የጎፋ ዞን አከባቢ ጥበቃ ደ/የአ/ን/ለ/ቁጥጥር ጽ/ቤት
ተፈራ አሽኔ የጽ/ቤት ኃላፊ
ራዕይ፣ተልዕኮ ና ዕሴቶች
ቀን 2021-09-03
ራዕይ • በ2017 ዓ/ም ለአየርንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ በዞኑ ተገንብቶ ለኑሮና ለሥራ ምቹ አካባቢ ተፈጥሮ ማየት ተልዕኮ • የአካባቢ፣የብዝ-ሀሕይወትና የደንሀብት አያያዝ፣ ልማትና አጠቃቀም ለዘላቂ ልማትና ለድህነት ቅነሳ አስተዋጽኦ እንዲያ ደርግ ሥርዓትን የማዘጋጀትና ተፈፃሚነቱን የማረጋገጥ፤ የምርምር ና የአረንጓዴ ቴክኖሎጂ ሽግግርን የማስተባበርና የማካሄድ፤ትምህርትና ግንዛቤን የማስፋፋት፤ለአየርንብረት ለውጥ የማይበገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚልማት ትግበራን የማስተባበር፤የተግባሪዎችን አቅም የመገንባት፤ የደን ኢንቨስትመንትንና ግብይትን የማስፋፋት፤ ሀገሪቷ የተፈራረመቻቸውን ዓለም አቀፍ የአካባቢና የደን ስምምነቶች የመተግበር እና ወቅታዊ የአካባቢ እና የደን ሁኔታና ለውጥ ዘገባን የማዘጋጀት ተግባራትን ማከናወን ዕሴቶች • ለተገልጋዮች ፈጣንና ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት፤ • በዕቅድ መመራት፤ • የተፈጥሮ ሀብታችንና አካባቢያችንን መንከባከብ፤ • የለውጥ ኃይሎችን ማበረታታት፤ • ህብረተሰቡን በልማት ማሳተፍ፤ • ሀብትን በአግባቡና በቁጠባ መጠቀም፤ • ሙያዊ ሥነ-ምግባር ማስፋፋት፤ • ፍትሃዊነት፤ሰብአዊነትና ተጠያቂነትን ማስፋን፤ • ለሀገርበቀልዕዉቀትእዉቅናመስጠት፤ • የሴቶችና የወጣቶች የልማት ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፤
የጎፋ ዞን ኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ጽ/ቤት
አቶ ያለዉ ያማ ዳጋላ ኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ጽ/ቤት ኃላፊ
የሴክተሩ ራዕይ፣ ተልዕኮ፤ እሴቶች እና ዓላማ
ቀን 2021-09-03
ራዕይ • በ2022 ዞናችን በክልላችን ምቹ ኢንቨስትመንት ሁኔታ የሰፈነበት፤ኢንቨስትመንት የተስፋፋበት እና ተወዳዳሪ አልሚ የሆኑ ባለሀብቶች የተፈጠሩበት ለኢኮኖሚው ዕድገት ድርሻውን የሚያበረክት ግንባር ቀደም ተቋም ሆኖ ማየት ፤ ተልዕኮ • የዞኑን የኢንቨስትመንት አማራጮች በማጥናት፣ በማስተዋወቅ፣ ፈቃድና መሬት በመስጠት ልማታዊ ባለሀብቶችን በማበረታታት እንዲሁም የኢንቨስትመንት አፈጻጸማቸውን በመከታተልና የሚከሰቱ ችግሮች የሚፈቱበትን አሰራር በመቀየስ በዞኑ የግል ኢንቨስትመንትን ማስፋፋትና ማጠናከር ነው፡፡ ዕሴቶች • የመንግሰት ፖሊሲና ስትራቴጂ የዕቅዶቻችን መርሆዎች ናቸው፣ • ሥራዎቻችን የጋራ አመለካከትና ግንዛቤ ከመፍጠር ይጀምራሉ፣ • ፍትሃዊ፣ አሳታፊና ዴሞክራሲያዊ አመራር መለያችን ነው፣ • የሰው ሀይልና ጊዜ ካሉን ሀብቶች ሁሉ ቀዳሚ ሀብታችን ነው፣ • በዕቅድ እንመራለን፤ • መረጃ ለልማት እናዉላለን፤ • ዉጤት ያሸልማል፤ • ክራይ ሰብሳብነትን እንፀየፋለን፤ • ተገልጋዮቻችን የህልዉናችን መሠረት ናቸዉ፤ • የአገልግሎቶቻችን ተጠቃሚዎችን እናከብራቸዋለን ደመወዛችንን የሚከፍሉን እነሱ ናቸው፣ • ቅሬታ አቅራቢዎች መካሪዎቻችን ናቸው፣ • ቀጠሮ ማክበርና ማስከበርን ባህላችን እናደርገዋለን፣ • ጥራት፣ ግልፀኝነት፣ ተጠያቂነት፣ ፍጥነት እና ታማኝነት አምስቱ ጥምር የስራ ሂደታችን ሀብቶች እናደርጋቸዋለን፣ • ሁሌም ተማሪና አስተማሪ ነን፣ • አለቃችን ሥራችን ነው ሥራውም ውጤቱም የኛ ነው፡፡ ዓላማ • በዞኑ የኢንቨስትመንት አማራጭ ዕድሎችና ንጽጽራዊ ጠቀሜታ ላይ ያነጣጠረ የማስተዋወቅ ስራ በመስራት የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶችን በመሳብ የዞኑን የግል ኢንቨስትመንት በማስፋፋት የተፈጥሮ ሀብታችንን ጥቅም ላይ በማዋልና በማልማት፣ የወጪ ምርቶች ገበያን በማዳበር፣ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲፈጠር በማድረግ፣ ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር የዞኑን ህዝቦች የኑሮ ደረጃ ማሻሻልና ለአጠቃላይ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ዕድገት የበኩሉን ድርሻ እንዲያበረክት ማድረግ፣
የንግድና ገ/ልማት መምሪያ
ወ/ሮ ትዝታ አብርሃም ሲሪ የንግድና ገ/ልማት መምሪያ ኃላፊ
የንግድና ገ/ልማት መምሪያ ዓላማ ፣ራእይ፣ ተልዕኮና ዕሴቶች
ቀን 2021-09-02
ዓላማ፡- • ፍትሃዊ የንግድ አሰራርንና ዘመናዊ የግብይት ሥርዓትን ማስፈን • መልካም አስተዳደርን በማስፈን የንግዱን ማህበረሰብ፣ ሸማቹን ማህበረሰብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ • እርካታ ደረጃዉን ከፍ ማድረግ ራዕይ፡- • ለሀገር ዉስጥና ለዉጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን በዓይነት፣ በመጠን፣ በጥራት አድገዉ ማየት • በቀጣይ ዕድገት ላይ የተመሰረተ በዓለም ተወዳዳር ማድረግ • ዘመናዊ ፣ ህጋዊና ፍታሃዊ የንግድ ግብይት ዘርፍ ተፈጥሮ ማየት ተልዕኮ፡- • በዞኑ የነፃ ገበያ ፖልስ መሪህ የተከተለ ንግድና ግብይትን ማዘመን • ንግድን በማስፋፋት ህጋዊነትን፣ ፍትሃዊነትን በማስፈን የሸማቹን ህብረተሰብ ተጠቃምነትን ማረጋገጥ ዕሰቶች፡- • በዕቅድ መመራት • ፍትሃዊ፣ አሳታፍና ዴሞክራሲያዊ አመራር ተለይቶ የማያቋርጥ ለዉጥ ማየት • ጊዜና የሰዉ ኃይል ካሉን ሀብቶች ሁሉ ቁልፍ ሀብቶች ስለሆኑ ሟሟላት • ኪራይ ሰብሳቢነት መታገል • መረጃን ለልማትዊ ጉዳይ በአፋጣኝ መስጠት • ሥራን ዉጤታማ በማድረግ መሸለም • ተገልጋዮችን በክብር ማስተናገድ • ቅሬታ አቅራቢዎቻችን በመልካም ሥነ ምግባር ማስተናገድ
ያግኙን
☏046-777-1536
ተዛማጅ ሊንኮች
Copyright © 2021-2025 Gofa Zone Adminstration.All Rights Reserved
Gofa,Ethiopia