የጎፋ ዞን ፕላንና ልማት መምሪያ
አቶ ግርማ ዋሼ ዋናቃ የፕላንና ልማት መምሪያ ኃላፊ
ራዕይ፣ተልዕኮ ና ዕሴቶች
ቀን 2021-07-02
የመምሪያው ራዕይ ፍትሃዊ የሀብት ድልድልና አጠቃቀም በማረጋገጥ፣ኢኮኖሚያዊና ማኀበራዊ ዕድገትን በማስፈን የዞኑ ሕዝብ ከድህነት ተላቆ “ኢትዮጵያ አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌት” ሀገራዊ ራዕይ ተሳክቶ ማየት፣ የመምሪያ ተልዕኮ በማኀበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ጥናቶችን በማካሄድና የፖሊሲ ማሻሻያ ሀሳቦችን በማመንጨት፣ግልፀኝነትና ተጠያቂነት በሰፈነበት አሰራር ዘመናዊ የልማት ዕቅድና መረጃ በመዘርጋት፣የልማት አጋሮችን በማስተባበርና የሕዝብ ቁጥር ዕድገት ከኢኮኖሚ እድገት ጋር እንዲጣጣም በመስራት በዞኑ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ልማት እንዲረጋገጥ ማስቻል፣ የመምሪያው ዕሴቶች • ቆጣቢነት • ወቅታዊና አስተማማኝ መረጃ • ፍትሃዊነት • ውጤታማነት • ግልፀኝነትና ተጠያቂነት • ተቆርቋሪነት • ቀልጣፋ አገልገሎት • በዕ ቅድ መመራት • ሕጋዊነት የጎፋ ዞን ፕላንና ልማት መምሪያ የሚያከናውነው ተግባራት የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት አስፈፃሚ አካላትን እንደገና ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 180/2012 መሠረት ከጥቅምት ወር 2012 የክልሉ ፕላን ኮሚሽን መቋቋሙ ይታወሳል ፡፡ በመሆኑም ኮሚሽኑ በአዋጅ የተጣለበትን ተግባርና ኃላፊነት በአግባቡ በመገንዘብ በብቃት ለመወጣትና ከላይ እስከ ታች ባለው መዋቅር የሚገኘውን የኢኮኖሚና የማህበራዊ ችግሮች በተደራጀ አግባብ ለመቅረፍ የሚያስችል ውጤታማ ስራዎች እንዲተገበሩ ለማስቻል የፕላን ኮሚሽኑን ወጥ በሆነ መልኩ ማደራጀት እንዲቻል እንዲሁም ኮሚሽኑ ከፋይናንስና ኢኮኖሚ መምሪያ ተነጥሎ ሲደራጅ ይዞ የወጣውን ዋና ዋና ተልእኮዎችን በሚመለከት ይህ መግለጫ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ 1. የክልሉን የረጅም የመካከለኛና የአጭር ጊዜ ዕቅድ ያዘጋጃል !አፈጻጸማቸውን ይከታተላል ! ይገመግማል ሪፖርት በማዘጋጀት ለሚመለከታቸው አካላት ያቀርባል፣ • የክልሉን የ10 ዓመት መሪ የልማት እቅድ ሰነድ ዝግጅት ማጠናቀቅና ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ በማሳተም ለተተቃሚዎች ማሰራጨት፣ እንዲሁም የሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የማጠቃለያ ጊዜ አፈፃፀም መገምገምና የሪፖርት ሰነድ ማዘጋጀት !ማሳተምና ለተጠቃሚዎች ማሰራጨት፤ • የክልሉን የመሪ ልማት ዕቅድ ዓመታዊ አፈጻጸም ክትትልና ግምገማ ማካሄድና የአፈጻጸም ሪፖርት ማዘጋጀት፤ 2. የማክሮ ኢኮኖሚና ፊስካል ማዕቀፍ ያዘጋጃል ለመስተዳድር ም/ቤት አቅርቦ ያስፀድቃል 3. የክልሉን መንግሥት የካፒታል ፕሮጀክቶች የአዋጭነት ጥናት ያካሂዳል !ይገመግማል !