የኦይዳ ብሔረሰብ ባህላዊ ጫዋታ
ቀን 2021-09-03
ሰዎች ከጥንትም ጀምሮ በቡድንም ሆነ በነጠላ የተለያዩ ባህላዊ ጫዋታዎችን በደስታም ሆነ በሀዘን ጊዜ የሚጫወቱ ስሆን እግረ-መንገዳቸውን ወላጆች ለልጆቻቸው ባህሉን ወጉን እና ሥርዓቱ ያስተምሯቸዋል፡፡ በተጨማሪ ሰዎች በጫዋታ ወቅት እድሜና ፆታ መሠረት ባደረገ መልኩ በግለሰብ ፣ በቡድንና በማህበረሰብ አቀፍ በህብረት አልያም ጎራ ለይተው ለመዝናናት ፣ ጥንካረና ብቃትን ለማሳየት ፣ የተለያዩ የማህበረሰቡን አስተሳሰብና ፍልስፍና የሚያንፀባርቁ ጉዳዮች ለማስረፅ ባህላዊ ጫዋታዎችን ይጫወታሉ፡፡ በዚህ መሠረት ኦይዳ ብሔረሰብ የሚዘውተረውን ባህላዊ ጫዋታዎች ከዚህ በታች ዋና ዋናዎች እንደሚከተለው ተቀምጧል፡፡ ጦር ወርውራ /toora woringge/ luuxxe /ሰበቃ/ ይህ ባህላዊ ጨዋታ በኦይዳ ብሔረሰብ በአብዘኛው በወጣቶች የሚዘውተር ስሆን በማንኛውን ሰዓትና ወቅት የሚጫወቱት የጫዋታ ዓይነት ነው፡፡ ብሔረሰብ ጥንት ለአደን ትልቅ ቦታ ስለሚሰጥ ባህላዊ የጦር ዉርወራን /ሰበቃ/ እንደ ዒላማ መለማመጃነት ስለሚጠቀሙና አድነው መግደል በማህበረሰቡ ዘንድ ማህበራዊ ክብርና ዕውቅና የሚያሰጥ በመሆኑ ከቤት ጦር ይዘው ስወጡ ገድለው እንደሚመልስ መልካሙን ሁሉ በመመኘት ይመርቁታል፡፡ ጦር በኦይዳ ብሔረሰብ እንደሌሎቹ የዞን ነባር ብሔረሰቦች እርሻ ለማረስ ሣር ለማጨድ ፣ የቤት መሥሪያ ግርግዳ እንጨት ለመቁረጥ …. ወዘተ የሚንቀሳቀሱበት ወቅት ጦር ከእጃቸው አይለይም ምክንያቱም ከአደን ተግባር ጎን ለጎን ስለሚካሄዱ ፣ ራሳቸውን ከጠላትና ከአውሬ ለመከላከል ምንም ጊዜ ጦር ከእጃቸው አይጠፋም፡፡ ይሁን እንጂ የባህላዊ ጫዋታ ሁለትና ከዚያ በላይ ባሉ ተቃራኒ ቡድኖች መካከል ለማሸነፍ በውድድር መልክ ያከናውናሉ፡፡ ከፍታና የምድር ዝላይ (Afan Gaangge Doolle) ይህ ባህላዊ ...ተጨማሪ አንብብ ጫዋታ በኦይዳ ብሔረሰብ ከሚዘውተሩ የጫዋታ ዓይነቶች አንዱ ስሆን የከፍታና የምድር ዝላይ በመባል በሁለት ይከፈላሉ፡፡ ይህ ባህላዊ ጫዋታ ሁለት የተለያየ ደረጃ ያላቸው የባለእንጨቶች ግራና ቀኝ በማቆም እና ቀጭን ረጅም እንጨት አግድም በቆሙ በባላዎች ላይ በማጋደም ከዚያ ውድድር የሚያካሄዱ (የሚገጥሙ) ተወዳዳሪዎች አግድም በሁለት ቋሚ እንጨቶች ላይ የተጋደመውን እንጨት ተንደርድረው እንደዚሁ ይደረጋል፡፡ ተወዳዳሪዎች ያለምንም