የጋብቻ ሥርዓት በኦይዳ ብሔረሰብ
ቀን 2021-09-03
ቅድመ-ጋብቻ በኦይዳ ብሔረሰብ የኦይዳ ብሔረሰብ የማንነት አሻራ ከሚየንፀረቁ በርካታ ባህላዊና ማህበራዊ እሴቶች መካከል ባህላዊ የጋብቻ ሥርዓት አፈፃፀም አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ አንድ ሰው ብሔረሰቡ ማህበራዊና አስተዳዳራዊ ጉዳዮች ዉስጥ ለመሳተፍና ተቀባይነትን ለማግኘት የጋብቻ ሁኔታ አስተዋፅኦ ይኖረዋል፡፡ ትዳር መስርቶ የሰከነ ኑሮ መምራት ያልቻለ ግለሰብ በብሔረሰቡ ዉስጥ ለተሻለ ኃላፊነት ሊታጪና የመሪነት ደረጃ ሊያገኝ አይችልም፡፡ ስለሆነም ጋብቻ ዘር ለመተካት ከሚኖረው አስተዋጽዖ ባሻገር በብሔረሰቡ ዉስጥ የሚኖረውን ኃላፊነትና ተሰሚነት ለማሳደግ ሚና አለው፡፡ በብሔረሰቡ ጋብቻ እንዲመሰረቱ ከሚያስገድዳቸው በርካታ ምክንያቶች መካከል የወላጆቻቸው ፍላጎት ዋነኛው ስሆን በአብዛኛው ጊዜ ወላጆች ልጆቻቸው ትዳር ይዘው ጎጆ መሥረተው ዘራቸው ቀጣይነት እንዲኖረው የልጅ ልጅ ማየትን፣ እድሜያቸው እየገፉ ሲሄድ ጉልበታቸው እየደከመ ስመጣ የሕይወታቸው መሠረት ለሆነው እርሻና ተጓዳኝ ተግባራት አጋዥ ለማግኘት እና በእርጅና ወቅት ጧሪ ቀባሪ እንዳያጡ በሚል እንደሆነ የዕድሜ ባለፀጋዎች ያስረዳሉ፡፡ ጋብቻ በብሔረሰቡ ትልቅ ሥፍራ የሚሰጠው ከመሆኑም ባሻገር ማህበራዊ ክብሬታና ዕውቅና ያጎናጽፍል ፣ አንድነትና ጥምረት ለመፍጠር ፣ ትውልድ እንዲቀጥል ልጅ ለመወለድ ፣ የዝምድና የደም ትስስርን ለመፍጠር ጋብቻ ዋንኛው ማህበራዊ ተቋም ነው፡፡ በአጠቃላይ ሁለት ተቃራኒ ፆታዎች በፊቃደኝነት ላይ የተመሠረት ብቻ ሳይሆን የተጋቢዎች ቤተሰብ ስምምነት እና ይሁንታ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ስለሆነም ጋብቻ ሁለት ተጣማሪዎች የሚመሰረቱት ማህበራዊ ውል ሲሆን ቢያንስ ሰዎች በጋራ ለመኖርና በሕዝብ ዉስጥ ማህበራዊ ዕውቅናና ክብሬታ ትውልድ ለመተካት ሲባል የሚፈጠር ማህበራዊ ተቋም ነው፡፡ የመተጫጨት ሥርዓት በኦይዳ ብሔረሰብ በአብዛኛው በቤተሰብ ስምምነት ሊሚፈፀም ባህላዊ ጋብቻ በሁለቱም ቤተሰቦች ዘንድ ከፍተኛ ትኩረት ከሚሰጣቸው ጉዳዮች መካከል የዘር ሀረግ ፣ ጐሳ አቻነትና ሀብት እንደሆነ የሀገር ሽማግሌዎች ያስረዳሉ፡፡ የልጁ ቤተሰቦች ወይም የልጁ አባት ልጃቸውን ለአቅመ አዳም መድረሱን ሲያውቁ ለልጃቸው ሚስት የሚትሆን ልጅ ለማጨት ከቤተ-ዘመድ ጋር ይመካከራሉ፡፡ ከምክክር በኋላ በልጁ አክስትና እህት በኩል ለልጁ ትመጥናለች ብለው የሚያስቧትን ልጃገረድ ምርጫ ያደርጋሉ፡፡ ለልጁ ወይም ለቤተሰቦቹ ጥቆማ ይደረጋል፡፡ ልጁም በተነገረው ጥቆማ መሠረት ከጓደኞቹ ጋር በመሆን ልጅቱን የሚያዩበትን አጋጣሚዎችን ይጠባበቃል፡፡ የኦይዳ ብሔረሰብ ልክ እንደሌሎች ብሔረሰቦች