልጥፍናና ውጤታማነት • የአገልግሎት ጥራት • በቡድን መስራት
ያግኙን
☏046-777-1536
ተዛማጅ ሊንኮች
Copyright © 2021-2025 Gofa Zone Adminstration.All Rights Reserved
Gofa,Ethiopia