ባህላዊ መድኃኒት
ቀን 2021-09-03
ባህላዊ መድኃኒት ህክምና የሚደረግላቸው በሽታዎች ስያሜ፡- ቁርጥማት፣ ተቅማጥ፣ ስብራት፣ ወለምታ፣ ወባ፣ የዓይነ ጥላ ቁስል የሆድ መነፋት በሽታ ለተለያዩ በሽታ የሚውል መድኃኒቶች ስያሜ ጤና አዳም፣ፌጦ፣ወንቆቆ፣የግራዋ እንቡጥ፣ሳአ ሻራ፣የወይባ ላጊ፣ቅቤ፣የበሬ መቅኔ፣አንቺ ዓይፌ፣ ማልዶ ማታ፣የሀለኮ ስር፣ከዛንጋዳ እና ቆጮ በጋራ ታምሶ የሚዘጋጅ ጩቁነ፣ሎሜ፣ አይዳሜ፣ሂግሻ ጣሌ፣ ጎሎ ሽአ፣ኦይሳ፣ፃሌ፣ጫላ፣ቦርሲ፣የዶሮ ኩስ፣ጣሌ፣ አልተቴ፣ማቃዶ፣ታልባ፣ቱሞ፣ጋጋፋ ወዘተ…. የመድኃኒቱ አጠቃቃም ዘዴ ፡- ለተቅማጥ፡- ዘንጋዳ እና ቆጮ በአንደነት ተፈጭቶ ታምሶ የተዘጃውን ስበሉት ተቅማጡም በቀላሉ ይስቆማል፡፡ ለድንገተኛ ሆድ በሽታ ወይም ማሎ፡- ሳአ ሻራ ተወቅጦ ተጨምቆ ይጠጣል፡፡ ለሆድ መንፋት ችግር፡- አንቺ አይፌ ቅጠል ተወቅጦ ጨማቂው በቡና ይጠጣል፡፡ ጤና አዳም ከአርቲ ጋር እንዲሁ ተዘጋጀቶ ይጠጣል፡፡ ከሆድ የኮሶ ትል ለማስወገስ፡- ወንቆቆ/እንቆቆ እና የሼሽ ፃጶ በአንድነት ተወቅጦ ጨምቂው ይጠጣል፡፡ የመድኃኒቶቹ አጠቃቀም አሁን ያለበት ደረጃ በአብዘኛው ለምሳሌ፡- የባህል መድኃኒቶች ፈዋሽነታቸው ቀላል ስላይደለ የመጠቀም ሁኔታ ቢኖርም አሁን እየቀነሰ ነው፡፡ የበሽታው መድኃኒት አጠቃቀም ዕውቀት ወደ የሚቀጥለው ትወልድ የሚተላለፍ ከሚያዩት እምነት ነው፡፡
ባህላዊ እምነት
ቀን 2021-09-03
የባህላዊ እምነት ዓይቶች፡- ፆሳ፣ቃዳ፣ያርሾ ኮራ፣ማጆ ማራሞ የባህላዊ እምነቶች የሚወሱበት ጊዜ ባህላዊ እምነቶች የሚውሉበት በሰንቤት ቀን ሲሆን አብዘኛው ጊዜ ቃዳ ቃማ ግለሰቤ የተወለደበት ዕለት የሚፈፀም በመሆኑ በዕለቱ ይከናወናል፡፡ ለልዩ ልዩ እምነታዊ ሥራዓቶች የሚደርጉ ድርጊትን በተመለከተ ይርሾ፡- ፍየል ይታረዳል፣ቦርዴ ከተለያዩ ዕህል ዓይነቶች ይዘጋጃል፣ወለላ ማር ቦታው የሚረጩበት ይሆናል፡፡ ባህላዊ እምነቱ አሁን ያለበትን ሁኔታ ስንመለከት እየጠፋ ነው ማለት እንችላለን ለምን ቢባል አሁን ላይ የተለያዩ እመነት ተከታዮች ባህላዊ ሥራዓቱን ካለመቀበላቸው የተነሳ የለም ማለት ይቻላል፡፡ ለምነቱ የሚጠቀሙበት ማቴሪያል በተመለከተ፡- አድባር የተለያዩ የምግብ ማብሰያዎችና መመገበያዎች፣ የእርድ ቢላዎች፣ የቦርዴ መጠጫ ዕቃዎች ይዘጋጃሉ፡፡ ባህላዊ እምነት ከአስተዳደራዊ ሥራዓት ጋር ያለው ቁሩኝት ሰው በባህሉ እምነት ፍራሃት ስላለው በጊዜው የሚፈፀም ጥፋት ለማጋለጥ አያስቸግርም፡፡ የዋሼ እንደ እምነቱ ይሞታል ተብሎ ስለምታመን ነገሮችን በግልጽ በመናገር ለውሳነ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡ በተለይ ማመንዘር፡- ለሞት ይዳረጋል፣ መዝረፍ/መስረቅ ለመቅሰፍት ለምሳሌ በመብረቅ ያስመታል፣አዛውንቶችን የተሳደበ፡- ሆዱ በውሃ ይሞላል /ሆዱ ያብጣል ተብሎ ይታመናል፡፡ እምነቱ በምን በምን ላይ የተመሰረተ ነው ለሚለው ለምሳሌ’ቃዳ ቃማ’ያርሾ ኤቃ፣ኮራ በዕጽዋት ሲሆን ‘ያርሾ ዴሼ’ /ዶርሴ እና ባቃ ቦራ በእንሳሳት ሲሆን የያርሾ እንስሳት ምርጫ የሚካሄደው በእንስሳት ቁመናና መልክ የተመሰረት ይሆናል፡፡
የባህላዊ ቤት ዲዛይን፡- /Goofa Keetha Keexo Woga/
ቀን 2021-09-03
የባህላዊ ቤት ዲዛይን፡- /Goofa Keetha Keexo Woga/ አሁን የሚታየው ቤት ጥንት እንዴት እንደተጀመረ የሚታወቅ ስለመሆኑ የሚገልፀው የቀድሞ አባቶች የሠሩትን በማየት ነው፡፡ በባህሉ የቤት መሥሪያ ቦታ መስፈርት አለው፡፡ በባህሉ ቦታ መረጣ ሲካሄድ የመሬት ምርታማነት ይታያል ከአባቱ ቤት አጠገብ ከሆነ ቦታው ልጅ ከአባት ቤት ቤታች ዝቅ ተደረጎ መሠራት እንዳለቤት ይታመናል፡፡ ይህም አባት ለልጅ እንደ አባትም እንደ ፈጣሪም ተደርጎ ስለሚወሰድ ክብር እንደሚገባው በማለት ነው፡፡ ብዙ ጊዜ እንደ አጋጣሚ ማሣው አውራ መንገድ በሚቋርጥበት ሆኖ ከተገኘ ከመንገዱ በታች እንዲሠራ አይመርጥም፡፡ በአጠቃላይ በባህሉ መረጣው ጠጠር በመጣል የሚፈፀም ሲሆን ይህም ግለሰቡ ካሰበበት ቦታ ሆኖ የቤቱ ምሶሶ መቆፈር ያለበትን ጠጠር በመጣል ንገረኝ ምርታማ ስለመሆኑ ምሶሶም ቢሆን ለቀጣይ ችግር አለመኖሩን ስል ይጠይቃል፡፡ በዚህ በሚደረገው ጠጠር ተቀባይነት ባገኘበት ይሠራል ማለት ነው፡፡ በባህል የቤት አሠራር ዲዛይን አለው፡፡ ከላይ ለቀረበው ጥያቄ የባህላዊ ቤት ዲዛይን ወይም ሞድ አለው የጎተማ /Gottoma/ ቤት ሞድ እና የዙፋ /Zuufa / ቤት ሞድ በመባል የተለየ ሲሆን ሁለቱም የራሳቸው የሆነ የአሠራርና ወግ አላቸው፡፡ የቤት መሣሪያ ማቴሪያሎች በአከባቢ ባህል ምንድናቸው፣ ለፃንጌ፡-/xange/ ወይራ ጋላልኦ ማጦተ አምቤ ፃይት ለወፍቾ፡- ግርጫ ቤራ ማይጫ/Loola/ ለጨፈቃነት፡- ማካይሶ ዎርጳቴ ጽጵላ ሣንካራ ወር ሶቦ ሶሊዜ መጋራ ለሰንበሌጥ፡- ዎሾ ማቶስ ጽንቃ ቃጫ ወዘተ…. የባህላዊ ቤት አወቃቀር የቤት ስፋት የሚለካው በእግር ተረግጦ በመቁጠር ሲሆን አለካኩም ሁለቱም እግር በአንድነት