የጎፋ ዞን የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
አቶ ብርሐኑ ደቻሳ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ
ተልዕኮ የተቋሙ ራዕይ እሴቶች
ቀን 2021-09-10
ተልዕኮ ሁሉአቀፍና አዳዲስ የኮሚዩኒኬሽን መገናኛ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ለህብረተሰቡ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማቶችን እንዲሁም የኢንቨስትመንት መረጃዎችን የሚሰጥ በጥናትና ምርምር የታገዘ አካታች የኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ምቹ አካባቢ መፍጠር ነው፡፡ የተቋሙ ራዕይ በ2025 በመረጃ የበለጸገ እና በሀገሩ ላይ መልካም ገጽታን የተጎናጸፈ ዜጋ ተፈጥሮ ማየት፤ እሴቶች • ቅንነት • ታማኝነት • ተጠያቂነት • የላቀና አሰተማመኝ አገልግሎት መስጠት • የፈጠራና የሀሳብ አመንጭነት አቅምን ማዳበር • አክብሮትና አንድነት • በሀሳብ አሸናፊነት ማመን • ትብብርና የቡድን ስራ • የአመራር ብቃት • ኃላፊነትን መውሰድ
የጎፋ ዞን ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና መምሪያ
አቶ አብርሃም አልዬ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና መምሪያ ኃላፊ
የጎፋ ዞን ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና መምሪያ ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ ዓላማ
ቀን 2021-09-10
የጎፋ ዞን ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና መምሪያ ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ ዓላማ፡- ራዕይ • በዞናችን ለሀገሪቱ ኢኮኖያዊና ማህበራዊ ዕድገት አስተዋጽዖ የሚያበረክት ብቁና በሙያ የሚተማመን ዜጋ በማፍራት የህዝቡ ኑሮ ደረጃ ተሻሽሎና ቀጣይነት ባለዉ ሁኔታ ድህነት ጠፍቶ ማየት፤ ተልዕኮ • በሥራ ላይ የገበያ ፍላጎት ጥናት ላይ የተመሠረተ ተለማጭ የሆነና ውጤትን መሰረት ያደረገ የተቀናጀና የተዋሀደ ስልጠናን በመስጠት ኢንዱስትሪዉም በስልጠና ሂደት ኢንዲሳተፍ በማበረታትና የቴክኖሎጂ ፍላጎት ለመሙላት ስራ ፈጥሮ /ተቀጥሮ/ ራሱን ማስተደዳር የሚችል ከመሰረታዊ እስከ መካከለኛ ደረጃ የሰለጠነ የሰዉ ኃይል በብቃትና በብዛት በማፍራት በዞኑ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ዕድገት አስተዋፅኦ ማድረግ፡፡ ዓላማ • ገበያው የሚፈልገውን ብቃት ያለው፣ተነሳሽነትና የሙያ ስነምግባር የተላበሰና ስራ ፈጣሪ በመሆን የኢኮኖሚውን ዕድገትና ልማት የሚያራምድ የሰው ኃይል መፍጠርና ድህነትን ከዞናችን ብሎም ከክልላችን በመቀነስ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት አስተዋጽኦ ማድረግ፣ መርሆዎች የሴክተሩ አራቱን አብይ የትኩረት መስኮች በማሳካት ሂደት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ሥርዓቱ የሚመራበት መርሆዎች ያሉት ሲሆን እነዚህም፡- ተቋማት የቴክኖሎጂ ማቀበያና ማሸጋገሪያ ማዕከላት እንዲሆኑ ማድረግ፣ • በገበያ ፍላጎት የሚመራ ስልጠና እንዲኖር ማድረግ፣ • ተቋማት ብቁ የሰው ኃይል መፍሪያና የአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት መፈልፈያ እንዲሆኑ ማድረግ፣ • ከቴክኖሎጂ እድገት ጋር ራሱን የሚያስተካክል የሥልጠና ሥርዓት መዘርጋት፣ • ተለማጭ የሆነ የትምህርትና ሥልጠና ሥርዓት መዘርጋት፣ • ያልተማከለ ሥርዓት መዘርጋት፣ • የተቀናጀና የተዋሃደ ሥርዓት መዘርጋት፣ • የትብብር ሥልጠናን ማስፋፋት፣ • የባለድርሻዎችን ተሳትፎ ማሳደግ… እሴቶች፡- • ሥራ ፈጣርነት • በገበያ መመራት • ብቁ ተወዳዳሪነት • በህብረት የመስራት ባህል • ቀና አመለካከት • ሰዓት አክባርነት • ጥራት ያለዉ ትምህርትና ሥልጠና ናቸዉ፡፡
የጎፋ ዞን ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ መምሪያ
ወ/ሮ ፋንታዬ ወላ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ
የጎፋ ዞን ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ መምሪያ ራዕይ ተልዕኮና እሴቶች
ቀን 2021-09-07
የሴክተሩ ራዕይ በ2013 ሴቶችና ወጣቶች በኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና በባህል መስኮች እኩል ተሳትፎና ተጠቃሚነት የተረጋገጠባት፣ የህፃናት መብትና ደህንነት የተከበረባት፤ የህፃናትና የወጣቶች መልካም ስብዕና የጎለበተባት እና የስርአተ-ጾታ እኩልነት የሰፈነባት የዳበረዴሞክራሲያዊ ህብረተሰብ ተገንብቶ ማየት፡፡ የሴክተሩ ተልዕኮ የሴቶችንና ወጣቶችን በልማት፣ በመልካም አስተዳደርና በዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ እኩል ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ፤ የህፃናትን መብትና ደህንነት ማስጠበቅና የፆታ ዕኩልነትን ማስፈን፡፡ • ለዚህም ተፈፃሚነት፡- • የግንዛቤና ሁሉን አቀፍ ንቅናቄ መፍጠር፣ • ሴቶች፣ ህፃናት እና ወጣቶች እንዲደራጁ ምቹ ሁኔታ መፍጠርና ማብቃት፣ • በህጎች ፖሊሲዎችና የልማት ፕሮግራሞች የሴቶች፣ ህፃናት እና ወጣቶች ጉዳይ መካተቱንና መፈፀሙን ማረጋገጥ፤ ማስተባበር፣ ክትትል ማድረግና ድጋፍ መስጠት፣ • የሴቶች ልዩ ድጋፍ እርምጃዎች መፈፀማቸውንና ሴቶች በውሳኔ ሰጪነት ቦታ መመደባቸውን ማረጋገጥ • የህጻናትና የወጣቶች ስብዕና መገንባት • በቤተስብ ደረጃ ሴቶችን ውሳኔ ሰጪነት ብቃት ማጎልበት • የሴቶችና የወጣቶች የልማት ፈንድ በማቋቋም ተጠቃሚነታቸውን ማሳደግ የሴክተሩ እሴት፡- • አሳታፊነትና ፍትሃዊነት፣ ቅልጥፍናና ውጤታማነት • የአገልግሎት ጥራት፣ የቡድን ስራ • በዕቅድ መመራት፣ ወጪ ቆጣቢነት • ግልፀኝነትና ተጠያቂነት፣ ፈጠራ • አገልጋይነት ናቸው የሴክተሩ ዓላማ • የወጣቶች ሁለንተናዊ ብቃት በማጎልበት በፖለቲካ በእኮኖሚና በማህበራዊ መሰኮች እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ በዞኑ ንቁ ተሳትፎ እንድያደርጉ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር የራሳቸዉን ሚና እንድያበረክቱ ማስቻል፡፡
ያግኙን
☏046-777-1536
ተዛማጅ ሊንኮች
Copyright © 2021-2025 Gofa Zone Adminstration.All Rights Reserved
Gofa,Ethiopia