ከ 2011ዓ.ም ጀምሮ ጎፋ ዞንን ያስተዳደሩ


አቶ ፀጋዬ ዘካሪያስ ጉርሙ


የጎፋ ዞን የመዋቀር ጥያቄ ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ ቢሆንም ምላሽ ያገኘው በመላው ኢትዮጵያዊያን ትግል በመጣው የመንግስት ለውጥ በ 2011 ዓ/ም ነው፡፡ የጎፋ ዞን በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ውስጥ ካሉ ዞኖች እንዱ ሲሆን በ 7 ወረዳዎች እና በ 4 ከተማ አስተዳደሮች የተዋቀረ ነው፡፡ ዞኑ የጎፋ እና የኦይዳ እንዲሁም የለሎች በርካታ ብሔር ብሔረሰቦች መኖሪያ ነው፡፡ የዞናችን አጠቃላይ የቆዳ ስፋት 4,551 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ሲሆን የዞኑ ዋና ከተማ ሣውላ ከአዲስ አበባ በ526 ኪ.ሜ ከክልሉ ርዕሰ ከተማ ሀዋሣ በ300 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ እንደ ብሔረሰቡ ተወላጅ ይህንን ታላቅና የተከበረ ህዝብ በዞን ዋና አስተዳዳሪነት በፍፁም መሰጠት፣ በንፅህናና በቅንነት በማገልገሌ እጅግ በጣም ከፍ ያለ ደስታና ክብር ይሰማኛል፡፡ ዞናችን አዲስ እንደ መሆኑ መጠን ለዘመናት የቆዩ የመልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ያሉበት ሲሆን ይህንንትልቅ ሀላፊነትከተቀበልን በኃላ የህዝባችን ወቅታዊ እና አንገብጋቢ ጥያቄዎችን ከህዝቡ ከራሱ አንደበት ለመስማት በሁሉም መዋቅሮች በአካል በመውረድ ህዝባችንን የመጎብኘትና የማወያየት ሥራ ሠርተናል፡፡ ከሁሉም የመስክ ጉብኝቶች ልዩ፣ ልቤን የነካኝ እና ባየሁት ነገር እንባየን መቆጣጠር ያቃተኝ የመሎ ጋዳ ወረዳ ጉብኝት ነበር፡፡ ወረዳው አዲስ እንደመሆኑና መኪና የሚያስገባ መንገድ በላመኖሩ ኢርግኖ ወንዝን በእግራችን፣ አብዛኛውን መንገድ በእግር እና በሞተር ሳይክል ተጉዘን የወረዳው መቀመጫ ወንባ ከተማ ስንደርስ የህዝቡ አቀባበል እጂግ አስገራሚ ልብ የሚነካ ነበር፡፡ የዛን ቅፅበት ‘ይህን ምስክን ህዝብ በንፅህናና በፍፁም መሰጠት ማገልገል ምንኛ መታደል ነው?’ ብዬ ራሴን ጠየኩ:: በሁሉም መዋቅሮች የነበረው ደማቅ አቀባበል ለተልኳቸን ተጨማሪ ስንቅና ሞራል ሰጥቶናል፡፡ በዚህም በሁሉም መዋቅሮች የህዝባችንን የልብ ትርታ በማዳመጥ የቅድሚያ ቅድሚያ የሚሰጡ ተግባራት በመለየት ለየመዋቅሩ የፊት አመራሮች አመራር በመስጠትና የቅርብ ክትትል በማድረግ በአጭር ጊዜ ውስጥ ዉጤት ማምጣት ተችሏል፡፡ ለአብነት የመሎ ጋዳ ወረዳ ተደራሽ የጠጠር መንገድ ከክልሉ መንገዶች ባለስልጣን፣ ከኮይሻ የኤለክትሪክ ሀይል ማመንጫ ፕሮጀክት በአካል ግንኙነት በማድረግ እና ከዞን በልዩ ሁኔታ በጀት በመመደብ በአጭር ጊዜ መንገዱ ተጠናቆ አገልግሎት እንዲሰጥ ማድረግ ተችሏል፡፡ በተጨማሪ በገዜ ጎፋ ወረዳ ከህርግኖ ወንዝ አንስቶ በጃውላ-ኬንቾ-ባርዛ ቀበለያትን እልፎ እስከ ሣውላ በገንጠያ ያለውን መንገድ ጥገና ማድረግ ተችሏል፡፡ለላው በደምባ ጎፋ ወረዳ የፃይና-ፓልካ-ላይማ ፃላ 21 ኪ/ሜ መንገድ ጥገና እና 5 ኪ/ሜ ውስጥ ለውስጥ መንገድ ከፈታ፣ በዛላ ወረዳ የ3ቀበሌያት ዛላይነዴ-ባቦ-ጋርማ የምያገናኝ (በማላንጋ ወንዝ ድልድይ ሥራ እና ተደራሽ የጠጠር መንገድ)፣ አምቤ ጋይሌ ተደራሽ የጠጠር መንገድ እና እንዳ ጋራ ቀበሌ በማላንጋ ወንዝ የቱቦ ቀበራና ተደራሽ የጠጠር መንገድ ማስጀመር ተችሏል አብዛኛውን አስጨርሰን ማስመረቅ ችለናል፡፡ የብልፅግና ጉዟችን አንዱና ዋነኛው አደጋ ሌብነት እንደመሆኑ መጠን በተለይ በኦይዳ፣ ዛላ እና ሣውላ ከተማ አስተዳደር ለተነሱ የህግ የበላይነት፣ የህዝብ ሀብት አጠቃቀም የግልፀኝነትና ብክነት ችግር ጥቆማዎች