ችግር ከዘለሉ አሸናፊውን ለመለየት አግድም የተኛውን እንጨት ከፍታም በመጨመር እንዲዘሉ የሚደረግ ስሆን ነው፡፡ ተወዳዳሪዎች አሁንም ከፍ ተደርጎ የተሰራውን የተጋደመ እንጨት ከዘለሉ አሸናፊ እስክታውቅ ያለፉት ቀጥለው የመጨረሻውን ከፍታ ከዘለሉ የዉድድሩ አሸናፊ ይሆናል፡፡ ሁለተኛው የዝላይ ዓይነት የምድር ዝላይ ስሆን በመሬት ላይ ሁለት የተራራቁ መስመሮችን በማስመር ወይም ረዘም ያሉ አጫጭር እንጨቶች አራሪቀው በማጋደም ተንደርድረው ዘለው የሚሻገሩት ባህላዊ ጫዋታ ስሆን አሸናፊው እስኪሚለይ ድረስ የፊት ሜትር ርቀት በመጨመር የመጨረሻው ርቀት መስመርን የተሻገረ የዉድድሩ አሸናፊ የሚሆንበት ባህላዊ የጫዋታ ዓይነት ነው፡፡ ገበጣ(Laame) ገበጣ በአብዛኛው የሚጫወቱት አዛውንት ወንዶች ስሆኑ በአዘቦት ቀን ባህላዊ የመሰብሰቢያ ቦታ ላይ እና በቤት አከባቢ ይዘወተራል፡፡ ነገር ግን በአብዛኛው ገበጣ መጨወቻው የሚዘጋጀው ከእንጨት ስሆን የእንጨቱ ወፍረት የጉበን ያክል ስሆን እንጨቱ ይቦረቦርና ሰባት በተቦረቦረዉ ጉድጓድ አራት አራት ጠጠሮች ተጨምሮ ለሁለት ሰዉ ሆኖ ይጫወታሉ፡፡ ጫዋታው በአብዛኛው በእረፍት ቀን እና የባህላዊ በዓላት ወቅት የሚዘወትር ነው፡፡ ትግል (Butibuto) በዕድሜ አቻ በሆኑ በሁለት ወጣቶች መካከል የሚደረግ ፉክክር ወይም ውድድር ስሆን ወጣቶች አቅማቸውንና ጉልበታቸውን ለመፈተሽ በማናቸውም ከብት ስጠብቁ ፣ አዝመራ በሚሰበስብበት ወቅት ፣ ባህላዊ በዓላትና በእረፍት ጊዜ የሚዘውትሩ ባህላዊ ጫዋታ ነው፡፡ ይህ ባህላዊ ጫዋታ በአብዘኛው በጥጋብ ወቅት የሚዘወትር ስሆን የጥጋብ ምልክት ተደረገው ይወሰዳል፡፡ ከብቶቻቸውን በሚጠብቁበት ጊዜ ሰፈር በሚዉሉበትና በሠርግና በህብረት ሥራ ወቅት ከግብዣ በኋላ …. ወዘተ ጫዋታ በሰፊው ይዘወተራል፡፡ ሩጫ (Galagaadde) ይህ ባህላዊ ጫዋታ በአብዘኛው በልጆችና በወጣቶች ዕድሜ ክልል ላይ ያሉት የሚጫወቱት ጫዋታ ስሆን በዋናኝነት ዉድድር የሚካሄደው አሸናፊነትን ለመቀናጀት እና ማህበራዊ ዕውቅናን ለማግኘት ስባል የሚደረግ ዉድድር እንደሆነ ይገለፃል፡፡ የሩጫው ዉድድር በማንኛውም ጊዜ ሊካሄዱ ይችላል፡፡ የሩጫ እሽቅድድም በአንድ በተወሰነ ቦታ ምልክት ይደረግና ተወዳዳሪዎች በሩጫ ከዚህ ደርሰው ይመለሳሉ፡፡ ቀድመው ፈጥነው የተመለሰው አሸናፊ ይሆናል፡፡ ተውዳዳሪዎች ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ልሆኑ ይችላሉ፡፡ “ኮኮምኤ” /Kokom7ee/ “ኮኮምኤ” /Kokom7ee/ ከቀርካሃ የሚሰራ ለሁለት እግሮች መረገጫ ያለበት በሁለት እጅ ተይዘው ወጣቶች በቀርካሃው ላይ በእግር ቆመው በሜዳ ላይ በሩጫ የሚወዳደሩበት የጨዋታ ዓይነት ነው፡፡ እርግጫ (Iribache) በዕድሜ አቻ የሆኑ ህፃናትና ወጣቶች እርስ በርስ ያላቸውን አቅምና ጥንካሬ ለመፈተሸ በሁለት ተውዳዳሪዎች ፊቀደኝነት ላይ ተመስርተው የሚከናወኑ ስሆን ቅልጥፍናን እና አካላዊ ብቃት የሚጠይቅ ባህላዊ ጫዋታ ዓይነት ስሆን መጎዳዳት እንኳን ብኖር መበቃቀል ወይም ቅም መያዝ ፈፅሞ እንደማይቻል ይነገራል፡፡ ከላይ ከተጠሱት ባህላዊ የዉድድር ጫዋታዎች በተጨማሪ ኦይዳ ብሔረሰብ ዉስጥ በደስታም ሆነ በሃዜን ጊዜ እንዲሁም በልዩ ልዩ በዓላትና አጋጣሚዎች የሚዘፈኑና የሚጨፈሩ ጫዋታዎች አሉ፡፡ ኮሮቦ (korobo Wodhe) ይህ ባህላዊ ጨዋታ ዓይነት በብሔረሰቡ ዘንድ በዕድሜ አቻና እኩያ በሆኑት ለሁለት ቡድን ተከፋፍለዉ ከቀርካሃ ወይም ከጌሾ እንጨት በቀላሉ መጠቀለል ከሚቻል እንጨቶች በክብ የሚዘጋጅ እና ለሙዉጋት ወይም ለመወርወር ቀጥ ካለ እንጨት ተጠርቦ በአንካሴ መልክ በማዘጋጀት የሚጫወቱት ጨዋታ ዓይነት ሆኖ ለመዝናኛና በበዓላት ጊዜ ማሳለፊያነት የሚጫወቱት የጫዋታ ኣይነት ነዉ፡፡ በጨዋታዉ ሰዓት ብዙ ያስቆጠረዉ ቡድን አሸናፊነቱን የሚያረጋግጡት ከተሸናፊዎች ቡድን ከእያንድ ዳንዱ ተጨዋች አንድ አንድ ፀጉር አሸናፊዉ ወገን ነቅለዉ ይወስዳሉ፡፡ ባህላዊ መገናኛ ዘዴ በኦይዳ ብሔረሰብ ከጥንት አባቶቻችን ጀምሮ በልምድ የሚገናኙ “ቃራስ” /Qaarasa/ እጅ በማገናኘት ትንፋሽ በማውጣት ፣ “ሱሉንቄ” /Sulunqqe/ ፉጨት ፣ ለልጃገረዶች “ኤልልሰ” /Eelilse/ ስሆን እነኝ ባህላዊ መገናኛ ዘዴዎች ለሁሉም ወንዶች ለእያንዳንዱ የግል እና ለዉስን ሴቶች የራሳቸው የሆነ ኮድ ስላላቸው እስከ አምስት ኪ/ሜ ርቀት ካለው ሰው ጋር በአየር ላይ በድምፅ ለመገናኘት የሚችል ዘዴ
ባህላዊ የቤት አሰራር
ቀን 2021-09-03
