የጎፋ ዞን አስተዳዳር ጽ/ቤት
አቶ ታመነ ቢሻው ታፈሰ አስተዳዳር ጽ/ቤት ኃላፊ
የሴክተሩ አጠቃላይ ገጽታ፤ጽ/ቤቱ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች፤. ራዕይ፤ ተልዕኮ እና እሴቶች
ቀን 2021-07-12
የሴክተሩ አጠቃላይ ገጽታ የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/ም/ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት በ1987 ዓ/ም በጸደቀው የክልሉ ህገ-መንግስት ከህግ አውጭው አካል ጋር በአንድነት ተቋቁሞ የነበረ በመሆኑ በወቅቱ ይታይ የነበረውን የአደረጃጀት ችግር በክልሉ ህ/ተሰብ የመልካም አስተዳደር፤የልማት ተጠቃሚነት ላይ ያሳደረው ተጽኖ በመለየቱ ይኸው ህገ-መንግስት በ1994 ዓ/ም ተሻሽሎ ሲወጣ የአስተደዳደር ሴክተሩ ከህግ አውጭው አካል ተለይቶ የህግ አስፈጻሚ በመሆን ራሱን ችሎ ሲቋቋም በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 80 ላይ በተደነገገው መሰረት የጎፋ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤትም ተቋቁሟል፡፡ ሴክተሩ ከሌሎች በዞናችን ከሚገኙ አስፈጻሚ አካላት በተለየ ሁኔታ የዞኑ አስተዳደር ም/ቤት ጽ/ቤት በመሆንም ጭምር እንዲያገለግል በተሻሻለው የክልሉ ህገ-መንግስት አንቀጽ 80/2ለ/ተደንግጎ የሚገኝ ሲሆን ይህም ከሌሎች አስፈጻሚ አካላት ለመለያ አይነተኛ ባህሪ ነው፡፡ ጽ/ቤቱ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች • ደንብና መመሪያዎችን ማስፈጸም • የአስፈጻሚውን የአጭርና የረጅም ጊዜ ዕቅድ የመገምገምና ለሚመለከተው አካል የማቅረብ ስራ፣ • የአስፈፃሚውን የዕቅድ አፈጻጸም የመከታተል፣ የመቆጣጠርና የመገምገም እንዲሁም ለሚመለከተው አካል የማቅረብ ሥራ፣ • ውሳኔ የሚያስፈልጋቸው የኢኮኖሚያዊ፣ ማኀበራዊና የመሰረተ-ልማት ጉዳዮችን የመመርመር፣ የማጥናት፣ መፍትሔ እንዲያገኙ የማድረግና አፈፃፀማቸውን የመከታተል ስራ፣ • ለዕቅድ አፈጻጸም እንቅፋት ሊሆኑ የሚችሉ ክፍተቶችን በጥናት የመለየት እና የመከታተል ስራ፣ • በሚመለከታቸው በዞኑ ተቋማት የተከናወኑ ወሳኝ ተግባራትን በመለየት የፋይዳ ዳሰሳ ጥናት እንዲከናወን የማስተባበር ስራ፣ • በዞኑ የህግ የበላይነትን ማስከበር • የሰብአዊ መብቶች አያያዝና የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ እንዲሻሻል የሚያስችል አሰራር እንዲኖር የማድረግ ስራ፣ • በህግ ጉዳዮች ላይ ለአስተዳድር ም/ቤቱም ሆነ ለዋና አስተዳደር ተገቢውን ሙያዊ አስተያየትና አማራጮችን የማቅረብ ስራ፣ • የፍትህ ስርአት ማሻሻያ ፕሮግራም በሚመለከታቸው ተቋማት ተቀናጅቶ ሊተገበር በሚችልበት ሁኔታ መታቀዱንና መከናወኑን የመከታተልና ግብረ መልስ የመስጠት አገልግሎት፣ • የአስተዳድር ምክር ቤቱን የስብሰባ ሂደቶች በመቅረፀ-ምስል፣ መቅረፀ-ድምፅና በህትመት ሠነዶችን በአግባቡ በመያዝና በመጠበቅ ለሚፈቀድላቸዉ አካላት የማቅረብ ስራ፣ • የአስተዳድር ምክር ቤቱን ቃለ-ጉባዔ መያዝ እና የሚተላለፉ ዉሳኔዎች ምስጢራዊነታቸዉ ተጠብቆ ለሚመለከተዉ አካል ተደራሽ እንዲሆኑ የማድረግ ስራ፣ • ለካቢኔ የሚቀርቡ ጉዳዮች በአስተዳድር ም/ቤት የአሰራር ደንብ መሰረት ተገቢውን የጥራት ደረጃ ጠብቀው መቅረባቸውን የማረጋገጥ አገልግሎት፡፡ • የዞኑን አስተዳድር ምክር ቤት የሚያፀድቃቸዉን ደንቦችና መመሪያዎች አሳትሞ የማሰራጨት ስራ፣ • ከመንግስት መ/ቤቶች ለአስተዳደር ም/ቤት ውሳኔና ውይይት የሚቀርቡ ሰነዶችና