የመተያየትና መተጫጫት አጋጣሚዎች የሚፈፀሙት ባህላዊ በዓላት፣ በሠርግ፣ በለቅሶ ቦታና በገበያ እና በሌሎች አጋጣሚዎችን ….. ወዘተ በመሳሰሉት ነው፡፡ በዚህ መሠረት የመታየት ዕድል የገጠማት ልጃገረድ በልጁና ቤተሰቦች ተቀባይነት ካገኘች የልጁ አባት ታዋቂ የሀገር ሽማግሌዎች ከራሱ ይዘው ወደ ልጅቱ አባት ቤት ይሄዳሉ፡፡ የጋብቻ ዓይነቶች በኦይዳ ብሔረሰብ በኦይዳ ብሔረሰብ በተለያዩ ወቅቶችና በአጋጣሚዎች የሚፈፀሙ አራት ዓይነት ባህላዊ የጋብቻ ዓይነቶች አሉ፡፡ የየራሳቸው ባህላዊ የአፈፃፀም ሥርዓት እንዳላቸው በመቀጠል ለማየት ተሞክሯል፡፡ 1. የስምምነት ጋብቻ (Yi7isintte/Kadhe)፡- ባህላዊ ጋብቻ ሥርዓት በብሔረሰቡ ከጅምር እስከ ፍፃሜ ትልቅ ሥፍራ የሚሰጠው ሥርዓት ስሆን ጥንት በኦይዳ ብሔረሰቡ ጋብቻ በአብዘኛው በተጋቢዎች ቤተሰብ አቻነት ላይ ተመስርተው እንደሚፈፅም ለገንዘብ ተችሏል፡፡ የስምምነት ጋብቻ (Kadhe) በኦይዳ ከሚጠቀሱ የጋብቻ ዓይነቶች አንዱ ስሆን አፈፃፀሙ በሁለቱ ወላጆችና ቤተ-ዘመዶች ፊቃደኝነትና ይሁንታ ላይ ተመሰርተው የሚከናወን ስሆን በብሔረሰቡ ባህል በቅድሚያ በሁለቱ ወገኖች መካከል ዘር ሀረግ ጎሳ ግንኙነትና የደም ትስስር አለመኖሩ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡ ከጎሳ አቻነት በተጨማሪ የልጅቱ መልካም ሥነ-ምግባርና በህብረተሰቡ ዘንድ ያላት ተቀባይነት እንደመመዘኛ መስፈርት ይወሰዳል፡፡ በዚህ መሠረት በኦይዳ ብሔረሰቡ ሽማግሌ ወደ ልጅቱ ቤተሰብ የሚላክባቸው ቀናት በባህሉ የሴት ቀናት እርጥብ ብለው የሚጠራቸው ማክሰኞ ፣ ሐሙስና ቅዳሜ ዕለታት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ስለሆነም የልጁ አባትና አባት ከሌለው አጎት አንድ ታዋቂ የሀገር ሽማግሌ በመያዝ ከላይ ከተጠቀሱት ዕለታት በአንዱ ወደ ልጅቱ ቤተሰቦች ለጥየቃ ይከዳል፡፡ በዚህ መሠረት በነባሩ የብሔረሰቡ ባህል ወግና ልማድ የልጅቱ ቤተሰቦች ለሽምግልና ለመጡት ሽማግሌዎች የተለያዩ ምክንያቶች በማቅረብ እንደየአሰፈላጊነቱ እስከ ሦስት ጊዜ ድረስ አለመስማማታቸውን በመግለጽ ሊያመላልሳቸው ይቻላል፡፡ በመቀጠልም በተደጋጋሚ ሽማግሌዎች ከተመላለሱ በኋላ የልጅቱ ቤተሰቦች የመጡበት ምክንያት ይጠይቃሉ፡፡ ሽማግሌዎችም እቤታችሁ ያለችሁን ልጅቱን ስለወዳዳት /Na7a Na7a kadheezin/. በማለት ይገልፃሉ፡፡ የልጅቱ ወላጆች የሽማግሌዎች ጥየቃ ካዳመጡ በኋላ ከዘመድ አዝማድ ጋር ተመካክረን መልሱን እናሳውቃቸዋለን በማለት የቀጠሮ ቀን ሰጥተው ይሸኟቸዋል፡፡ ሽማግሌዎቹ በቀጠረው ቀን ተመልሰው እስክ ደርሱ የልጅቱ ቤተሰቦች ስለልጁ መልካም ፀባይ በህብረተሰቡ ዘንድ ስላለው ተቀባይነት እና የማስተዳደር አቅም ጭምር ከቤተ-ዘመድ ጋር በመሆን በትኩረት ይመካከራሉ፡፡ በቀጠረው ቀን ስመለሱ የልጅቱ ቤተሰቦች ሽምግልናውን ተቀብለው ይሁንታን ከሰጡ በኋላ በብሔረሰቡ ባህል መሠረት /Yih! Yo! /Doona buge/ አፍ መፍቻ በቀደሙ ጊዜያት ከወላጆቿ ከአንድ እስከ አምስት ጠገራ ብር /Xagara Bira/ የሚሰጥ ስሆን በተመሳሳይ መልኩ ለልጅቱ ደግሞ የማጌጫ /Moonno/ አምባር የብር ቀለበት በማጥለቅ ባህላዊ የመዋብያ ጌጦችን በማበራከት /Ma7sida/ መታጨቷን አረጋግጠው በልጅቱ ቤተሰቦች የተዘጋጀውን ባህላዊ ምግብና መጠጥ በልተውና ጠጥተው ለሠርጉ ቀን ቀጠሮ ተቀብለው ይለያያሉ፡፡ ይህ ሁሉ ፆማ ጐሳ ከሆነ ነው፡፡ በማላዎች ቤት ሽምግልና አይላክም እነርሱ ለፆማዎች ቤት ብቻ ይልካሉ፡፡ በኦይዳ ብሔረሰብ የሠርጉ ቀን ቀጠሮ ዕለት ሙሽሪት እቤት ስትሆን የሙሹራው የቅርብ ዘመዶች አጃቢ ጓደኞቹ ወደ ሙሽሪት ቤት ለመውሰድ ስሄዱ ሙሽሪት ከቤት ወጥታ ደጅ ላይ ትጠብቃለች፡፡ ነገር ግን በመሄድ የተዘጋጀላቸውን ባህላዊ ምግብና መጠጥ ተስተናግደው ሙሽሪትን አጅበው እየጨፈሩ ይዘው እየሄዱ ወንዝ አጠገብ በሚደርሱበት ጊዜ ሙሽሪት ትቆማለች፡፡ አትሻገርም በዚህ ጊዜ በብሔረሰቡ ባህል የሙሽራው ሚዜ በጀርባው አዝሏት ያሻግራል፡፡ ወደ ሙሹራው ቤት በር ላይ እንደደረሰች የሚትቆም ስትሆን መምጣታቸውን የሚጠባበቀው ሙሹራው ሙሽራዋን ገንዘብ ስጦታ በመስጠት ወደ ግብዣ በመቀበል እጇን በመያዝ ወደ ቤት ያስገባታል፡፡ የሙሹራው አጃቢዎች የሙሹራው ቤተሰብ የተዘጋጀላቸውን ምግብና መጠጥ ከተስተናገዱ በኋላ ከሙሹራው ቤተሰብ ጎጆው መውጫ ስጦታ ጋቢ ፣ ግደር ፣ ላምና ብር ይበረከታል፡፡ ከዚህ ሥርዓት በኋላ በማጀብ ወደ ጫጉላ ቤት ከገባች በኋላ አጃቢው ሠርገኞች ቤቱን ለቀው እንዲወጡ ይደረጋሉ፡፡ የሙሹራው ጓደኛው የሙሽሪትን ልብሷን አውልቃ መኝታ ላይ ታስተኛለች በዚህ ጊዜ አይዞሽ በርቺ በማለት መክራ ትሄዳለች፡፡ ከዚህ በኋለ፤ ሙሹራው ለግንኙነት ስቀርባት በእሽታ አታስተናግድም፣ ታታግለዋለች፡፡ ይሁን እንጂ በጉልበት ታግሏት ክብረ-ንጽህኗን ይወስዳል በዚህ ጊዜ ትጮሃለች፡፡ ይህንን የሰሙት ቤተሰብ እንኳን ደስ አላችሁ ይባባላሉ፡፡ እርስ በርስ ደስታቸውን በጋራ ይገልፃሉ፡፡ በማግስቱ ሙሹራውና ጓደኞች ወደ ሙሽሪት ቤተሰብ የምስራች ደስታ ለመግለጽ እየጨፈሩ ይሄዳሉ ፡፡ እዚያም ከቤተሰብ ዘመድ-አዝማድ ጋር ስበሉና ስጠጡ ውለው በመጨረሻ ለሙሹራዎች ጎጆ መውጫ እንደየአቅማቸው ይሰጣጣሉ፡፡ ከዚህ በኋላ መርቀው ውለዱ ፣ ክበሩ ብለው ይሸኛሉ፡፡ 2. ጠለፋ /Gochchi Eke/:- ቀደም ስል ጠልፎ ማግባት አንድ የህብረተሰቡ የባህላዊ ልማድ ስሆን በኦይዳ ብሔረሰብ ይህንን ጋብቻ ሥርዓት እንዲከናውን የሚያስገድዱ በርካታ ምክንያቶች አሉ፡፡ አነሱም ፡- አገብው ልጅቷን ወደው ወይም አፍቅረው ልጅቷን ሆነ ቤተሰቦቿ ተጠይቀው ፊቃደኛ ሳይሆኑ ስቀሩ፣ ልጅቱ ታጭታ እያለች ሌላ ሰው ቀድሞ ሊያገባት ነው የሚል ወሬ ከሰማ ወይም ጥርጣሬው ስኖር፣ ልጅቱም ሆነ ቤተሰቦቿ ጋብቻውን ከተቀበሉ በኋላ የሠርጉ ቀነ ቀጠሮ ከመድረሱ በፊት ሌላም ሰው ልጠልፋት ይችላል በሚል ጥርጣሬ ስፈጥር፣ ተዋዶው ሳሉ ቀጠሮ ሲያራዘሙ ሊጠልፋት ይችላል ፡፡ ጠለፋውን የሚያስከደው ልጅቱ ውሃ ለመቅዳት ወደ ወንዝ ስትሄድ ፣ ለእንጨት ለቀማና ለሣር አጨዳ ከመንደር ወደ ራቅ ያለበት ቦታ ስትሄድ እና ከገበያ በሚትመለስበት ጊዜ ነው፡፡ አልፎ አልፎ ጠለፋው ከመካሄዱ በፊት ልጁ ለልጅቱ ያለው ፍቅር ለመግለጽና ልጅቱን እንደሚፈልጋት ለማሳወቅ የተለያየ ስጦታዎችን በልጅቱ አክስት አማካኝነት ለልጅቱ ይሰጣል፡፡ ጠለፋ ከተከናወነ በኋላ ልጁ ልጅቷን ይዘው ለጊዜው ይሰወራል፡፡ ነገር ግን በልጁ ወገን ባሉ ሽማግሌዎች የልጅቱን ቤተሰቦች እንዲረጋጉ ይደረግና ጉዳዩ በሽማግሌ ይያዛል፡፡ የልጁ ቤተሰቦች የልጅቷና ለቤተሰቦቿ በባህሉና ወጉ መሠረት አስፈላጊውን ነገር ሁሉ ያሟላሉ፡፡ 3. ወዶገብ /Beta/፡- የዚህ ዓይነት ጋብቻ በኦይዳ ብሔረሰብ ዘንድ ጋብቻ ቀደም ስል በሰፊው የተለመደ ስሆን አሁን ላይ አልፎ አልፎ እንደሚፈፀም ይታወቃል፡፡ ለዚህ ዓይነቱ ጋብቻ ምክንያት ከሚሆኑ ጉዳዮች መካከል ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉ ናቸው፡፡ የ”ማላ” ዘር ሆና ሰው ሁሉ ደፍሮ ለመጠየቅ ስፈራ ሳታገባ ብዙ ጊዜ የቆየች እና ዕድሜዋ እየገፋ ስሄድ፤ በጣም የሚትወደው ልጅ ሌላ ሊያገባ ነው የሚል ወሬ ከሰማች ልጁ ጀግና ሥራ ወዳድ በዘሩ የተከበረ በሀብቱ እና በቁመና …. ወዘተ የሚመረጥ ከመሆኑ የተነሳ ብዙ ልጃገረዶች የሚወዱት ከሆነና ልጁቱ ቀድማ ልታገባ ከፈለገች በአጠቃለይ ከላይ በተጠቀሱት ምክንያች በአንዱ የተነሳ ልጁን ለማግባት የፈለገች ሴት ራሷን ቅድመ ዝግጅት ካጠናቀቀች በኋላ የሚትሄድበትን ቀን በማመቻቸት በቀጥታ ጓዟን ጠቅሊላ ይዛ ወደ ልጁ ቤት ገብታ ቁጭ ትላለች፡፡ በዚህ ግዜ የልጁ እናት ለምን እንደመጣች ስትጠይቅ ልጃችሁን ወድጄ ልኖር ዘር ላፈራ ነው የመጣውት በማለት መልስ ትሰጣለች፡፡ ልጁ እናት የልጅቱን መልስ ከሰማች በኋላ ወንድ ልጁን ትጠይቃለች፡፡ ልጁ ወደው ቤተሰቦቹ ቤት ድረስ የመጣችውን ልጃገረድ የሚወዳት ከሆነ ጉዳዩን በሽምግልና ያልቃል፡፡ ነገር ግን ልጁ እንደማይወዳት ካሳወቀ በማህበረሰቡ ባህል፣ ወግና ሥርዓት መሠረት ወዳ የመጣችሁን ሴት ልጅ ወንዱ የማትፈለጋት ከሆነ በስጦታ መልክ ጋቢ ተጥተዋት በልጁ እህቶች አማካኝነት ትሸኛለች፡፡ በተጨማሪ ወዳ የመጣች ልጃገረድ ለንጉስ /Kaati/ ዘር ከሆነች በስጦታ መልክ ጊደር ተበርክቶላት በክብር ትሽኛለች፡፡ በአጠቃላይ በኦይዳ በብሔረሰቡ ባህል ወዳ የመጣች ልጃገረድ ጋብቻው በልጁ በኩል ተቀባይነት ካላገኘ አስፈላጊውን ስጦታ ተቀብላ በክብር ትሸኛለች እንጂ ዝም ብለው ከቤት ማስወጣት በማህበረሰቡ የተወገዘ ነው፡፡ 4. የዉርስ ጋብቻ /Mahe/:- የዉርስ ጋብቻ በኦይዳ ብሔረሰብ ራሱ የሆነ አፈፃፀም ሥርዓት ያለው ስሆን አንድ ባል የሞተባት ሴት ከተወሰነ ጊዜ ቆይታ በኋላ የሟች ቤተሰብ ከሟች ሚስት ጋር በመካከር የሟች ታናሽ ወንድም ወይም የአጎት ልጅ የሟች ሚስት እንዲወርስ የሚደረግ የጋብቻ ዓይነት ነው፡፡ በተጨማሪ የዉርስ ጋብቻ መከሰቻ አጋጣሚዎች ሚስት የሞተችበት ባል የሚስቱን እህት በሁለቱ በቤተሰቦች ስምምነት እንዲወርስ የሚደረግበት ሥርዓት እንዳለ ያስረዳል፡፡ በሌላ አገላለጽ የዉርስ ጋብቻ ብዙ ጊዜ በሁለቱ ቤተሰቦችና በሟቿ ሚስት መካከል በሚደረገው በጋራ ስምምነት ይፈፀማል፡፡ ይሁን እንጂ የዉርስ ጋብቻ የሚመሰረትበት የራሱ የሆነ መገለጫዎች እንዳሉት ከዚህ በመቀጠል ለማየት ተሞክረዋ፡፡ ሟች በሕይወት ዘመኑ ያፈራውን ሀብት ንብረት በሌላ ባዕድ እጅ ገብተው እንዳይባከን የሟች ልጆች በእንጀራ አባት እንዳይበደሉ የሟች ቤተሰቦች የሟቹን ልጆችና በቅርበት እንዲከባከቡና እንዲጠብቃቸው የሟች እህት በእናትነት መንፈስ እየተንከባከበች እንዲታሳድግ ጭምር እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡ በዚህ ጋብቻ ሥርዓት በሟች ቤተሰብ ዉስጥ ሴት ልጅ ከሌላ ቤተሰብ ተመርቀው ሌላ እንድያገባ ይፈቀድለታል፡፡ ይሁን ኢንጂ ከላይ በተመለክተናቸው ዉርስ ጋብቻ ሥርዓቶች በአሁን ወቅት ይህ ተግባር እየቀነሰ መምጣቱን ለመገንዘብ ተችለዋል፡፡ በሌላ ደግሞ በኦይዳ ብሔረሰብ አልፎ አልፎ ሚስት በበሽታ ምክንያት እና በተፈጥሮ መሀን ስትሆን መውለድ ሳትችል ስትቀር ቤተሰብ ከመከረ እና ሚስት ከተስማማች አባወራው በኋላ ከአንድ ሚስት በላይ ለማግባት የሚገደድበት ሁኔታ ይፈጠራል፡፡ የ”ሶፋ” /Soofa/ መዝናኛ በኦይዳ ብሔረሰብ የ”ሶፋ” /Soofa/ ሥርዓት በኦይዳ ብሔረሰብ ከጋብቻ በኋላ ከጫጉላ ቤት ቆይታ ስወጡ ከቤተሰብና ከህብረተሰቡ ጋር በመጀመሪያ ጊዜ ከመቀላቀል ቀጥሎ ማህበራዊ ዕውቅና ለማግኘት ስባል ሁለቱም ተጋቢዎች ከጓደኞቻቸው ጋር በገበያ ስፍራ የሚፈፀም ባህላዊ የመዝናኛ ሥርዓት ስሆን ለህብረተሰቡ ከጫጉላ ቤት ቆይታ በኋላ በይፋ ይታዩበትና የሙሹራው ቤተሰብ የሀብት መጠን የሙሹሮች ተክለ-ሰውነት ደንግባት የሚለካበት ስለሆነ ቤተሰብም በተቻለ መጠን ከህብረተሰቡና ከልጅቱ ቤተሰብ ትችትና ወቀሳ ለመዳን ሙሹሮችን በጫጉላ ቤት ቆይታ ጊዜ በደንብ ይንከባከባሉ፡፡ አብዛኛው ሥርዓቱ የሚከበረው በገበያ ሥፍራ ስሆን በጓደኞቻቸው ታጅበው በባህላዊ ዘፈን በእልልታና በጭብጨባ ገበያውን ከዞሩ በኋላ ሥርዓቱ ወደሚፈፅበት ገበያ ዳር ከሚገኝ ጥላ ሥር በመሄድ እየበሉና እየጠጡ ሥርዓቱን ያከብራሉ፡፡ ከዚህ ሥርዓት በኋላ ሙሹሮችና ታዳሚዎች እርስ በእርስ እየተመራረቁ ታጅበው እንደመጡ ታጅበው በዘፍንና በጭፈራ ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ፡፡ በአጠቃላይ ከዚህ ሥርዓት በኋላ ሙሹሮች በማንኛውን ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ መሳተፍ የሚጀመርበት በመሆኑ የሶፋ /Soofa/ ሥርዓቱ በብሔረሰቡ ዘንድ ለዘመናት ስከበር መቆየቱ መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡ አያ “Aya” በብሔረሰቡ አንድ ወንድ ሚስት ካገባ መጀመሪያ ሴቷ በአባቷ ጐሳ ስትጠራና ስትታወቅ የነበረችውን ሴት በባሏ ጐሳ ተቀላቅላ በብሔረሰቡ ባህል የእርሱ ናት እንዲትባል የሚያደርግ ስጦታ ዓይነት ነው፡፡ ይህ ሥርዓት ካልተፈፀመ ባሏ በእርሷ ቤተሰብ ዘንድ ሁሌም እንደ ባለዕዳ ስለሚቆጠርና በሕዝቡ ዘንድ ሙሉ ሰው ስለመሆኑ ማረጋገጫ ስለማይሰጠው የአያ ሥርዓት በባልና ሚስት ቤተሰብ ዉስጥ ለዝምድና ማጠናክሪያ እንደ አምድ ይወሰዳል፡፡ ሌላው የአያ ሥርዓት /ሥጦታ/ የሰጠ በሚሰቱ ላይ ለሚደርሰው ማንኛውም ጥቃትና ጉዳት ሙሉ ኃላፊ ወይም ባለቤት በመሆን ስለእሷ የመከራከርና መብቷን ለማስከበር ሥልጣን አለው፡፡ ከሞተች በራሱ ጐሳ መቃብር የመቅበር ሥልጣን አለው፡፡ ይህ ሥርዓት ካልተፈፀመ ለደረሳት ጉዳት የመቆም ኃላፊነት የለውም ብትሞት በራሱ ጐሳ መቃብር የመቅበር ዕድል ስለማይኖረውና በሕዝብ መቃብር /ħayle Booza/ ስሚትቀብር የሞራል ክሳራ ጭምር ስለሚያጋጥም የአያ ሥርዓት ስጦታ በመስጠት የሁለቱም ጎሳ አካላት መተሳሰር ሥርዓት መፈፀም ለባል ግዴታ ነው፡፡ ላአሣ/ዣጋና/ “Laa7asa/Zhagana/” የአያ ሥነ-ሥርዓት ከጨረሱ በኋላ በልጅቱ ቤተሰብ የሚፈፅ ሥርዓት ስሆን በአሁን ዘመናዊ አጠራር መልስ ወይም ሠርግ እንደምባለው የልጅቱ ቤተሰብ የአያ ሥርዓትን የተከተለ ድግስ አዘጋጅተው ልጁና ልጅቱን የመመረቅና መልሰው የፍቅር ስጦታ የመስጠት ግዴታ አለባቸው፡፡ በተጨማሪም የሁለቱ ተጋቢዎች ቤተሰቦች የሚቀላቀሉበት ፕሮግራምም ነው፡፡
እምነት
ቀን 2021-09-03
ጥንታዊ ማህበረሰቦች የአኗኗር ግንኙነት ሥርዓት ዉስጥ ከሚከሰቱ ማህበራዊ ለውጦች ሳቢያ የሚገጥማቸውን ሰው ሰራሽና ተፈጥሮአዊ አደጋዎችን ለመከላከል ይረዳናል ብለው ስለሚያምኑ ባህላዊ የአምልኮ ሥርዓት ይፈፀማሉ፡፡ ይህ ባህላዊ አምልኮ ሥርዓት በግለሰቦች መካከል እንዲሁም ግለሰቦች ከማህበረሰቡ ጋር ጤናማና ሠላማዊ ግንኙነት እንዲፈጥሩ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት የዘርፉ ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡ ከጥንት ጀምሮ ከሰው ልጅ ባህላዊ የአምልኮ ሥርዓት የሚፈፀመው በሽታ ፣ ረሀብ ፣ ጦሪነት እንዳይከሰት ከመሆኑም በተጨማሪ ረጅም ዕድሜ እንዲሰጣቸው ፣ ልጆችን ለመወለድ ፣ ወደ እርሻ ተግባር ለመግባት ፣ ምርት ለመሰብሰብ ፣ ከብቶች እንዲራቡና ከድርቅና ከተምች ወረርሽን ለመከላከል የተለያዩ ባህላዊ ሥርዓቶችን በመፈፀም እምነታቸውን ይጠቀማሉ፡፡ በኦይዳ አካባቢ የክርስቲናና እስልምና ሐይማኖት ከመግባታቸው አስቀድሞ ጥንት ሰዎች እምነት ስጀምሩ የአባት ፣ የአያትና የቅድመ-አያቶቻቸው አማልክት በማምለክ እንደጀመሩት መረጃ ሰጪዎች ያስረዳሉ፡፡ ይሁን እንጂ የተፈጥሮ ክስተቶች መብረቅ ንፋስና ዝናብ የእንስሳት በሽታ እና በአገር ላይ ድርቅ እንዳይከሰት ….. ወዘተ የመሳሰሉትን ለመከላከል የአባትና እናታቸው አምላክ /Xoozi/ መልካም ነገር እንዲያመጣላቸው በተመረጡ በባህላዊ አምልኮ ሥፍራ ባህላዊ መሪ በቢታን በህዝብ ላይ ጉዳት እንዲያደርስ የእንስሳት እርድ መስዋዕት ይፈፀማል፡፡ እነዚህ ከላይ የተመከልናቸው ባህላዊ እምነቶች በኦይዳ በአብዛኛው የህብተረሰብ ክፍል ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ዉስጥ በመግባት ተፅዕኖ የሚፈጥሩ ባህላዊ ተቋሞች ናቸው፡፡ የኦርቶዶክስ ክርስቲና ኃይማኖት ወደ አካባቢ የገባው በ1890ዎች የወራሪው የሚኒልክ ሠራዊትን ተከትሎ እንደነበር ይናገራሉ፡፡ ኃይማኖቱ ወደ አካባቢው ከገባ ረጅም ጊዜ ብሆንም የቆይታ ያህል በአካባቢው በሰፊው እንዳልተስፋፋ መረጃ ሰጪዎች ያስረዳሉ፡፡ እንደ ኦርቶዶክስ ሁሉ የፕሮቴስታንት ኃይማኖት ወደ አካባቢው የገባው በ1920ዎች በሱዳን ኢንተሪየር SIM/sudan interior mission/ አማካኝነት እንደሆነ ይናገራል፡፡ ምንም እንኳን ከላይ ከተመለክትናቸውን የክርስቲና ኃይማኖት ቁጥራቸው ከፍተኛ ብሆንም አሁን ላይ ባህላዊ የአምልኮ ሥርዓቶች በአንዳንድ አከባቢዎች እንደሚስተዋሉ ለመገንዘብ ችለናል፡፡ በአጠቃላይ የእነዚህ የእምነት ተቋማት ማህበረሰቡን አንድ ላይ በማሰባሰብ የሰዎችን እርስ በርስ ግንኙነት በማሻሻል የህብረተሰቡን አንድነት በማስጠበቅ እንድሁም ግጭቶችን በማስወገድ እና የአገርን ደህነትና ሠላም በመስጠበቅ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዳበረከቱ በአከባቢው ነዋሪዎች ይነገራል፡፡
ባሕላዊ የፀጉር አሰራር በኦይዳ ብሔረሰብ
ቀን 2021-12-15