በብሔረሰቡ አንድ ግለሰብ ቤት ለመስራት ስያስብ መጀመሪያ በማሳው ላይ ቦታ መረጣ ያደርጋል፡፡ የቤቱን ዙሪያ በእንሰት ፣ በቡናና በመሳሰሉት አከባባያዊ አትክልቶችን የማልማትና የማስዋብ ሥራ መሥራት በባህሉ ከጥንትም ጀምሮ ከትውልድ ወደ ትውልድ ስተላለፍ የቆየ ተግባር ነው፡፡ ቤት ለመሥራት ቀርከሃ ፣ ማሰሪያ ወፊቾ፣ ከለጋ ቀርከሃ የሚዘጋጅ /cala/ ፣ የቀርካሃ ግርግዳ (ካዝማ) ፣ የጣሪያ ወራጅ ፣ ማገርና ሌሎች ቁሳቁሶች ጊዜ ተወስደው ይዘጋጃል፡፡ ባህላዊ የቤት አሰራር ሙሉ በሙሉ ግርግዳው እና ጣሪያው (kestst aafe) ከቀርካሃ ይሆናል፡፡ አንዳንዴ የጥድ እንጨት ካዝማውን/ግርግዳውን/ ለማጠናከር ድጋፍ ይጠቀማሉ፡፡ በደጋው አከባቢ ምሶሶ እምቢዛም የማይጠቀሙ ስሆን ቆላው አካባቢ ምሶሶ ይጠቀማሉ፡፡ በደጋው አከባቢ ያለ ምሶሶ የሚሰሩ ቤቶች ከመሥራቱ በፊት ግርግዳውና ጣሪያው ጠንካራ ቁሶቁሶችን በመጠቀም ለረጅም ጊዜ እንዲቆይ ተደርጎ ይሰራል፡፡ ከዚያ ቤቱን የሚሰራው ሰው የሚገኝበት የጎሳ መሪ (ቃይዴ አዴ) የቤት ሥራ ቀጠሮ ከተያዘለት ቀን ለቤት ሰሪው ህዝብ በተሰበሰበት በምሪቃት ሥራውን ያስጀምራል፡፡ Ћaari yo7o…. Ћaari yo7o yelo shu7o kumo ….. yelo shu7o kumo keetstsita daylidhdhe—keetstsita daylidhdhe ከብቶች ይራቡበት ፣ ልጆች ይጫወቱበት ፣ ከማሌ ማርታም በረከት ይምጣ በማለት ይመርቃል፡፡ ከዚያ ቀጥሎ ባለሙያና ህዝብ እንደ የአቅማቸውና ችሎታቸውን ያህል ባዘጋጁት ግብዓቶች ቤቱን መሥራት ይጀምራሉ፡፡ የግርግዳና ጣሪያ ሥራ ከጨረሱ በኋላ ክዳኑን በጋራ ይከድናሉ፡፡ በክዳኑ ወቅት ጠላ (Daana) ተጠምቆ ባህላዊ ጫዋታ እየተጫወቱ እየበሉና እየጠጡ ይከድናሉ፡፡ ክዳኑ በባህላዊ ጫዋታ የሚታጀብ ነው፡፡ ...ተጨማሪ አንብብ በዚህ ወቅት ከሚዘሙት ጫዋታዎች መካከል ፋርጉሌ ፋጭፔ (fargulle faccipe) (Keexxide Ade faccipe……songee Inda faccipe) ይላሉ፡ ሌላው የተለያዩ ባህላዊ ጨዋታዎችን በክራርና (Ditsts) እምብልታ (File) የታጀበ በተሰራው ቤት ዉስጥ ይጫወታሉ፡፡ በመጨረሻም ታዳሚውን አዛውንቶች መርቀው እንዲበተን ያደርጋሉ፡፡
የለቅሶ ሥነ-ሥርዓት በኦይዳ ብሔረሰብ
ቀን 2021-09-03
የሰው ልጅ አፀደ-ሥጋ ለብሰው በዚህ ሥጋዊ ዓለም ስንቀሳቀስ ዘመድ አዝማድ ወይም ወዳጅ ደስ ይለዋል፡፡ በሞት ስለይም እንባ እየተራጩ ደረት እየደቃ እየወደቀና እየተነሳ ፊቱን እየነጨ ለሟቹ ያለውን መረሪ ሀዜን መግለጫ ነው ፡፡ በኦይዳ ብሔረሰብ የለቅሶና የቀብር አፈፃፀም ሥርዓት በማህበረሰቡ ዘንድ ባላቸው ተቀባይነትና ማህበራዊ ሁኔታ ላይ ተመሰርተው የሚከናወን ባህላዊ ሥርዓት እንደነበረ ይገለፀል፡፡ በኦይዳ ብሔረሰብ የለቅሶና የሀዜን ሥርዓት በዕድሜና በማህበራዊ ደረጀ ተለይተው ይከናወናል፡፡ ወጣቶችና ጎልማሣ ስሞቱ ለቅሰው መራራ እንደሆነ ይነገራል፡፡ የአዛውንት ለቅሰው ከወጣቶችና ጎልማሣ የሚለየው እንደ ሌላው መራራ ሳይሆን በሕይወት ዘመኑ የፈፀማቸውን ታሪክ በባህላዊ ለቅሶ በዘፈን በማውደስ በሙገሳ ከፍ እያደረጉ ይለቀሳል፡፡ ንጉስ /Kaati/ ስሞት የሥልጣን ከፍታዎችን ለማሳየት ሲፈልጉ ተራራው ተናደ /dere woddida/wala woddida/ ይባላል እንጂ ሞተዋል ተብሎ አይነገርም፡፡ ከሞተም በኋላ አስከረኑን በአስከሬን ማቆያ /gaaffa/ ላይ እንዲቆይ ይደረጋል፡፡ ሟቹን ተክተው የሚነግሰው ንጉስ /Kaati/ ከጎሳው ክፍሉ ታላቅ የሆነው ሰው በሕበረተሰቡ ዘንድ ተቀባይነት ያገኘና ጥሩ ሥነ-መግባር ያለው ይታጫል፡፡ በአሿሿም ሥነ-ሥርዓቱ መሠረት ይሾማል፡፡ የመተካቱ ሥርዓቱ ከተከናወነ በኋላ በይፋ ለህዝቡ ይነገርና ለቅሶው ይጀመራል፡፡ የሚለቀሰው በንጉሱ ግቢ ሆኖ ከሦስት እስከ ሰባት ቀን ልቆይ ይችላል፡፡ የቀብር ሥነ-ሥርዓቱ በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች በንጉስ /Kaati/ መቃብር ይቀበራል፡፡ ሌላ በኦይዳ ማህበረሰብ በየእርኬኑ የሚገኙ የህዝብ መሪዎች ታዋቂ የሀገር ሽማግሌዎችና የጦር ጀግኖች ስሞቱ ኃላፊነታቸውን ፣ ተግባራቸውና ጀግንነታቸውን በማወደስና በ ...ተጨማሪ አንብብመዘከር የሚለቀስ ሆኖ የቀብር ሥነ-ሥርዓቱ በብሔረሰቡ ዘንድ ዕውቅና በተሰጠ ልዩ ቦታዎች ላይ ይሆናል፡፡ የለቅሶ ዓይነት በኦይዳ ብሔረሰብ በብሔረሰቡ ባህል የለቅሶ ዓይነቶች የተለያዩ ስሆን እነሱም፡-ዣሬ የፎ እናፌሾ የፎ በመባል ይታወቃል፡፡ 1. “ ዣሬ የፎ” የሚባለው የመጀመሪያ ቀን ለቅሶ ሆኖ በዕድሜና በሥልጣን ዕርኬን ልለያይ ይችላል፡፡ ለህፃናት ፣ ለታዳጊ ከሞተ የሟች ነፍስ ከሥጋው እንደተለየች የሚለቀስ ነው ፣ በኦይዳ ብሔረተሰብ ከፍተኛ ሀዜንና ለቅሶ መረር የሚሆነው ያላገባና ትውልድ ያላፈራ ወጣት እና ጎልማሳ ስሞት ለየት ያለ ለቅሶ ይለቀሳል፡፡ አልቃሾች ሀዜናቸውን ለመግለጽ ጥላሸት ፣ አፈርና አመድ አካላቸውን በመቀባትና ግንባራቸውን በማቧጨር በማድማት ከወገቡ በላይ እርቃን በመሆን የሟችን ስም በመጥራትና በአጭር መቀጨቱን በመረሪ ሀዜን እስከ ሦስት ቀን ከተለቀሰ በኋላ የቀብር ሥርዓት የሚፈፀም ሆኖ ለዕድሜ ጠገብ ሽማግሌ እና ባህላዊ መሪዎች ከሆነ ካረፉበት ጊዜ እስከ ሦስት ወይም አራት ቀን ቆይታ የሚጀምር ይሆናል፡፡ አለቃቀሱ የሟችን ዝና ጀግንነት እያነሱ በእንጉርጉሮ የሚያለቅሱ ስሆን ሟች በሕይወት በነበረበት ዘመን የሚጠቀምባቸውና ያፈራቸው ዕቃዎቹ ሁሉ ወጪ ይወጡና ለቀስተኛው በግልጽ በሚታይ ሥፍራ ይቀመጣል፡፡ በመቀጠልም የቤቱ ጣሪያ ተነድሎ በቤቱ ጣሪያ ላይ ቡልኮ ይነጠፋል ጋሻና ጦር ይቀመጣል፡፡ 2. “ፌሾ የፎ” በመባል የሚታወቅ ስሆን አቅምን ባገናዘቤ መልኩ በቂ ዝግጅት ከተደረገ በኋላ ከአንድ ወር እስከ ሦስት ወር ዉስጥ በአካባቢ በሚገኘው በባህላዊ ለቅሶ አደባባይ ላይ የሚለቀስና አልቃሾች የሚጋበዙበት የመጨረሻው የለቅሶ ሥርዓት ነው፡፡ ለቅሶው በምግብና መጠጥ ተዘጋጅተ በድግስ መልክ ይካሄዳል፡፡ በአጠቃላይ በኦይዳ ብሔረሰብ ለቀሶና የቀብር ሥርዓት ባህላዊ ወግን መሠረት ያደረገ የማንነታቸው መገለጫ ነው፡፡ 3 .“ሞጎ“ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ፡-የቀብር ሥነ-ሥርዓት በኦይዳ ብሔርሰብ ባህል በሀብት ፣ በዕድሜ እና በሥልጣን እርከን ይለያያል ፡፡ 4./Dame Wodhe/ “ዳሜ ወꬌ” ዳሜ ወꬌ የሚባለው የመጀመሪያ ጥርስ ካበቀሉ ህፃናት ዕድሜ በላይ ሆኖ ለሞቱ ሰዎች ለቅሶ ከቀብር በኃላ የሚፈጸም ነው፡፡ በባህሉ ለቅሶ ሞት በተጋጋሚ ካጋጠመው እና የሀብት አቅም የማይችል ቤተሰብ የለቅሶን ሥርዓት በማሳጠር የሚያጠናቄቁት ሥርዓት ነው፡፡ በታሳ “Betatstsa/” ይህ ሥርዓት ሰው ከሞተ አልቅሰው ከቀብሩ በኋላ የሟች ቤተሰብ ከአንድ ወር እስከ ሁለት ወር ባለው ጊዜ ራሳቸዉን አጎሳቁሎ ካዘኑ የለቅሶ ማብቂያ ተደርጎ የሚወሰድ የሀዜን ልብስ የሚጥሉበት ገላቸውን የሚታጠቡበት ፣ አዲስ ልብስ የሚለብስበት ፣ ቅቤ የሚቀቡበት ወግ ነው፡፡
ያግኙን
☏046-777-1536
ተዛማጅ ሊንኮች
Copyright © 2021-2025 Gofa Zone Adminstration.All Rights Reserved
Gofa,Ethiopia
By logging in you agree to our Terms and Conditions and Privacy Policy
By logging in you agree to our Terms and Conditions and Privacy Policy