ሲሆን ሁለት ጫማ እንደ አንድ ይቆጠራል፡፡ ለምሳሌ 4 ጊዜ የተረገጠ 1 ሜትር ወይም /issi toho/ እስቶ በመባል ነው፡፡ የመጨረሻትልቁ እና ሰፊ ቤት ነው የሚባለው 8 /ስምንት ቶሆ/ ሲሆን የቤቱ ስፋት በግለሰቦች ኢኮኖሚ የሚወሰን ይሆናል፡፡ ከአንድ ግድግዳ ወደ ሌላው ግድግዳ ያለው ርቀቱ በተመለከተ ከአንዱ ፃንጌ ወደ አንዱ ፃንጌ/መሪ/ያለው አንድ ክንድ ሲሆን በመሀል በተመሳሳይ ግድግዳዎች ይገባሉ፡፡ለአንድ ቤት ያለው ምሶሶ የሚወሰነው እንደ ቤቱአሠራር ይሆናል፡፡ ለምሳሌ ቤቱ ጉቶማ ከሆነ ምሶሶ አንድ ይሆናል፡፡ ቤቱ ዙፋ ከሆነ ደግሞ እንደ ቤቱ ስፋት የሚሆንበት ሁኔታ አለ፡፡ በቱ ጎቶማም ሆነ ዙፋ ለቤቱ ያለው በር በባህሉ መሠረት አንድ ይሆናል፡፡ የቤቱ አቅጣጫ ወደ ቀኝ ወይም ምሥራቅ ይሆናል፡፡ ምክንያቱም ይህ ቀኝ የበረከት መምጫ ተብሎ ስለሚታመን ነው፡፡ አማራጭ የታጣ ከሆነ ቤቱ ወደ ግራ ወይም ምዕርብ ተደርጎ ይሠራል፡፡የተኛው ዓይነት ቤት በባህሉ መስኮት የሌውም በህላዊ ቤቱ ሦስት ክፍሎች ይኖሩታል፡፡ጓዳ/ qol77a/ እና ሣሎን /wula/ እና ቁሩጾ /የአባት መኝታ/ የሚገኝበት ቦታ በመባል ሲታወቅ የከብቶች ጋጣም ከቤቱ ክፍል አንዱ ነው፡፡ በባህላዊ ቤቱ ጓዳ ወይም ቆልአ የሚባለው ክፍል የምግብ ማብስያ የሴቶችንና ልጆች መኝታ ያለበት እና መስጢራዊ ዕቃዎች የሚቀመጡበት ቦታ በመሆን ያገለግላል፡፡ በቤቱ ደግሞ ሣሎን የተለያዩ ውብ የሆነው ባህላዊ ዕቃዎች መቀመጫዎች የጦር መሣሪያዎች የአባት መኝታ ፣የእርሻ በሬዎች፣በቅሎ፣አንዳንዴ የከብቶችንና የቤቱ በረከት የሚጠብቅ በግ/ Dharshsho dorssi/ የሚባለው በመግቢያ ላይ ሲታሰር ሌሎች ከብቶች፣ ላሞችና ፍየሎች ወደ ጓዳ በኩል ይታሰራል፡፡ የባህላዊ ቤት የውስጥ አደረጃጀት ስለቤት ውስጥ ክፍፍል ጣሪያ ግድግዳ ጓዳ ሣሎን ወዘተ ዝርዝር በተመከተ በመጀመሪያ አንድ ባህላዊ ቤት ከተሠራ በኃላ የተለያዩ ክፍሎች አሉት በዋናነት በሁለት ከፍሎች ጓዳና ሣሎን በመባል የሚታወቅ ሲሆን የአባት መኝታ ቦታ ተጨማሪ ቁርጾን/ቁርጦ/ አንዳንዱጋ ሲታከል 3/ሦስት ክፍሎች ይኖራሉ፡፡ የቤቱ ምሶሶ ለሣሎን እና ለጓዳ አከፋፈል ተመሳሳይ ሲሆን ከምሶሶ ጋር እኩል ለ2/ለሁለት/ በቃርከሃ ወይም በግርጫእየሠሩ ይለያሉ፡፡ ወደ ጓዳ ያለው ቆልኣ/ጓዳ/ ሲሆን እሳት የሚነድበት እና የተለያዩ የሴት ምግብ ማብስያ መሣሪያ ነገሮች እናመኝታዎች የሚገኙበት ነው፡፡ ከምሶሶው ወደ ወጪ በኩል ያለው