የኦይዳ ብሔረሰብ እንደ ሌሎቹ የኦሞቲክ ሕዝቦች የራሳቸዉ የሆነ ባሕላዊ የፀጉር አሠራር ዓይነቶች አሉዋቸዉ፡፡ እነዚህ ዞኬ (zokke)፣ ጎፋሬ (Goofare)፣ ጭሬ (ciire)፣ ጉሌ (Guulle)፣ ዴራ (deera/duuro)፣ ጩቄ (Cuqqe)፣ ሜዴ (Meede)፣ ጉቴ (guute)፣ እሽሜ (Ishimme) እና ብንድሬ (Bindire) የሚባሉ ሲሆኑ፤ ቀጥለን በዝርዝር አሠራራቸውን እንመለከታለን፡፡ ዞኬ (zokke)፡- ይህ ባሕላዊ የፀጉር አሠራር በወጣት ወንዶች የሚዘወተር እና ከአናት እስከ ማጅራት የመሀሉን ክፍል ፀጉር በመተው ግራና ቀኝ ከጆሮ ግንዳቸው ከፍ ብሎ ያለውን በመላጨት የሚሠሩት የፀጉር አሰራር ዓይነት ነው ፡፡ ጎፋሬ (Goofare) ፡- ይህ ባሕላዊ የፀጉር አሰራር ለሁለቱም ፆታዎች ማለትም ከአሥራ ሁለት ዓመት ዕድሜ በላይ ላሉ ሴቶች እና ከአሥራ አምስት ዓመት ዕድሜ በላይ የሆኑ ወጣት ወንዶች ፀጉራቸውን በማሳደግ እና በማጎፈር ንጽሕናውን በመጠበቅ የሚያሳድጉት ባሕላዊ የፀጉር አሰራር ዓይነት ነው፡፡ ጭሬ (ciire)፡- በመሀሉ የአናታቸዉን ክፍል ፀጉር በማሳደግ ከሥር ዙሪያውን የሚላጩት ዓይነት ሲሆን፤ ይህንንም አሠራር ሁለቱም ፆታዎች የሚጠቀሙበት የፀጉር አሠራር ዓይነት ነው፡፡ ጉሌ (Guulle)፡- ይህ ባሕላዊ የፀጉር አሰራር በሕፃናት ፣ በወጣቶች እና በአዋቂዎች ፣ በእመጫት ወይም በአራስ ሴቶችም ጭምር የሚዘወተር የፀጉር አሰራር ሲሆን የፀጉር ተባይን ለመከላከል እና ለጤና አጠባበቅም ጭምር ሙሉ በሙሉ ፀጉራቸውን የሚላጩት ሲሆን አዲስ ፀጉር እንዲበቅልም ሲፈለግ የሚጠቀሙት የፀጉር አሠራር ዓይነት ነው፡፡ ዴራ (deera):- ይህ ባሕላዊ የፀጉር አሰራር በሁሉም ፆታዎች በሕፃንነት ዕድሜ የሚሰሩት የፀጉር አሠራር ዓይነት ሲሆን ቅቤ በመቀባት ፀጉራቸውን በማሳደግ ተጠቅልሎ ወደታች እንዲወርድ የሚጠቅሙበት የፀጉር አሠራር ዓይነት ነው፡፡ ሜዴ (Meede):- ይህ ባሕላዊ የፀጉር አሰራር በሁለቱም ፆታዎች በሁሉም የእድሜ ደረጃ የሚሰሩት አሠራር ሲሆን ፀጉራቸውን አሳጥረው በመቆረጥ ወይም በመከርከም የሚጠቀሙበት የፀጉር አሠራር ነው፡፡ ጉቴ (guute)፡- ወንዶች ልጆች ዕድሜያቸው ከስድስት እስከ አሥራ ሁለት ዓመታት ዉስጥ ሲገኙ ለከብት ጥበቃ መድረሳቸውን ለማመላከት የሚሰሩት ባሕላዊ የፀጉር አሠራር አይነት ነው፡፡ ጉሽቱሬ (gushture):- ይህ የፀጉር አሰራር ዞኬ የተባለው የፀጉር ልጨት ከተከናወነ በኋላ የራስ ፀጉርን በእንክብካቤ የሚያሳድጉበት የፀጉር አያያዝ ዘዴ ነው፡፡ እሽሜ (Ishime)፡- ለአቅመ-ሄዋን የደረሱ ልጃገረዶች የሚያዘወትሩት የፀጉር አሰራር ሲሆን በሌላ አገላለፅ ለጋብቻ መድረሳቸዉንም ጭምር ማሳያ ነዉ፡፡ ኤሴ (Binddire)፡- ይህ ፀጉራቸውን ለማስረዘም ወይም ለማሳደግ የሚሰሩት የፀጉር አሠራር ዓይነት ነው፡፡
ያግኙን
☏046-777-1536
ተዛማጅ ሊንኮች
Copyright © 2021-2025 Gofa Zone Adminstration.All Rights Reserved
Gofa,Ethiopia