ያስፀድቃል፣ በክልሉ የሚተገበሩ የካፒታል ፕሮጀክቶች ከትግበራ በፊት የፕሮጀክት አዋጭነት ጥናት ማካሄድና ፍትሃዊ ስርጭቱን ማረጋገጥ እና አማራጭ የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት • በፕሮጀክት ዝግጅት ! አዋጭነት ጥናት እና በፕሮጀክት አስተዳደር ዙሪያ ለሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ስልጠና መስጠት 4. በክልሉ የታችኛውን የአስተዳደር እርከን አመታዊ የሀብት ማከፋፈያ ቀመር ያዘጋጃል ! ለክልሉ ም/ቤት እንዲፀድቅ ያቀርባል፣ • የክልሉን የሀብት ማከፋፈያ ቀመር አሠራርን መሠረት በማድረግ ሀብትን በፍትሀዊነት ማከፋፈል ! • በክልላዊ የሀብት ማከፋፈያ ቀመር ዙሪያ ለክልል ለዞንና ልዩ ወረዳ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች እና ለክልልና ለዞን ቋሚ ኮሚቴ አባላት የግንዛቤ ማጎልበቻ ስልጠና ማዘጋጀት ! 5. የክልሉን የካፒታል ፕሮጀክቶችን አፈፃፀም ክትትልና ግምገማ ያደርጋል ' ወቅታዊ ሪፖርት በማዘጋጀት አግባብነት ላላቸው አካላት ያቀርባል፣ • ክልላዊ የካፒታል ኘሮጀክቶች አፈፃፀም ግምገማ በዓመት ሁለት ዙር ማከናወንና ውጤታማነታቸውን ማረጋገጥ፣ 6. የማክሮ ኢኮኖሚ የፖሊሲ አፈጻጸም ጥናት ያካሂዳል • በክልሉ ከሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ጋር በመቀናጀት የክልሉን ቁጠባና ኢንቨስትመንት ጥናት ማካሄድ ! • በሴክተር መ/ቤቶች ተግባራዊ የሚደረጉ ሃገራዊና ክልላዊ የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፖሊሲዎችን ማደራጀት ! ትንተና ማካሄድና የአፈጻጸም ሪፖርት ማቅረብ ! 7. የክልሉን የልማት ክፍተት እና የመልማት አቅም ጥናት ያደርጋል 8. የክልሉን የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ገፅታ ጥናት ያካሂዳል 9. የክልሉን የመካከለኛ ጊዜ የማክሮ ኢኮኖሚና ፊስካል ማዕቀፍ ያዘጋጃል ያስፀድቃል 10. የክልሉን ዓመታዊ የሀብት ግመታ ያዘጋጃል ! ለክልሉ መስተዳድር ም/ቤት በማቅረብ ያፀድቃል፣ • የክልላዊ የሀብት ግመታ ትንተና ሰነድ ማዘጋጀትና ሰነዱን ማሳተም፣ • በክልላዊ የሀብት ግመታ ሰነድ አዘገጃጀት ዙሪያ ከብሔራዊ ፕላንና ልማት ኮሚሽን ጋር በመቀናጀት የኮሚሽኑን ባለሙያዎችንና ኃላፊዎችን አቅም ለመገንባት የሚያስችል ስልጠና ማዘጋጀት • የክልሉን የኢኮኖሚ ዕድገት ምጣኔን ዓለም አቀፍ ስታንዳርዶችና አሰራሮችን መሠረት በማድረግ በጥራትና በብቃት ለመለካት የሚያስችሉ የግብርናና ተዛማጅ ዘርፎች የኢንዱስትሪና የአገልግሎት ዘርፎች የተለያዩ ምርቶችና አገልግሎቶችን ተጨማሪ እሴቶችን ለመለየት የሚያስችሉ ልዩ ልዩ የናሙና ጥናቶችን ማካሄድ 11. የክልሉን የኢኮኖሚ የማህበራዊና መልከአ ምድራዊ መረጃዎችን ይሰበስባል! ያደራጃል! ትንተና በማድረግ ለተጠቃሚዎች ያሰራጫል 12. የክልሉን ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ልማት ስርጭትንና የመልክዓ ምድራዊ ገጽታን የሚያሳይ አትላስና ካርታ ያዘጋጃል 13. የክልሉ መንግሥት መስሪያ ቤቶች በሥራቸው ኃላፊነት የሚያመነጩትን ስታቲስቲካዊ መረጃዎችን የማሰባሰብ፣ የማደራጀት፣ የመተንተንና ለተጠቃሚዎች ተደራሽ እንዲሆን የማድረግ እንዲሁም ስታንዳርዱንና ጥራቱን ጠብቆ እንዲዘጋጅ ድጋፍ፣ ክትትል እና ኦዲት ያደርጋል፣ በመረጃዎች ኦዲት ግኝት መሠረት ተገቢውን የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል፤ 14. የክልሉን የመረጃ ክፍተት ለማሟላት የጥናትና ምርምር ሥራዎችን ያከናውናል፤ 15. የክልሉን የስታቲስቲክስ መረጃ ሥርዓት በማዘመን ለመንግስታዊ መስሪያ ቤቶች ድጋፍ ይሰጣል፤ ሥራውን ያስተባብራል፤ ይመራል፤ 16. የሥነ-ህዝብ ጉዳዮችን በልማት ዕቅድ አካቶ ከመተግበር አኳያ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ያስተባብራል፤ 17. በሥነ-ህዝብ ጉዳዮች የማህበረሰቡንና አመራር አካላትን ግንዛቤ ለማጎልበት የሚያስችሉ የትምህርትና ቅስቀሳ ሥራዎችን ያካሂዳል፤ 18. የሥነ-ህዝብና ልማት ጉዳዮችን በተመለከተ የጥናትና ምርምር ተግባራትን ያከናውናል፤ 19. በየአስተዳደር እርከኑ የሚገኙትን የሥነ-ህዝብ ም/ቤቶችን በማጠናከርና ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር የ5 ዓመት የሥነ-ህዝብ ኘሮግራም ያዘጋጃል፤ ለሥነ-ህዝብ ም/ቤቱ በማቅረብ ያጸድቃል፣ ተግባራዊነቱን ይከታተላል፣ ይገመግማል አቅጣጫ ያስቀምጣል፤ 20. በዕቅድና ኘሮጀክቶች ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዙሪያ የአቅም ግንባታ ሥራዎችን ተግባራዊ ያደርጋል፤ 21. ዓላማውን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስፈልጉ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል ፡፡ • በዚህም መሠረት የኮሚሽንኑን የአደረጃጀት መዋቅር ጥናት በማካሄድ ለክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስ እና ለርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት በማቅረብ ማስወሰን ተችሏል ፡፡ ከላይ እስከ ታች ባለው የአስተዳደር እርከን የኮሚሽኑን አደረጃጀት የሰው ሃይልና የድጋፍ ሰጪ ሁኔታዎችን በተመለከተ ጥናት በማድረግ የጥናት ሰነዱ ለርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ቀርቦ ኮሚሽኑ በዞኖች/ልዩ ወረዳዎች በመመሪያ ደረጃ እንዲሁም በወረዳዎች በጽ/ቤት ደረጃ እንዲቋቋም ተወስኖ በሁሉም የአስተዳደር እርከን መዋቅር እንዲያውቁት በደብዳቤ በተገለፀው መሠረት የጎፋ ዞን ፕላን መምሪያ በመስከረም ወር 2013 ዓ.ም በጎፋ ዞን ህዝብ ምክር ቤት እውቅና አግኝቶ ወደ ሥራ ገብቷል ፡፡ • በዚህም መሠረት እስከ አሁን ባለው ሁኔታ ሁሉም ወረዳ መዋቅሮች ኃላፊ በመሾምና መዋቅሩን በማደራጀት ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች መግባታቸው ይታወቃል፡፡ • የጎፋ ዞን ፕላን መምሪያ በክልሉ መንግስት የተጣለበትን ኃላፊነትና ተግባራትን ለመወጣት በሥሩ ሦስት ዳይሬክቶሬቶች ተደራጅተው ወደሥራ የገቡ ሲሆን፤ እነዚህም ዳይሬክቶሬቶች 1. የፕላን ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክቶሬት 2. የሶሺዮ-ኢኮኖሚና ፊዚካል ጂኦግራፊ ጥናት ጥናት ዳይሬክቶሬት 3. ሥነ-ሕዝብና ልማት ዳይሬክቶሬት • በመሆኑም የጎፋ ዞን ፕላን መምሪያ የክልሉ መንግስት በአዋጅ የጣለበትን ተግባርና ኃላፊነት በአግባቡ በመገንዘብ በብቃት ለመወጣትና ከላይ እስከ ታች ባለው መዋቅር የሚገኘውን የኢኮኖሚና የማህበራዊ ችግሮች በተደራጀ አግባብ ለመቅረፍ የሚያስችል ውጤታማ ስራዎች እንዲተገበሩ ለማስቻል በየዳይሬክቶሬቶች ያሉ ዋና ዋና ሥራዎች በሚመለከት ይህ መግለጫ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ የፕላን ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክቶሬት 1. የዞኑን የረጅም የመካከለኛና የአጭር ጊዜ ዕቅድ ያዘጋጃል !