ባህላዊ የምግብ ዓይነቶች
ቀን 2021-09-08
ሀ/ ሸንደራ/Dhote (shendera):- ከበቆሎ ዱቄት በቅቤና በቅመማ ቅመሞች የሚዘጋጅ ባህላዊ ገንፎ ነዉ ለ/ ኡከታ/uketha ፡-ይህ ከበቆሎ፣ ከጤፍና ማሽላ ዱቄት የሚዘጋጅ ባህላዊ ቂጣ ነዉ፡፡ ሐ/ህጭቆጫ/ hiciqqoca፡- አዘገጃጀቱም ሥጋ ቆርጠዉ ከቆጮ ጋር በማድረግ የሚበላ ባህላዊ ምግብ ነዉ መ/ ሱልሶ/sulsso፡- ሥጋን ጎረድ ጎረድ አድርጎ በመክተፍ በበቂ ሁኔታ ማጣፈጫ ቅመሞችንና ቅቤ በመጨመር የሚዘጋጅ ነዉ፡፡ ሠ/ ባጭራ/baacira፡- በዓይብ ላይ ቅቤ፣ቅመምና ነጭ ሽንኩርት ገብቶበት የሚዘጋጅ ነዉ፡፡ ረ/ ቦዬ ሆቶልሳ/boye hotolssa፡- ቦዬ ተቀቅሎ ቅመም ገብቶበትና በቅቤ ተለዉሶ በርበሬ ተጨምሮበት የሚበላ ነዉ፡፡ ሰ/ ኮሰ/koose፡- ከቡላ የሚዘጋጅ ባህላዊ ምግብ ነዉ፡፡ ሸ/ ቅንእሻ/qin77isha ganzilla፡-ከአተር፣ከስንዴና ከበቆሎ ዱቄት የሚዘጋጅ ምግብ ነዉ፡፡ ይህም በዛ ላሉ ሰዎች በገበታ ተደርጎ የሚቀርብ ነዉ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ሌሎችም ባህላዊ ምግቦች Ayibiza(posose)፣bibe፣boye፣cadhe፣picata፣diqqe፣shuncha፣Dhuppe ተብለዉ ይጠቀሳሉ፡፡
ባህላዊ የጦር (toora)መሳሪያዎች እና ግልጋሎታቸዉ
ቀን 2021-09-02
የጎፋ ህዝብ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን እንደየዓይነታቸዉ ለተለያዩ አገልግሎቶች በተለያየ ግዜና ሁኔታ አዘጋጅቶ በመጠቀም ይታወቃል፡፡ ባህላዊ ጦር መሳሪዎች በተለያዩ አዉዶች እንደ አጠቃቀሙ ከበረታ፤ መልካም ስምና ሞገስ አለዉ፡፡ በመሆኑም ባህላዊ ጦር መሳሪያዎቻችን በስሞቻቸዉ መቸና የት ጥቅም ላይ እንደምዉሉ ከዚህ እንደምከተለዉ ለማቅረብ ተሞክሯል፡፡ 1.ጋንችሬ ቶራ (ganchchire toora)-ተሰክዉ ብረት ብዙዉን ጊዜ የመስፋት ሁኔታ ያለዉ ስሆን ህዝቡ ያፈራዉን ሀብት ና ንብረት ከአደጋ ና ከስርቆት በአብዛኛዉ ለመጠበቅ የምገለገልበት ባህላዊ ጦር መሳሪያ ነዉ ፡፡ 2.ዋሌ ቶራ(walle toora)-ጫፍ ብረቱ ጠፍጣፋ ስሆን በአደን ጊዜ በአብዘኛዉ ከርከሮ ለመግደል ጥቅም ላይ ይዉላል፡፡ 3.