መነሻ በማድረግ ባጠረ ጊዜ ህጋዊ የማጣራት ሥራ በመሥራት አብዛኛዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ ተወስዷል፡፡ ቀሪዎች ላይ ተገቢ እና ህጋዊ ማጣራት እየተደረገ ይገኛል፡፡ ህዝባችንን በተለያዩ አጀንዳዎች ዙሪያ በማስተባበር ከፍተኛ የህብረተሰብ ተሳትፎ ተግባራት አከናውነናል፡፡ የጎፋና ኦይዳ ህዝቦች በሀገር አንንድነት እና ሉአላዊነት የማይደራደሩ በተግባር እስከ ግንባር በመዝመት ከወንድም ኢትዮጵያን ጋር ወራርውንፋሽስት የጣልያን ጦር በአድዋ በማሸነፍ በመላው የጥቁር ህዝቦች ታሪክ ደማቅ ታሪክ ፅፈዋል፤ በተጨማሪ ወራርውን የሶማሊያ ጦር በካራማራ ድባቅ ስመታ የህዝባችን ተጋድሎና ጀግንነት ታላቅ ነበር፡፡ ለዚህ ታርካዊ ጀብድ በሀገራችን መዲና በአዲስ አበባ ‘’የጎፋ ሰፈር’’ ህያው ምስክር ነው፡፡ ይህ አርበኝነታቸው ለዘመናት ሳይበርድና ሳይቀዘቅዝ ስለመዝለቁ እንቁ ልጃችን ምክትልአስር አለቃ ገበያነሽ ደባልቄ የሠራችው ገድል ምስክር ነው፡፡ በአሁኑ ትውልድ በሰሜን ዕዝ የመከላለያ ሠራዊታችን ላይ በጁንታው የህወሃት ቡድን በተፈጠረ ክህደት እና በተካሄደ እጅግ አሰቃቂ ጭፍጨፋ ምክንያት እጅግ በጣም በአጭር ጊዜ ውስጥ ህዝባችንን ከጫፍ ጫፍ በማስተባበር የመጀመሪያው ዙር ድጋፍ እንደ አዲስ ዞን ሳይሆን በክልሉ ካሉ ነባር እና ከሁሉም ዞኖች ከፍተኛውን ድጋፍ በአይነትና በቁጥር 203 ሰንጋ፣ 16 ፍየል፣ 4 በግ በተጨማሪ 4 ሚሊዮን ብር ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የገንዘብድጋፍ የተሰበሰቤ ሲሆን በአጠቃላይ ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረግ ተችላል፡፡ለላው በመሎ ላሃ እና በቶ ከተማ አስተዳደር በከፍተኛ የህብረተሰብ ተሳትፎ የከተማ ውስጥ ለውስጥ የመብራት ዝርጋታ እና ለሎች የልማት ሥራዎች እንደ ምርጥ ተሞክሮ በመውሰድና እውቅና በመስጠት በአመራር ተልዕኮ ወደ ሁሉም የዞኑ ከተሞች ማስፋት ተችሏል፤ በተለይ በኦይዳ ወረዳ ሸፍቴ ከተማ፣ ዛላ ወረዳ በአጭር ጊዜ አመሪቂ ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል፡፡ በዞናችን ስር አዳዲስ 3 መዋቅሮች ምስረታ ማካሄድ ችለናል፤ በዚህም መሠረት የመሎ ጋዳ ወረዳ ከዞኑ መዋቅር መፈቀድ ጋር አብሮ የተፈቀደ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች ይፋዊ የምስረታ መርሃ-ግብር ሳይደረግ ቆይቷል፡፡ ይሁን እንጂ የካቲት 07/ 2013 ዓ/ም የዕለቱ ክብር እንግዳ የተከበሩ አቶ ተስፋዬ በልጂጌ የዴሞክረሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚንስትር፣ ለሎች ከፍተኛ የክልልና ዞን ከፍተኛ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት እጂግ ደማቅ በሆነ ስነ-ስርአት ተመስርቷል፡፡ ተጨማሪ በክልሉ መንግስት ውሳኔ መሠረት የመሎ ኮዛ ወረዳ መቀመጫ ላሃ ከተማ እና የዑባ ደብረፃይ ወረዳ መቀመጫ የበቶ ከተማ ወደ ከተማ አስተዳደርነት እንዲያድጉ ተደርጓል፡፡ ለአንድ አከባቢ ሁለንተናዊ እድገት የአካባቢ ልህቃን በወሳኝ ጉዳዮች ላይ አንድነት እና ወንድማማችነት ወሳኝ ጉዳዮች ናቸው፤ ከዚህ አንፃርዞናቸችን ጠንካራ፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ እና ተደማጭ ዞን ለማድረግ እንዲያስችለን የዞኑ የመጀመሪያ የዞኑ ምሁራን የአንድነት እና የመግባባት መድረክ በሀዋሣ ከተማ በተሳካ ሁኔታ አካህደናል፡፡ በሂደቱ አሸናፊም ሆነ ተሸነፊ የለም፤ አሸናፊ ሰፊው ህዝባችን ነው፡፡ በማህበራዊ ዘርፍ የጎፋ ባራንