የጎፋ ዞን ግብርና መምሪያ
ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አብርሃም ዞራ
ተልዕኮ (MISSION) ራዕይ (vision) እሴቶች (Values)
ቀን 2021-12-01
ተልዕኮ (MISSION) የተፈጥሮ ሀብትንና አካባቢን በመጠበቅና በማልማት ፤ የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ስርዓትን በማስፈን፤ ሥነ-ምህዳርን መሠረት ባደረገ መልኩ የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም፤ የመስኖና ሌሎች የልማት አዉታሮችን በመዘርጋትና የተጠናከረ የኤክስቴሽን አገልግሎት በመስጠት ምርትና ምርታማነትን መጨመርና የገበያ ትስስርን በመፍጠር የኅብረተሰቡን ገቢ ማሳደግ ራዕይ (vision) በ2014 ዓ.ም በገበያ ላይ የተመሰረተ ዘመናዊ የግብርና ልማት ሰፍኖ የአርሶ አደሩን የኑሮ ደረጃ ተለዉጦ ማየት እሴቶች (Values) • አርሶ አደሩ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ቅድሚያ እንሰጣለን • ህብረተሰቡን በልማት እናሳትፋለን • ፍትሃዊነት፤ ሰብአዊነትና ተጠያቅነትን እናሰፍናለን • ለሀገር በቀል ዕዉቀት እዉቅና እንሰጣለን • የሴቶችና የወጣቶች ተሳትፎና የልማት ተተቃሚነትን እናረጋግጣለን • ፈጣንና ጥራት ያለዉ አገግሎት እንሰጣለን • ተፈጥሮ ሀብታችንና አካባቢያችንን እንከባከባለን • መረጃ ለልማት እናዉላለን • የለዉጥ ኃይሎችን እናበረታታለን • ሙያዊ ሥነ-ምግባር እናሰፍናለን
የጎፋ ዞን ገ/ባ/ዋ/ቅ/ጽ/ቤት
ወ/ሮ ጥሩነሽ ወዛ ገ/ባ/ዋ/ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ
ራዕይ(Vision) ተልዕኮ(Mission) እሴቶች(Value)
ቀን 2021-11-30
ራዕይ(Vision) በ 2022 ዜመናዊ የታክስ አስተዳደር ሥርዓት ተገንብቶ ኢኮኖሚዉ ከሚያመነጨዉ ሀብት ሙሉ በሙሉ ገቢ ተሰብስቦ ለልማት ዉሎ ማየት ተልዕኮ(Mission) ሁለንተናዊ አቅሙ የተገነባ ተቋም እና የሰዉ ሀይል በማፍራት ዜመናዊ ቴክነ ሎጅ በመጠቀም የተጣጣመ ዞናዊ የታክስ አስተዳደር ሥርዓት በመገንባት ፍትሃዊ የላቀና ተጠያቂነት የሰፈነበት አገልግሎት በመስጠት ታክስ በፍቃደኝነት የመክፈል ባህልን በማደሳበር የታክስ እና የገቢ ህግጋትን በማስከበር ኢኮኖሚዉ የሚያመነጨዉን ገቢ መሰብሰብ፡፡ እሴቶች(Value) • አገልጋይነት • አገልግሎትን በጊዜና በጥራት በመስጠት በልጦ መገኘት • ሙያና ክህሎት ለተጨባጭ ዉጤት መጠቀም • ታማኝነት • ተጠያቂነት • በትብብርና በዉድድር ላይ የተመሰረተ የሥራ ግንኙነት መፍጠር ለግንዛቤ ያክል ለዞናችን ህብረተሰብ የሚተላለፉ መልዕክቶች እርስዎ ምን ይላሉ? • ግብይት ስፈፁሙም ሆነ አገልግሎት ሲያገኙ ለከፈሉት ገንዘብ ደረሰኝ ይቀበላሉ? • ደረሰኝ በመስጠትም ሆነ በመቀበል ዙሪያ እርስዎ ምን ይላሉ? • ሕጋዊ ግብይት ሲፈጽሙም ሆነ አገልግሎት ሲያገኙ ለከፈሉት ገንዘብ ደረሰኝ ይቀበላሉ? • ደረሰኝ በመስጠትም ሆነ በመቀበል ዙሪያ እርስዎ ምን ሀሳብ አለዎት? • ሕጋዊ የንግድ ሥርዓትን እዉን ለማድረግ ደረሰኝን በአግባቡ መጠቀም ቅድሚያ የሚሰጠዉ ጉዳይ ነዉ እና በዚህ ላይ ላይ አስተያየትዎን፣ ገጠመኝዎን ወይም ምን መደረግ አለበት በሚለዉ ላይ ሃሳብዎን ያካፉሉን? • ገንዘብዎን ለሚከፍሉት ንብረትዎ ደረሰኝ መቀበልዎን አይዘንጉ!! • በታማኝነት የምንከፍለዉ ታክስ ለነገዉ ትዉልድ የምናስቀምጠዉ ስንቅ ነዉ!! • የግብር ማጭበርበርን እና ሙስናን መከላከል ብሎም ማጋለጥ የሁሉም ዜጋ አገራዊ ኃላፊነት ነዉ!! ለግንዛቤ ያክል የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ ጥቅም ከግብር ባለሥልጣኑ መ/ቤቱ አንፃር • ፍትሃዊ የግብር አሰባሰብ ስርዓትን ለማስፈን ይረዳል፣ • ታክስን በቀን ገቢ ግምት ላይ ተመስርቶ ከመወሰን በመላቀቅ በመረጃ ላይ የተመሰረተ የግብር አወሳሰንና አሰባሰብ ስርአትን ለማስፈን ይረዳል፣ • ወቅታዊ የሽያጭ መረጃ እንዲኖር ያደርጋል፣ • ለዘመናዊ የታክስ ስረዓት እድገት መሠረት ነዉ፡፡ የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ ጥቅም ከግብር ከፋዩ አንጻር • ዘመናዊ የሂሳብ አያያዝ እንዲኖር ያደርጋል፣ • ሽያጮችን ለመቆጣጠር ያስችላል፣ • የዕቃ ክምችትን ለመቆጣጠር ያስችላል፣ • በጥቅት የሰዉ ሀይል ስራን መስራት ያስችላል፣ • ጊዜና ወጪን ይቆጥባል፣ • ከግብር ዉሳኔ ጋር በተያያዘ ከባለሥልጣን መ/ቤት ጋር የሚፈጠሩ አላስፈላጊ ክርክሮችን ያስቀራል፣ • በድርጅቱ የተሻለ የአሰራር ስርዓት፣ፈጣንና ቀልጣፋ እንዲሁም ዘመናዊ የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲኖር ያስችላል፡፡
የጎፋ ዞን የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት መምሪያ
ወ/ሪት ዜና ሙሉ
የሴክተሩ ራዕይ፣ ተልዕኮ፤ እሴቶች እና ዓላማ
ቀን 2021-09-23
ራዕይ በ2017 በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ የሆነ አምራች ኢንዱስትሪ ተፈጥሮ እና በዞናችን በገጠርና በከተማ በተፈጠረ የሥራ ዕድል የህብረተሰቡ የኢኮኖሚ እድገት ተረጋግጦ ማየት ነው፡፡ ተልዕኮ በገጠርና በከተሞች ለሚደረጉ የሥራ ዕድል ፈጠራዎች የድጋፍ ማዕቀፎችን በማጠናከርና የሥራ ዕድል በመፍጠር ለኢንዱስትሪ መስፋፋት ምቹ አከባቢ ሁኔታ በመፍጠር ለኢንተርፕራይዞችና ለልማታዊ ባለሀብቱ የላቀ አገልግሎትና ድጋፍ በመስጠት እና የዘርፉን የቴክኖሎጂ አቅም በማሳደግ እንዱስትሪው በተከታታይ በከፍተኛ ደረጃ እንድስፋፋ ማድረግ፡፡ ዕሴቶች • አሳታፍና ቅንጅታዊ አሰራር፤ • የማያቋርጥ ለውጥና መሻሻል፤ • ኪራይ ሰብሳቢነትን መፀየፍ፤ • ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብን እናሰፍናለን፤ • በግልፀኝነትና ተጠያቂነት ማገልገል፤ • ሁሉ አቀፍ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን እናሰፍናለን፤ • በሥራ ውጤት ብቻ መመዘን፤ • መረጃን ለልማት እናውላለን፤ የመምሪያው ዓላማ በዞኑ በከተማ እና በገጠር አካባቢ የሚኖሩ ሥራ አጥ ወጣቶች የመስሪያ ግብዓቶችን በማግኘት በተለያዩ የሥራ መስኮች ተሰማርተው ገቢያቸውን እንዲያሳድጉና የኑሮ ደረጃቸውን እንዲያሻሽሉ ለማስቻል፡፡
ያግኙን
☏046-777-1536
ተዛማጅ ሊንኮች
Copyright © 2021-2025 Gofa Zone Adminstration.All Rights Reserved
Gofa,Ethiopia