አፈጻጸማቸውን ይከታተላል ! ይገመግማል ሪፖርት በማዘጋጀት ለሚመለከታቸው አካላት ያቀርባል፣ • የዞኑን የ10 ዓመት መሪ የልማት እቅድ ሰነድ ዝግጅት ማጠናቀቅና ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ በማሳተም ለተተቃሚዎች ማሰራጨት፣ • የዞኑን የመሪ ልማት ዕቅድ ዓመታዊ አፈጻጸም ክትትልና ግምገማ ማካሄድና የአፈጻጸም ሪፖርት ማዘጋጀት፤ 2. የዞኑን መንግሥት የካፒታል ፕሮጀክቶች የአዋጭነት ጥናት ያካሂዳል !ይገመግማል !ያስፀድቃል፣ • በዞኑ የሚተገበሩ የካፒታል ፕሮጀክቶች ከትግበራ በፊት የፕሮጀክት አዋጭነት ጥናት ማካሄድና ፍትሃዊ ስርጭቱን ማረጋገጥ እና አማራጭ የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት • በፕሮጀክት ዝግጅት ! አዋጭነት ጥናት እና በፕሮጀክት አስተዳደር ዙሪያ ለሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ስልጠና መስጠት 3. በዞኑ የታችኛውን የአስተዳደር እርከን አመታዊ የሀብት ማከፋፈያ ቀመር ያዘጋጃል ! በዞኑ ም/ቤት እንዲፀድቅ ያቀርባል፣ • የዞኑን የሀብት ማከፋፈያ ቀመር አሠራርን መሠረት በማድረግ ሀብትን በፍትሀዊነት ማከፋፈል ! • በዞኑ የሀብት ማከፋፈያ ቀመር ዙሪያ ለዞን፣ለወረዳ እና ከተማ አስተዳደሮች የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች እና የግንዛቤ ማጎልበቻ ስልጠና ማዘጋጀት ! 4. የዞኑን የካፒታል ፕሮጀክቶችን አፈፃፀም ክትትልና ግምገማ ያደርጋል ' ወቅታዊ ሪፖርት በማዘጋጀት አግባብነት ላላቸው አካላት ያቀርባል፣ • ዞናዊ የካፒታል ኘሮጀክቶች አፈፃፀም ግምገማ በዓመት ሁለት ዙር ማከናወንና ውጤታማነታቸውን ማረጋገጥ፣ • የክልላዊ የሀብት ግመታ ትንተና ሰነድ ማዘጋጀትና ሰነዱን ማሳተም፣ የሶሺዮ-ኢኮኖሚና ፊዚካል ጂኦግራፊ ጥናት ጥናት ዳይሬክቶሬት 1. የዞኑን የኢኮኖሚ የማህበራዊና መልከአ ምድራዊ መረጃዎችን ይሰበስባል! ያደራጃል! ትንተና በማድረግ ለተጠቃሚዎች ያሰራጫል፣ 2. የዞኑን ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ልማት ስርጭትንና የመልክዓ ምድራዊ ገጽታን የሚያሳይ አትላስና ካርታ ያዘጋጃል፣ 3. የዞኑ መንግሥት መስሪያ ቤቶች በሥራቸው ኃላፊነት የሚያመነጩትን ስታቲስቲካዊ መረጃዎችን የማሰባሰብ፣ የማደራጀት፣ የመተንተንና ለተጠቃሚዎች ተደራሽ እንዲሆን የማድረግ እንዲሁም ስታንዳርዱንና ጥራቱን ጠብቆ እንዲዘጋጅ ድጋፍ፣ ክትትል እና ኦዲት ያደርጋል፣ በመረጃዎች ኦዲት ግኝት መሠረት ተገቢውን የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል፤ 4. የዞኑን የስታቲስቲክስ መረጃ ሥርዓት በማዘመን ለመንግስታዊ መስሪያ ቤቶች ድጋፍ ይሰጣል፤ ሥራውን ያስተባብራል፤ ይመራል፤ ሥነ-ሕዝብና ልማት ዳይሬክቶሬት 1. የሥነ-ህዝብ ጉዳዮችን በልማት ዕቅድ አካቶ ከመተግበር አኳያ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ያስተባብራል፤ 2. በሥነ-ህዝብ ጉዳዮች የማህበረሰቡንና አመራር አካላትን ግንዛቤ ለማጎልበት የሚያስችሉ የትምህርትና ቅስቀሳ ሥራዎችን ያካሂዳል፤ 3. በየአስተዳደር እርከኑ የሚገኙትን የሥነ-ህዝብ ም/ቤቶችን በማጠናከርና ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር የ10 ዓመት የሥነ-ህዝብ ኘሮግራም ያዘጋጃል፤ ለሥነ-ህዝብ ም/ቤቱ በማቅረብ ያጸድቃል፣ ተግባራዊነቱን ይከታተላል፣ ይገመግማል አቅጣጫ ያስቀምጣል፤ የጎፋ ዞን አስተዳደር 2013 ዓ.ም የሕዝብ ብዛት ተ.ቁ የወረዳ/ከተማ ስም የከተማ ሕዝብ ብዛት የገጠር ሕዝብ ብዛት ጠቅላላ ድምር ወንድ ሴት ድምር ወንድ ሴት ድምር ወንድ ሴት ድምር 1 ዑ/ደ/ፀሐይ 19,613 14,692 34,305 64,178 53,354 117,532 83,791 68,046 151,837 2 ዛላ 11,506 9,436 20,942 77,848 63,300 141,148 89,354 72,736 162,090 3 ኦይዳ 15,478 11,812 27,290 31,533 13,850 45,383 47,011 25,662 72,673 4 ሣውላ ከተማ 32,577 32,936 65,513 18,573 20,357 38,930 51,151 53,293 104,444 5 ደምባ ጎፋ 5,819 4,642 10,461 93,104 74,267 167,371 98,923 78,909 177,832 6 ገዜ ጎፋ 7,322 5,590 12,912 55,696 41,083 96,779 63,018 46,673 109,691 7 ቡልቂ ከተማ 18,722 14,827 33,550 0 0 0 18,722 14,827 33,549 8 መሎ ኮዛ 25,130 18,941 44,071 70,834 51,708 122,542 95,964 70,649 166,613 9 መሎ ጋዳ 2,578 3,567 6,145 33,648 34,156 67,804 36,226 37,723 73,949 ድምር 138,745 116,443 255,189 445,414 352,075 797,489 584,160 468,518 1,052,678 የትምህርት ሴክተር መረጃ ዋና ዋና መረጃዎች እድሜያቸዉ ለትምህርት የደረሰ ተማሪዎች ብዛት መረጃ ተ ቁ ወረዳ /ከ/አስተዳደር/ስም ከ 7-14 ዓመት የሆናቸዉ 15-18 ዓመት የሆናቸዉ 7-18 ጠ/ድምር ወንድ ሴት ድምር ወንድ ሴት ድምር ወንድ ሴት ድምር 1 ቡልቂ ከተማ 1774 1847 3621 645 780 1425 2419 2626 5045 2 ዑባ ደ/ፀሐይ 9895 9144 19039 3519 3423 6942 13414 12567 25981 3 ኦይዳ 5098 4942 10040 1871 1996 3867 6969 6938 13907 4 ገዜ ጎፋ 10006 9797 19803 3802 4067 7869 13808 13864 27672 5 ዛላ 11811 11358 23169 4643 4568 9211 16454 15926 32380 6 ሣውላ ከተማ 6133 6656 12789 4734 4724 9458 10867 11380 22247 7 ደምባ ጎፋ 12663 12338 25001 5205 5497 10702 17868 17835 17835 8 መሎ ኮዛ 14094 13130 27224 4501 4795 9296 18594 17925 17925 9 መሎ ጋዳ ወረዳ 3889 3701 7590 1239 1353 2592 5128 5054 5054 10 ላሃ ከተማ 988 962 1950 303 357 660 1291 1319 1319 11 በቶ ከተማ 1348 1270 2618 459 483 942 1807 1753 1753 ጠ/ድምር 77699 75145 152844 30921 32043 62964 108619 107187 215806 በመደበኛው ክፍለ ጊዜ በመንግስት ት/ት ቤት በዓመቱ ለመማር የተመዘገቡ ተማሪዎች ብዛት መረጃ /1--8 / ተ/ቁ ወረዳ /ከ/አስ/ስም 1ኛ ክፍል 2ኛ ክፍል 3ኛ ክፍል 4ኛ ክፍል 5ኛ ክፍል 6ኛ ክፍል 7ኛ ክፍል 8ኛ ክፍል ድምር ጠ/ድምር ወ ሴ ወ ሴ ወ ሴ ወ ሴ ወ ሴ ወ ሴ ወ ሴ ወ ሴ ወ ሴ 1 ቡልቂ ከተማ 167 207 216 188 159 158 163 220 248 252 168 188 130 140 118 113 1369 1466 2835 2 ዑባ ደ/ፀሐይ 2289 2005 1731 1503 1265 1139 1196 1105 1287 1211 1030 939 669 655 472 440 9939 8997 18936 3 ኦይዳ 753 708 658 580 465 525 541 506 568 623 446 542 223 212 411 409 4065 4105 8170 4 ገዜ ጎፋ 1353 1348 1317 1196 949 934 1113 1063 1261 1229 994 1038 748 660 691 664 8426 8132 16558 5 ዛላ 1711 1699 1982 1736 1625 1608 1568 1688 1358 1509 1186 1434 834 925 619 587 10883 11186 22069 6 ሣውላ ከተማ 920 870 757 709 639 697 601 623 636 668 668 662 549 562 436 413 5206 5204 10410 7 ደ/ጎ/ወ 1385 1316 1593 1410 1279 1385 1601 1500 1263 1416 1051 1097 1031 999 759 672 9962 9795 19757 8 መሎ ኮዛ 1829 1695 2389 2021 1535 1485 1563 1464 1564 1504 1417 1284 1085 979 909 806 12291 11238 23529 9 መሎ ጋዳ ወረዳ 1355 1227 1068 846 687 553 767 543 790 562 640 424 502 435 460 265 6269 4855 11124 ጠ/ድምር 11762 11075 11711 10189 8603 8484 9113 8712 8975 8974 7600 7608 5771 5567 4875 4369 68410 64978 133388 በመደበኛው ክፍለ ጊዜ በመንግስት ት/ት ቤት በዓመቱ ለመማር የተመዘገቡ ተማሪዎች ብዛት መረጃ /9--12 / ተ.ቁ ወረዳ /ከ/አስ/ ስም 9ኛ ክፍል 10ኛ ክፍል 11ኛ ክፍል 12ኛ ክፍል አጠ/ድምር 9--12 ወ ሴ ወ ሴ ወ ሴ ወ ሴ ወ ሴ ጠ/ድምር 1 ቡልቂ 445 439 245 319 164 305 128 110 982 1173 2155 2 ዑባ ደ/ፀሐይ 499 406 370 369 266 259 151 94 1286 1128 2414 3 ኦይዳ 301 330 202 238 72 45 70 78 645 691 1336 4 ገዜ ጎፋ 278 274 274 312 133 104 98 60 783 750 1533 5 ዛላ 560 597 396 445 242 268 205 188 1403 1498 2901 6 ሣውላ ከተማ 749 751 566 601 723 729 369 265 2407 2346 4753 7 ደምባ ጎፋ 479 509 393 374 265 247 188 148 1325 1278 2603 8 መሎ ኮዛ 805 668 499 463 343 293 143 127 1790 1551 3341 9 መሎ ጋዳ ወረዳ 159 91 181 103 0 0 0 0 340 194 534 ጠ/ድምር 4275 4065 3126 3224 2208 2250 1352 1070 10961 10609 21570 በመንግስት ት/ት ቤት ያሉ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራን ብዛት መረጃ ወረዳ/ከተማ Primary Lower Cycle Primary Upper Cycle Total General Secondary Total Number of teachers M F T M F T M F T M F T M F T 1 ቡልቂ 28 39 67 39 24 63 67 63 130 54 18 72 121 