ማጫሜ ቶራ(maccaame toora)-ጫፍ ብረት ዓይነቱም በአብዛኛዉ በሁለቱም በኩል እንደ ጆሮ ያለ ነገር ይበጅለታል፤ በዚህም አደን በምወጣበት ጊዜ ከዱር እንሳሰት ነብር ለመግደል የምጠቀምበት፡፡ 4.ካጫቶራ(kaaca toora)- ይህ ባህላዊ ጦር ብዙዉን ጊዜ ለወንድ ልጅ በልጅነቱ ከአባት የምበረከት ስሆን፤ይህ የምያመለክተዉ በማናቸዉም ከባድ ሁኔታዎች ዉስጥ በጀግንነት ና በብርታት ነጥሮ እንድወጣ የምያስችል የሞራል ስንቅ ለማላበስ ነዉ ፡፡ 5.ኦርጎቶ ቶራ(orgoto toora)-መያዣ እንጨቱ አጠር ያለ ሆኖ በጫፉ ተሰኪ ብረት ያለዉ ስሆን ምዳቆ አዲኖ ለመግደል ይጠቀሙበታል፡፡ 6.ቦንጆ ቶራ(bonjo toora)- ለአደን ተግባር እንጨቱ ወፍራምና ብረቱ ጠንካራ ሆኖ የምዘጋጅ ስሆን ዝሆንን አድኖ ለመግደል የምጠቀሙበት ነዉ፡፡ 7.ሸለሌ ቶራ(shellele toora)-መያዣ እንጨቱ እንድለመጥ ተደርጎ ሚዘጋጅ ስሆን በለቅሶ ጊዜ ለፉከራና ሽለላ የምጠቀሙበት ነዉ፡፡ 8.ጽንቃ ቶራ(xinqa toora)-ባህላዊ ጦር መሳሪያዉጫፍ ብረቱ የመርዘም ሁኔታ ና የመምዘግዘግ ባህርይ ያለዉ ሆኖ አሳማ አድኖ ለመግደል ይጠቀሙበታል፡፡ 9.ቦዶ ቶራ(bodo toora)-ይህ ባህላዊ ጦር መሳሪያ በቤት ዉሰጥ በክብር የምቀመጥ ናበወሳኝ ግዜም ለምወዱት ና ለምያከብሩት ሰዉ በተለይም ለአማች በክብር የምሰጡት(የምያዉሱት) ባህላዊ ጦር መሳሪያ ነዉ፡፡ 10.ዙሎ ቶራ(zuulo toora)-ይህን ባህላዊ ጦር መሳሪያ አንዳንዶች ለአያያዝበምመች ሁኔታ በማሰራት ካልተጠበቀ ጠላት ራስን ለመከላከል ከእጅ የማይጠፋ ባህላዊ ጦር መሳሪያ ነዉ፡
የጎፋ ህዝብ ለቅሶ ባህል
ቀን 2021-09-03
የጎፋ ብሔረሰብ ከለሎች ብሔረሰቦች የሚለይበት የራሱ የሆነ ለቅሶ ባህል አለው ፤ለቅሶ አብሮ የኖረ ዘመድና ወዳጅ ሲሞት ሐዘን የሚገልጽበት ሂደት ነው፡፡አንድ በሽተኛ በሕይወት እንደማይቆይ ሁነታውን አይተው አዋቅዎችና ሽማግሌዎችን የበሽተኛውን ቤተሰብ ራሱን እንድያዘጋጅ ያሳስባሉ፡፡ከዚያም ቤተሰብ የለቅሶ ቅደመ ዝግጅት ያደርጋሉ፡፡ቅድመ ዝግጅቶቹም ለምግብና ለመጠጥ የሚያገላገሉ የእህል ዓይነቶች መግዛት ማስፈጨት ለ‹ፓርሶ› ወይም ‹ቦርደ› የሚሆን ቁሳቁስ ማሟላት የማገዶ እንጨት ማዘጋጀት ወዘተ ያጠቃልላል፡፡ በመቀጠል መልዕክት /keeza/ መላክ ይኖራል፤ይህም ሩቅ ለሚገኝ ቤተዘመድ የምላክ መልዕክት ሲሆን ሰውየው ከሞተ በኋላ እገሌ በጣም ታሟል በነፍስ ድረሱ ራሳችሁንም አስባችሁ ተብሎ ይነገራል፡፡ የአለቃቀስ ሁነታዉም ሂደቱንና ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ የምፈፀም ይሆናል፡፡ የለቅሶ እወጃ ለቅሶውን ለማወጅና ይፋ ለማድረግ የተለያዩ መሣሪያዎችን ይጠቀማሉ ለአካባቢው የቅርብ ጎረቤት የሆኑ ሰዎች ሌሊት ጥሩንባ ሲነፋና ዳርቤ ሲመታ በመስማት በአካባቢያቸው ታሞ የነበረው ስው ስለሚገምቱና ጠይቀው በመረዳት ወደ ለቅሶው ለመምጣት ይዘጋጃሉ፡ የለቅሶ አለቃቀስ ሥርዓት፤ የለቅሶ አለቃቀስ ሥርዓት እንደሟች ዕድሜ፤ፆታና ማህበራዊ ከበረታ ይለያያል ፡፡ ለምሳሌ፤- ለህፃን፤ወጣት፡ ጎልማሳ ፤ሽማግሌ፤አለቃ፤ ባለአባትና ለጀግና የሚለቀስ ለቅሶ አንድ አይነት አይደለም ፡፡ ይህም ማለት ለቅሶው የሚወስደው ጊዜ፤የሀዘኑ ክብደትና ቅለት ፤የቅድመ ዝግጅቱ ሁኔታ ይለያያል፡፡ለቅሶ ተጀምሮ እስከ እስኪፈፀም ድረስ እንደ ሟቹ ሁኔታ ከሁለት እስከ አምስት ቀን ሊቆይ ይችላል፡፡ምክንያቱም ከርቀት የሚመጡ ዘመዶች እስኪደርሱ ሌላው ምክንያት ደግሞ እንደሟቹ ሁኔታ ለለቅሶ እንድደምቅ ታስቦ ነው፡፡ የህፃን ልጅስሞት የሚለቀስ ለቅሶ ሟቹ አንድ ወርእና ከዚያ በታች ከሆነ በደንብ አይለቀስም፡፡እንደሞተ ወድያውኑ እንድቀብር ያደርጋል፡፡ የቀብሩም ቦታ ጓሮ ወይም እንሰት ውስጥ ነው፡፡ወደ ወላጅ እናት ለማፅናናት የምመጡ ሰዎች “እርጥብ ሳር ና ቅጠል(dal7isha maata) በመያዝ “ማህፀንሽ ይለምልም፤የሚያድግ ልጅ ይስጥሽ”በማለት ስያፅናኑ ከተወሰኑ ቀናቶች በኃላ ፀጉሯ ላይ ቅቤ ይደረግና ሀዘኑ ያበቃል:: ወጣት ስሞት የሚለቀስ ለቅሶ ለአካለ መጠን የደረሰና ዕድመዉ ከ18ዓመትበላይ የሆነወጣትስሞትለቅሶዉከ3 እስከ 4ቀንይፈጃል፡፡አለቃቀሱም በጣም ከባድናመራራ ነዉ::ስያለቅሱም ሰዉነታቸዉን በተለያዩ ነገሮችማለትም፦በጦር፣በምላጭ፣በድንጋይ እናበመሳሰሉት ነገሮች ግንባራቸዉን፣ጉንጫቸዉን ፣ሆዳቸዉንና ጀርባቸዉን ያደማሉ፤ፀጉራቸዉንምይላጫሉ በእንብርክክ መሄድ መዉደቅና በመሬት መንከባለል የተለመዱ ናቸዉ። ሴት አልቃሾችም ጦር ባይዙም በቆንጥር ፈታቸዉንና እራሳቸዉን ያደማሉ። በአለቃቀስ ሂደት ከላይ በሱዉነት