ሣሎን እየተባለ የሚጠራው የእግዳ መቀበያ አባት የሚቀመጡበት ሲሆን በሣሎን ላይ በአንድ በኩል ተደርጎ ቁርጾ/አሁንም በቃርካሃ ለመኝታ ብቻ የተሠራ ትንሽ ክፍል ይኖረዋል፡፡ በዚህም በአንድ በኩል ወደ ቆልኣ እና ውላ የሚወጡበትን የሚገቡበትን ጎን ከሣሎን እስከ ጓዳ የከብቶች ጋጣ ዛዳሎ በማቆም በዛዳሎ ላይ ጎጳ በመደርደር የሚዘጋጅ ይሆናል፡፡ ቤት የሚሠራው ለሰዎች መጠለያ እናለእንስሳት ማረፊያ ነው፡፡ እንዳአሁኑ ዘመን እንስሳት ከሰዎች ተለይተው እንድኖር አይመከርም፡፡ ምክንያቱም ከብቶች በባህሉ የቤት ማሞቂያ እና የበረከት ማምጫ ተብሎ ስለሚታመን ነው፡፡ የሠራው ቤት ዕድሜ እንድኖረው የተለያዩ ነገሮች ይደጋሉ፡፡ ከዕነዚህም መጀመሪያ ዕድሜ እንድኖረው ሥሠራ በነቀዝ የማይበሉ እና በአከባቢው ጠንካራ እንጨቶች ተመርጦ ይሠራሉ፡፡ ጣሪያው ዝናብ እንዳያሳልፍ ተደርጎ ይከደናል፡፡ ቤቱ ስከደን በምስጥ እንዳይበላ ዙሪያው ይቆጣጠራል፡፡ ንፋስ እንዳያነሳው በጠንካራ ወፍቾ ከውጪ ቁስተው /qustte/ አንስተው በተለያዩ አቅጣጫ እስከታች በማምጣት የሚያሥሩበት ሁኔታ አለ፡፡ ቤትን ለማስጌጥ የሚገለገሉት ነገር ካለ ለምለው ቤቱ ከተሠራ በኃላ ውቤት እንድኖረው በውጪው በኩል ጣሪያው ላይ ከሸክላ የተዘጋጀ ነገር ይከድናሉ፡፡ መግቢያውን በክናቤ ዳንጭሶ/Kinaabe/ እና በተለያዩ አታክልቶችን በመትከል ዙሪያውን ያሳምራሉ፡፡ በውስጥ በኩል፡- ምርጥ ታጎ/ሰገነት/ በማድረግ በታጎ ላይ የተለያዩ ዕቃዎችን ያስቀምጣሉ የከፍቶች ጋጣ በምያማምሩ እንጨቶች በማዘጋጀት ቆይቶከቀርካሃ በማዘጋጀት እና እቤት ውስጥ በተለያዩ የባህላዊ ዕቃዎች በመስቀል ለምሳሌ ቃንዳ፣ጨንቻ፣ቶራ፣ጋሻ፣ቅሎችን በመስቀል ያስውባሉ፡፡ የአንድ አበወራ ምድረ ገቢ አሟልቶ መገኘት አለበት የሚለው ነገር ብኖር የራሱ የሆነ አጥር ያው እና በግው ውስጥ የተለያዩ አታክልቶች ልኖሩት ይገባል፡፡ ቡና፣ሃለኮ፣ሀረግ በዬ፣እንሴት ወይም እንድሁ እንሴት በብዛት ስኖር ነው የማን ቤት ነው? ብሎ ሰው የሚጠይቀው፡፡ ወይም ይህን ሀሳብ መሠረት በመድረግ አንድ አበወራ በግቢው እንሴትን ብትክል የመጀመሪያ ጉዳይ ነው፡፡ /ሌላው ማድመቂያ ንብ ማርባት ሲሆን ጀግና የሆነ አ/አደር/ ጓሮውን በንብ ቀፎዎች ሲያጅብ በብሔረሰቡ ዘንድ ትልቅ ቦታ አለው፡፡ጎዳሬ፣የተለያዩ ፍራፍረዎች ሎሚ፣ብርትኳን እና ቅመማ ቅመምን ይጠቀማሉ፡፡ ለእንግዳ ማረፍያ ከውስጡ መቀመጫ ያለው እንጨት መኖር አለበት፡፡ የተለያዩ የዕህል ጎተራዎች