81 202 2 ዑባ ደ/ፀሐይ 256 107 363 227 70 297 483 177 660 98 11 109 581 188 769 3 ኦይዳ 158 77 235 117 14 131 275 91 366 71 13 84 346 104 450 4 ገዜ ጎፋ 150 123 273 165 46 211 315 169 484 70 19 89 385 188 573 5 ዛላ 205 115 320 163 69 232 368 184 552 112 36 148 480 220 700 6 ሣውላ ከተማ 125 169 294 54 35 89 179 204 383 122 40 162 301 244 545 7 ደምባ ጎፋ 202 217 419 151 48 199 353 265 618 75 12 87 428 277 705 8 መሎ ኮዛ 305 274 579 238 58 296 543 332 875 122 13 135 665 345 1010 9 መሎ ጋዳ 136 47 183 113 5 118 249 52 301 22 2 24 271 54 325 ድምር 1565 1168 2733 1267 369 1636 2832 1537 4369 746 164 910 3578 1701 5279 እንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ዋና ዋና መረጃዎች በጎፋ ዞን ያለው የእንስሳት እርባታ፣ እንስሳት ሐኪም፣ አዳቀይ ባለሙያና የንብ ቴክኒሺያን መረጃ ተ.ቁ ወረዳ/ከ/አስ የእንስሳት እርባታ ባለሞያ እንስሳት ሐኪም ረዳት የእንስሳት ሀኪም ረዳት ጤ/ቴክንሽያን አዳቀይ ባለሙያ የንብ ቴክኒሺያን ጠቅላላ የዞን ባለሞያ ወ ሴ ድ ወ ሴ ድ ወ ሴ ድ ወ ሴ ድ ወ ሴ ድ 1 መሎ ኮዛ 7 2 9 2 0 2 16 6 22 0 0 0 2 1 26 8 34 2 መሎ ጋዳ 7 4 11 1 0 1 11 6 12 0 0 0 1 0 20 10 30 3 ገዜ ጎፋ 5 1 6 2 0 2 19 6 25 0 1 1 2 0 27 8 35 4 ኦይዳ 18 6 24 1 0 1 10 1 11 0 0 0 2 0 30 7 37 5 ደምባ ጎፋ 7 2 9 3 0 3 20 1 21 0 0 0 2 1 31 3 34 6 ዛላ 6 8 14 6 0 6 33 4 37 1 0 1 4 0 47 12 59 7 ዑ/ደብረ-ፀሐይ 16 5 21 9 2 11 11 1 12 0 1 1 2 0 37 9 46 8 ቡ/ከተማ አስ. 1 0 1 2 2 4 0 0 0 0 0 0 1 0 4 2 6 9 ሳ/ከተማ አስ. 6 3 9 4 3 7 3 0 3 0 0 0 1 0 14 6 20 ጠቅላላ ድምር 73 31 104 30 7 37 123 25 143 1 2 3 17 2 228 65 293 የእ/ዓ/ሀ/ል/መምርያ 2013ዓ.ም የእንስሳት ቁጥር መረጃ ተ/ቁ ወረዳ ከ/አስ/ር ዳ/ከብት በግና ፍየል የጋማ ከብት ዓዋፍ ቀ/ከብት በግ ፍየል አህያ ፈረስ በቅሎ ዶሮ ጠ/ድምር 1 መሎ ኮዛ 121,351 178,717 32,211 7487 3381 8701 229,770 581,618 2 መሎ ጋዳ 99,515 134,188 65,555 1412 2515 2223 146,838 452,246 3 ገዜ ጎፋ 260079 94169 37542 7822 10057 8701 140417 558,787 4 ደምባ ጎፋ 299,250 64,073 73,045 15,750 2159 1007 285,119 740,403 5 ኦይዳ 121,359 79,747 38,154 10626 3282 4987 265,251 523,406 6 ዛላ 624626 9435 526990 272256 0 583 383481 1817371 7 ዑባ ደብረ ጸሀይ 287865 57175 116449 20835 8786 6722 263130 760962 8 ሳውላ ከተማ 42,396 5,536 8,250 4,517 0 8 55,600 116,307 9 ቡልቂ ከተማ 7675 5956 1081 17850 405 165 18000 51,132 ድምር 1,864,116 628,996 899,277 358,555 30,585 33,097 1,787,606 5,602,232
