የጎፋ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ
አቶ ጃኬቴ ዛይሴ የትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ኃላፊ
የሴክተሩ ራዕይ፣ ተልዕኮ፤ እሴቶች
ቀን 2021-09-15
ራዕይ /Vision/ የዞኑ ኅብረተሰብ እስከ 2020 ሚቹ፤ አስተማማኝና ዘመናዊ የመንገድ አውታርና የተሣለጠ ትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚነት ተረጋግጦ ማየት፤ ተልዕኮ /MISSION/ ለዞኑ ህብረተሰብ የተቀናጀ ልማት ለማምጣት የሚያስችሉ የተለያዩ ደረጃ ያላቸው መንገዶችን በማስጠናት መገንባት፤ መጠገንና ማስተዳደር፤የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ማስፋፋትናማጠናከር፤ የአሽከርካሪዎችንና የተሸከርካሪዎችን ብቃት ማረጋገጥና የህብረተሰቡን የመንገድ አጠቃቀም ግንዛቤ በማሳደግ የትራንስፖርት ተጠቃሚነትንና ደህንነትን እውን ማድረግ፤ መላዉን ህዝብ በማነቃነቅ በዕቅድ ዝግጅት፣ አፈፃፀምና ዉጤት ላይ ማሳተፍ መቻል፡፡ የሴክተሩ መሠረታዊ እምነቶችና ዕሴቶች • ጥራት፣ግልጽነት፣ተጠያቂነትና ፍትሃዊነት ያለው አሠራር የሴክተራችን መገለጫ እናደርጋለን! • ቀልጣፋ አገልግሎትና ዉጤታማነት ማረጋገጥ የተግባራችን ስኬት ዋና መለኪያ ናቸዉ! • ህብረተሰቡን ያሳተፈ ልማት ላይ እናተኩራለን! • በጠንካራ የሥራ ተነሣሽነትና የቡድን ስሜት እንሠራለን! • ያለንን ውስን ሀብቶችን በአግባቡና በቁጠባ እንጠቀማለን! • በጋራ እንሠራለን ስኬቱም ውድቀቱንም የጋራችን ነው! • የሙያ ስነምግባር መጠበቅ መለያችን ነው! • በሰውና በንብረት ላይ የሚደርሰውን አደጋ ለመቀነስ እንጥራለን! • ለደንበኞቻችን እርካታ ቅድሚያ እንሰጣለን! • ዉጤት ያሸልማል!
የጎፋ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ
ኢ/ር ተመስገን ጣሰው
የሴክተሩ ዓላማ፣ ራዕይ፣ ተልዕኮና እሴት
ቀን 2021-09-08
ዓላማ በዞኑ ተወዳደሪና ብቁ የሆነ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ በመፍጠር፣በከተሞች የአካባቢ ልማትን በማፋጠን፣የከተማ-ከተማና የከተማ-ገጠር ትስስርን በማጠናከር ለከተማ ልማት ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ከተሜነትን ማሳደግና ዘላቂ የሆነ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ልማት ማረጋገጥ ነው፡፡ ራዕይ በ2022 በዞኑ ተወዳዳሪ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ በመገንባት ከተሞች ምርታማና የብልጽግና ማዕከል ሆነው ማየት ነው፡፡ ተልእኮ በዞኑ የሚገነቡ ግንባታዎች ወጪ ቆጣቢና ጥራቱ የተጠበቀ፣ከተሞችን በፕላን በመምራት፣ የመሬት አቅርቦት እና አስተዳደርን ግልጽ ቀልጣፋና ፍትሃዊ በማድረግ፣የቤትና መሠረተ ልማት አቅርቦት በማሳደግ፣አረንጓዴ ልማት በማረጋገጥ ከተሜነትን በማስፋፋት ክፍለ ኢኮኖሚውን ማሳደግ ነው፡፡ የሴክተሩ ዕሴቶች • የመንግስት ፖሊሲና ስትራቴጂ የዕቅዶቻችን መርሆዎች ናቸው፣ • የሰው ኃይል ካሉን ሀብቶች ሁሉ ትልቁ ሀብታችን ነው፣ • በማያቋርጥ ለውጥና መሻሻል እናምናለን! • ተገልጋዮቻችን የሕልውናችን መሠረት ናቸው! • ቅሬታ አቅራቢዎች መካሪዎቻችን ናቸው፣
የጎፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
አቶ ተክለማርያም በቀለ
የሴክተሩ ራዕይ፣ ተልዕኮ፤ እሴቶች እና ዓላማ
ቀን 2021-09-06
የተቋሙ ራዕይ የዞኑ ሀብት አድጎ፣ ፍትሀዊ የሆነ የሀብት ድልድልና አጠቃቀም በማረጋገጥ፣ የዞኑ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገትን በማስፈን በ2022 የህብረተሰቡ የኑሮ ደረጃ ተሻሽሎ ለማየት የሚደረገውን ዞናዊ ጥረት የሚያግዝ ተቋም ሆኖ ማየት ፡፡ የተቋሙ ተልዕኮ በቁጠባ ላይ የተመሰረተ የሃብት አጠቃቀም እንዲሰፍን በማድረግ ፣የኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያ ሐሳቦችን ተግባራዊ በማድረግ፣ግልጸኝነትና ተጠያቂነት በሰፈነበት አሰራር ዘመናዊ የእቅድና መረጃ፣ የፋይናንስና የንብረት አስተዳደር ቁጥጥር ስርዓትን በመዘርጋት ፣የልማት አጋሮችን ሃብት በማስተባበር ፣ በዞኑ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ልማት ተግባራዊ ማድረግ ፡፡ የተቋሙ ዓላማ በዞን፣በወረዳና በቀበሌያት በመንግስታዊና ህዝባዊ ተቋማት ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል ሰፍኖ የተለያዩ ፕሮግራሞችን በመተግበር ለተገልጋዮች ግልጸኝነትና ተጠያቂነት በሰፈነ ሁኔታ ፈጣን ቀልጣፋና ተደራሽ አገልግሎት አሰጣጥ ሂደትን በማሳደግ ህብረተሰቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ዉጤቶች ተቋዳሽ እንዲሆኑ ማድረግ ነዉ፡፡ የተቋሙ ዕሴቶች • ቆጣቢነትና፣ • ውጤታማነት፣ • ቀልጣፋ አገልግሎት፣ • ወቅታዊና አስተማማኝ መረጃ፣ • ተቆርቋርነት፣ • ህጋዊነት፣ • ፍትሐዊነት፣ • ግልፀኝነትና ተጣቂነት • በዕቅድ መመራት፣
ያግኙን
☏046-777-1536
ተዛማጅ ሊንኮች
Copyright © 2021-2025 Gofa Zone Adminstration.All Rights Reserved
Gofa,Ethiopia