ለምሳሌ የቦቆሎ፣የጤፍ፣ክምሮች መኖር አለበቸው፡፡ ከደጅፍ ትልቅ ጥላ መኖር አለበት ምክንያቱም ጥላ መኖሩ የጀግንነት መስፈርት ሲሆን ግለሰቡ ለታላላቅ ተግባራት ስፈልግ/gadhan garoy de77ii/? ተብሎ ይጠይቃል፡፡ በጎፋ ብሔረሰብ ሁለት ዓይነት የቤት ስያሜዎች አሉ፡፡ እነዚህም ጎተማ እና ዙፋ በመባል ይታወቃሉ፡፡ ቤት ሥሠሩ የሚፈፀም ባህላዊ ሥራዓትን በተመለከተ፡- መጀመሪያ ቤቱን ለመዘጋጀት በሰበበት ቦታ ላይ ዴሻ ፄሰስ ማለት ፈየል ያርዳል ከዚያ ከማረዱ በፊት የፍየሉ ጀርባ ላይ እየተመታ ቦታው ቀና ነው? ንገረኝ አንተ ፍየል ቦታው ምርታማ ነው? በማለት እየመታ ካረደ በኃላ አንጀቱን እየተመለከተ አንጀቱ ይሁን በሚለው ቦታ ነው ቤቱን የሚሠራው፡፡ አከባቢው የአፈር ዓይነትም ታይቶ ፍዬሉ ከ2-3 ጊዜ ተጠይቆም ተመሳሳይ አይሆንም ምላሽ ከሰጠ ቦታው የግድ መቀየር እንዳለበት ይታመናል፡፡ ጥሩ ቤት ተብሎ የሚወሰደው ቤት ከተለያዩ ጠንካራ ተብለው ከሚገመቱ ዕቃዎች የሚሠራ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ ለፃንገ፡- ቡርጉዴ ኩዜ አምቤ ባርኤ ሶቀላ ግርጫ ሎላ ቤራ ለወፍቾነት፡- ግርጫ ሎላ ቤራ ማይጫ ዳፎ ወዘተ. ለጨፈቃ፡ ጋሎ ሙዝጋ ኦንጋፍሬ ሶሊዜ ለሰንበሌጥ፡- ማቶስ ዎሻ ቃጫ ወዘተ…. እንግዲህ ቤት የሚሠራው በባህሉ በሕብረት በደቦ ነው፡፡ ለደቦ ለሕብረቱ ዘንድ ልዩ ትኩረት ይሰጣል፡፡ ምክንያቱ የቤቱ ጥሩነት መለኪያው የደቦ ወኔና የተሳተፉ የሰው ብዛት ስለሆነ ነው፡፡ ቤቱ ጥሩና የበረከት ቤት እንድዲሆን ሲፈልግ ለደቦ ምግብና የመጠጥ ዝግጅት ወሳኝነት ስላለው ምግቡ ለሥራው ልዩ ጉልበት የሚሰጡ ምግቦችና መጠጦች እንድዘጋጅ ይደረጋል፡፡ ለምሳሌ ምግቡ የቦቆሎ ቅጣ ከዱባ፣ከሀላኮ፣ከድንች፣ከእንሴት ጋር ድብልቅ ማባያ /በብሔረሰቡ ዘንድ ዲናቂ ተዘጋጅቶ ይቀርባል፡፡ በተጨማሪነት የጤፍ ዳቦ ከአዋዜ፣ሀላኮ በአይብ፣ጎመን በአይብ ይቀርባል፡፡ መጠጡ በሚመለከት በዋናነት ከጤፍና ከቦቆሎ የሚዘጋጅ ቦርዴ መጠጥ ሲሆን በአሁኑ ዘመንም ለባለሙያዎች ቨቦርዴው በማር እና የቅጠል ቡና በወተት /ኤንጌሬ/ይቀርባል፡፡ ታዲይ ጥሩ ቤት ተብሎ የሚወሰደው ባህላዊ ቤት ተሠርቶ ለአገልግሎት ለማዋል እስከ 2 ዓመት ጊዜ ይፈጃል፡፡
ያግኙን
☏046-777-1536
ተዛማጅ ሊንኮች
Copyright © 2021-2025 Gofa Zone Adminstration.All Rights Reserved
Gofa,Ethiopia