የጎፋ ዞን ውሃ ማ/ኢ/ መምሪያ
ዋልታንጉስ ዋቻ ውሃ ማ/ኢ/ መምሪያ ኃላፊ
የሴክተሩ ራዕይ፣ ተልዕኮ፤ እሴቶች እና ዓላማ
ቀን 2021-07-02
ራዕይ የዞኑ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ሀብት በአግባቡ ተጠብቆና ለምቶ የዞኑ ህ/ሰብ ንፁህ ፤በቂና አስተማማኝ የውሃ አቅርቦት ፍትሐዊ በሆነ መልኩ አግኝቶ የአከባቢውን የማዕድን ሀብትና ኢነርጂ አማራጮች ተጠቃሚ ሆኖ የተሸለ ሕይወተወ ሲመራ ማየት ተልዕኮ የዞኑን ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ሀብት ፍትሐዊ በሆነና ዘለቀታዊነት ባለው መልኩ በማጥናት በማልማትና በማስተዳደር የዞኑን ህዝብ ኢኮኖሚያና ማህበራዊ ኑሮ ማሻሻል እሴቶች • ለዘላቂና ለተቀናጀ የውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ሀብት ልማት ጠንክረን እንሰራለን • የውሃ መስኖ ማዕድንና ኢነርጂ ዘርፍ የመረጃ ባንክ ነን • ሴቶች የውሃ መስኖ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ እንድሆኑ እናደርጋለን • ውሃ ሕይወት ነው • ውሃ ቁልፊ የልማት መግብያ ነው • የውሃ መስኖ ማዕድንና ልማት በሌሎች የልማት ዘርፎች ላይ ወሳኝ ድርሻ አለው • ውሃን በቁጠባ እንጠቀም • ውሃ ለግብርና ልማት • ለተጠቃሚው በቂና ዘላቂ የመስኖ ውሃ አቅርቦት • የህብርተሰብ ተሳትፎ ለመስኖ ልማት • ማዕድን ወጋ አለው ማዕድን ለመሰረተ ልማት ግንባታ ወሳኝ ነው • ግልፅኝነት ታማኝነት ተጠያቂነት ቁርጠኝነት ፍትሃዊነትና ቅንነት • አማራጭ ኢነርጂ በመጠቀም የመብራት አገ/ት ለገጠሩ ህብረተሰብ ተደራሽ እናደርጋለን
የጎፋ ዞን ህብረት ስራ ልማት ልማት ጽ/ቤት
አቶ ዲቡ ሰለሞን
ተልዕኮ (MISSION) ራዕይ (vision) እሴቶች (Values)
ቀን 2021-03-13
ራዕይ፡- በ2014 ዓ.ም የአባላትን ኑሮ በላቀ ደረጃ የለወጡ እና ለአገር ብልጽግና የላቀ ሚና ያበረከቱ ጠንካራና ተወዳዳሪ ኅብረት ሥራ ማኅበራት ተፈጥረው ማየት ነው፡፡ ተልዕኮ፡- በገጠርና በከተማ የሚኖረው ህብረተሰብ የአካባቢውን ሃብት መሰረት አድርጎ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሩን ለመፍታት በፈቃደኝነት ላይ ተመስርቶ በተለያየ አይነትና ደረጃ የተደራጁ የኅብረት ስራ ማህበራትን በማጠናከርና በማዘመን፣የኅብረት ሥራ ኤክስቴንሽን በማስፋፋት፣አቅማቸውን እና ኢንቨስትመንትን ማበረታታት፤ህግናህጋዊነታቸውን እና ጤናማነታቸውን ማስጠበቅ፤የአገልግሎት አሰጣጣቸውን ቀልጣፋ በማድረግ የአባላትን ተጠቃሚነት በዘላቂነት ያረጋገጡ ውጤታማና ተወዳዳሪ የኅብረት ስራ ማህበራትን የመፍጠር ተልዕኮ አንግቧል፡፡ ዕሴቶች፡- • ግልጽነትና ተጠያቂነት • ፍትኃዊነትና አሳታፊነት • ታማኝነት • ቁርጠኝነት • መተባበርና ወንድማማችነት • በራስ መተማመን • መቀናጀት • በህዝብ አገልጋይነት መኩራት • ለአካባቢያዊ ዕውቀት ክብር መስጠት • ለስኬት እውቅና መስጠት • በእኩልነት ማመን
ያግኙን
☏046-777-1536
ተዛማጅ ሊንኮች
Copyright © 2021-2025 Gofa Zone Adminstration.All Rights Reserved
Gofa,Ethiopia