የውሳኔ ሀሳቦችን በተመለከተ የማማከር፣ ድጋፍ የመስጠትና የማስተባበር ስራ፣ • በአስተዳድር ም/ቤቱ ለሚቋቋሙ ልዩ ልዩ ኮሚቴዎች ድጋፍ የመስጠትና የማስተባበር ስራ መስራት፡፡ • በወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የካቢኔ የአሰራር ስርዓት ደንቡን የተከተለ ስለመሆኑ ክትትልና ድጋፍ የማድረግ ስራ፣ • በዞኑ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝዉዉርን በመከላከል ዙሪያ በተለያዩ ተቋማት የሚከናወኑ ተግባራትን የመከታተልና የመደገፍ ስራ መስራት፣ • ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጪ ሀገር ወደ በዞኑ ለሚመጡ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ አምባሳደሮችና የአለምአቀፍ ድርጅቶች ተጠሪዎች የፕሮቶኮል ሽፋን የመስጠት አገልግሎት፣ • በዞኑ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝዉዉርን በመከላከል ዙሪያ በተለያዩ ተቋማት የሚከናወኑ ተግባራትን የመከታተልና የመደገፍ ስራ፣ • የሪፎርም ኘሮግራሞች ጉዳዮችን አተገባበር የመከታተል፣ የመደገፍና ግብረ-መልስ የመስጠት ስራ፣ • የመልካም አስተዳደር ፖኬጆች አተገባበርና ዉጤታማነትን በተመለከተ የፋይዳ ዳሰሳ ጥናት የማከናወን ስራ፣ • ሁሉም የለውጥ (Reform) ኘሮግራሞች ተቀናጅተዉ እንዲመሩ የንቅናቄ መድረክ የመፍጠር ስራ፣ • የፀጥታ ምክር ቤቶችን የመምራትና የመከታተል ስራ፣ • የፀጥታ ሴክተሩን አፈፃፀም በበላይነት የመምራት፣ የመከታተል፣ የመደገፍና የመቆጣጠር ስራ፣ • አጠቃላይ የፀጥታ ሪፖርት በመቀበልና ትንታኔና ዕንድምታዎችን ለይቶ የመደገፍ ስራ፣ • ቅሬታዎችና አቤቱታዎችን መቀበል፣ማጣራትና ዉሳኔ የመስጠት ስራ፣ • የቅሬታና አቤቱታ መንስኤዎችና በተገልጋይ እርካታ ዙሪያ የጥናት ስራ፣ • በየደረጃዉ የሚገኙ የቅሬታና አቤቱታ መዋቅሮችን የመከታተልና የመደገፍ ስራ፣ • በየደረጃዉ የሚገኙ የቅሬታና አቤቱታ መዋቅሮች ላይ የሚሰሩ ፈፃሚዎችን አቅም የማሳደግ ስራ፡፡ • የአፈጻጸም ሪፖርቶችን ማሰባሰብ፤ማደራጀትና ማቅረብ • የማህበረሰብ የመረጃ ማእከል ማደራጀትና የኢንፎርሜሽን አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ • የግንባታ ዲዛይን በማዘጋጀት የውለታ አስተዳደር ጥራትና ቁጥጥር ማድረግ • የስነ-ምግባር ግንዛቤ ማስጨበጫ በመስጠት የህዝብና የመንግስት ሃብት እንዳይባክን ለመከላከል፡፡ ራዕይ፤ ተልዕኮ እና እሴቶች ራዕይ በዞኑ ሰላምና ፀጥታ ተረጋግጦ እና መልካም አስተዳደር ሰፍኖ ዘላቂ ልማትን በማምጣት ህብረተሰቡ ተጠቃሚ ሆኖ ማየት፡፡ ተልዕኮ በዞኑ ያሉትን ሰብአዊና ተፈጥሮአዊ ሐብቶች አቀናጅቶ፣ቀጣይነት ባለው መልኩ ጥቅም ላይ እንዲዉሉ በመምራትና በማረጋገጥ፣ፈጣን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት እድገትን አጠናክሮ በማስቀጠል የዞኑ ህዝብ የልማትና መልካም አስተዳደር ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ፡፡ እሴቶች • የህግ የበላይነት መርሀችን ነው! • ለተገልጋይ ፍላጎት ትልቅ ዋጋ እንሰጣለን፣ • መቻቻል ባህላችን ነው፣ • አሳታፊነት መለያችን ነው፡፡ • ልዩነታችን ውበታችን፣ ውበታችን አንድነታችን ነው፡፡ • ህብረተሰቡ ቅን አገልጋይ መሆን መለያችን ነው ! • ቅሬታ አቅራቢዎች መካሪዎቻችን ናቸው ! • ፍትሀዊነት እናሰፍናለን ! • ሙስናን ከሚያጋልጡና ከሚቃወሙ ጋር በአንድነት ቆመናል ! • ለተለያዩ ባህሎች አክብሮትን እንሰጣለን ! • መማማርና መለወጥ መታወቂያችን ነው ! • ሥርዓተ-ፆታ የስራችን አካል ነው ! • የመረጃ ልውውጥን በማዳበር ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂን እናስፋፋለን