ላይ የምታዩ ጎጅ ድርግቶች የማይደገፉ ልማዳዊ ስርዓቶች በመሆናቸዉ እየቀነሰና እየቀረ የመጣ የለቅሶ ስርዓት ነዉ፡፡ ጎልማሳስሞት የሚለቀስ ለቅሶ ሟች አባወራና ጎልማሣ ከሆነ የሚደረግለት ለቅሶ ሐዘን ከወጣቶች ጋር የሚቀራረብ ነዉ። ለጎልማሳዉ እንደማንኛዉም ለቅሶ ቅድሜ ዝግጅት ከተደረገበኋላ ለቅሶዉ ስጀምር አባወራ መሆኑን ለማሳወቅ የተለያዩ ምልክቶች ይደረጋሉ ። ለምሣሌ፤- በቤቱ ጣሪያ ላይ ቡሉኮ፣ጋቢ፣ጦር፣ጋሻ፣የመሳሰሉት የሰዉዩዉ ንብረቶች ይቀመጣሉ። ዓላማዉም ከዉጪ የሚመጣ አልቃሽ የሟችን ማንነት በቀላሉ እድያዉቁት ይረዳል። በለቅሶ ወቅት የሟች ታላቅ ልጅ የሚይዘዉ ጦር ከጫፉእንድቆለመም ይደረጋል። ከቤቱ ጣሪያ ላይም ቤቱ የተከደነበት ሣር እየተነቀለ ጣሪያዉ ባዶ እስኪሆን ድረስ ይበተናል።የሟች ፈረስ ወይም በቅሎ ካለ ነጠላ ለብሶ አንድ ቦታ እንዲቆም ይደረጋል። ሥነ-ቃሎች Gadiyan laggiyan erettidayso bade ! በአካባቢውና በህብረተሰቡ በጓደኞችህ የተወደስክ ወይኔ ! Asappe Aadhdha aqidaysso bade ! ከሰው ሁሉ በልጠህ የኖርክ ወይኔ ! Paydin wurenna shalo Godaw ! ተቆጥሮ የማያልቅ የሀብት ጌታ ወይኔ! ሽማግሌ ስሞት የሚለቀስ ለቅሶ ሟች በዕድሜ የገፋ ሽማግሌ ወይም አሮጊትከሆነ/ች እንደ ወጣትና ጎልማሣ ምርር ያለ ለቅሶ አይኖርም፡፡በለቅሶ ወቅት ራስን መጉዳትም አይኖርም፡፡አለቃቀሱም የደስታ ያህል ሲሆን ጥንት ሰውዬው /ሴትዮዋ/የሰሩት ገድል እየተወሣ ይለቀሳል፡፡ ለለቅሶ ወቅት አለባበስ አቀማመጥና የለቅሶ አገባብ ሁኔታ በለቅሶ ወቅት የሟች ቤተሰብ ወይም የቅርብ ሰው ሁሉ በለቅሶው ቦታ አይጠፋም፡፡ሁሉም አንድ አከባቢ ሆነው የሚመጣውን ለቀስተኛያስተናግዳሉ፡፡አቋቋማቸው፤አቀማመጣቸው ለሟች ያላቸውን ቅርበት የሚገልፅ መሆን አለበት፡፡ ለምሳሌ፤-ሟች የቤቱ አባወራ ከሆነ የመጀመሪያ ሚስት በአንድ ወገን ወንድ ልጆች በሌላወገን ይሆኑና በሚስት በኩል ሌሎች ሴት ዘመዶች በወንድ ልጆች በኩልም እንደዚሁ ወንድ ዘመዶች በዕድሜና በዝምድና ቀረበታ መሠረት በቅደም ተከተል በተርታ በመቆም /ደራ/ በተለዬ ሁኔታ የሚመጣውን ለቀስተኛ ያስለቅሱታል፡፡ ይህ አቋቋም የሚጠቁመው ለቅሶ መድረስ እንደ ትልቅ ማህበራዊ ግደታና ውለታ ስለምቆጠር ማን ለቅሶ እንደደረሰና እንዳልደረሰለመቆጣጠርም ጭምር ነው፡፡የለቅሶ ወቅት አለባበስ ከወገብ በላይ ራቁት ይሆናል፡፡ከወገብ በታች የተለያየ ዓይነት ልብሶች ይለበሳሉ፡፡ ከወገብ በታች ለመታጠቅም፤ቡሉኮ የመሳሰሉት ይገኛሉ፡፡ለቀስተኞች ከውጪ ስመጡ ነጠላቸውን በወገባቸው ላይ አሸርጠዉ ይገባሉ፡፡ አሁን አሁን ግን ከወገብ በላይ ራቁት መሆን ቀርቶ በውስጥ ሸምዝ መሰል ነገር መልበስ እየተለመደ መጥቷል፡፡ አልቃሾች ከውጪ ወደ ለቅሶ ስገቡ እንደ አመጣጣቸው፤አገባባቸው ሊለያይ ይችላል፡፡ ሰውለቅሶ ሊደርስ ስመጣ ሁለት እጅ ወደ ላይ በማንሳት እየሮጠ ታናሞ!ታናሞ!እኔን!እኔን!እኔን! እያሉ መጥቶ አልቃሹ አከባቢ ሲደርስ አክሮባት መልክ ወደ ላይ ዘሎ በመሬት ላይ በመውደቅና ሰውነቱን በመጉዳት ሐዘኑን ይገልፃል፡፡(ምንጭ፤-የጋሞ ጎፋ ዞን የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶች መጽሐፍ፡በጋ/ጎ/ዞ/ባ/ቱ/መ/ኮ/መምሪያ፡በባ/ታ/ቅ/ጥ/ል/ዋ/ስ/ሂደት የተዘጋጀ፡ገፅ 131፤ከልዩ ልዩ ያልታተሙ ፅሑፍ ዉጠቶች እና ከዕድሜ ባለፀጎች ጋር በተደረገ ቃለ ምልልስ) በለቅሶ ግዜ መገልገያ ቁሳቁሶች ጦር፤ቁስቴ፤ጉቼ፤ዳርቤ፤ዳባላ ዳንጮ፤ማዳ ናቸዉ፡፡ የለቅሶ አገባብ ሥርዓቶች Wasso----goyro/saba-------diishsho-------goyro/pargulssi------olliza-----share የመቃብር አቆፋፈር ዓይነቶች ኡዱላ ዱፎ(Udulla duufo)-የቃሊቻ ዘር ሀረግ ያላቸዉ መቃብር ሸጴ(Shephe (qota))- የገንዘብ አቅም ያላቸዉ መቃብር ዎንግሬ(Wongire (qore))-ዝቅተኛ ገቢ ያላቸዉ መቃብር ናቸዉ የመቃብር ቦታዎች ስያሜs ጎራ(Gora)-የማላ መቃብር ሆኖ እንደ ጎፋ የአይካ ና ጎሻና ዘር ሀረግ መቃብር ነዉ፡፡ ማካና(Makana)-የቃሊቻ ዘር ሀረግ መቃብር ስፍራ ስያመ ነዉ፡፡ ደረ ዱፎ(Dere duufo)-በዓይነት ና በቁጥር የበዛዉ የዶጋላ ዘር ሀረግ መቃብር ነዉ፡፡ ማና ዱፎ(Mana duuffo)-የዕደ-ጥበብ ባለሙዎች መቃብር ተብለዉ ይታወቃሉ፡፡
ያግኙን
☏046-777-1536
ተዛማጅ ሊንኮች
Copyright © 2021-2025 Gofa Zone Adminstration.All Rights Reserved
Gofa,Ethiopia