የጎፋ ዞን ሕዝብ ምክር ቤት
አቶ ጠንክር ጠንካ የጎፋ ዞን ህዝብ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ
የጎፋ ዞን ሕዝብ ምክር ቤት ራዕይ ተልዕኮና እሴቶች
ቀን 2021-05-01
ራዕይ በ2022 ዓ.ም ምክር ቤቱ የህዝብ ሥልጣን ባለበትነት የተረጋገጠበት የመልካም አስተዳደርና የዴሞክራስ ተምሳሌት ሆኖ ማየት፡፡ ተልዕኮ የምክር ቤቱን አሰራር በማሻሻል በህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ ለዞኑ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፐለቲካዊ ዕድገት መፋጠን ፈይዳ ያላቸውን ህጎችን በማውጣት የመንግሥት አካለትን በማደራጀት አፈፃፀማቸውን በመከታተልና በመቆጣጠር የህዝብ የስልጣን ባለቤትነት እንድረጋገጥ የግልጸኝነትና ተጠያቂነት አሰራር እንዲሰፍን እና ዴሞክራሲያዊ ሥራዓት እንድጎለበት ማድረግ ነው፡፡ እሴቶች • ፍትሃዊነት መርሀችን ነው፡፡ • ህዝብን በቅንነት ማገልገል መታወቂያችን ነው • የአሠራር ግልጽኝነትና ተጠያቂነት መለያችን ነው • ለህግ የበላይነት መቆም ሥራችን ነው • ልዩነታችን ውቤታችን ውበታችን ውቤታችን አንድነታችን ነው • አሳታፊነትና ቅንጅታዊ አሰራር መመሪያችን ነው • ለህዝቡ ጥያቄ ፈጣን ምላሽ መስጠት ባህላችን ነው
የጎፋ ዞን ፍትሕ መምሪያ
አቶ ደመላሽ ብላቴ ፔሻ ፍትሕ መምሪያ ኃላፊ
የተቋሙ ራዕይ፤ተልዕኮና ዕሴቶች/VISION
ቀን 2021-04-13
የተቋሙ ራዕይ //VISION/ በ2022 በዞኑ ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ተጠብቀው የህግ የበላይነት ተረጋግጦ በክልላችን ብሎም በዞናችን በአርአያነት ሊጠቀስ የሚችል ፍትህ ሰፍኖ ማየት፡፡ የተቋሙ ተልዕኮ (MISSION) በዞኑ ፍትህ እንዲሰፍን፣ የመንግስትና የህዝብ ጥቅሞች እንዲጠበቁ፣ በህገ መንግስቱ ላይ የተደነገጉ ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ ለማስቻል የህብረተሰቡን ንቃተ-ህግ በማሳደግ፣ ወንጀል ፈጻሚዎች ለህግ እንዲቀርቡና ለፈጸሙት ጥፋት በሕግ እንዲጠየቁ በማድረግ እንዲሁም የዜጎችን የመደራጀት መብት በማረጋገጥ የመሪነት ሚና በመጫወት መልካም አስተዳደርን ማስፈን ነው፡፡ የተቋሙ ዕሴቶች • የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ፣ • ገለልተኝነት፣ • ታማኝነት፣ ግልፀኝነትና፣ ተጠያቂነት፣ • ቀልጣፋነት፣ ፍትሐዊነት፣ ተደራሽነት እና ወጪ ቆጣቢነት፣ • እኩልነትና የአልጋይነት ስሜት፣ • ውጤትና ተገልጋይነት ተኮር መሆን፣ • የተቀናጀ የፍትህ አገልግሎት፣ • ለለውጥ ዝግጁነት የተቋሙ ዓላማ መለምሪያው በህግ የተሰጠውን ህገ-መንግሥት ፤ህገ መንግሥታዊሥርዓቱንና የህግ በላይነትን የማክበርና የማስከበር ፤የዘጎች ሠብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸውን የምክበርና የማስከበር ፤የህዝብና የመንግሥት ጥቅም በተሟላ ሁኔተታ የማስጠበቅና ለዘጎች ውጤታማ እና ቀልጣፋ አገልግሎት የመሥጠት ኃላፊነቱን በተደረጀና በተቀናጀ መልኩ መወጣት ነው ፡፡
ያግኙን
☏046-777-1536
ተዛማጅ ሊንኮች
Copyright © 2021-2025 Gofa Zone Adminstration.All Rights Reserved
Gofa,Ethiopia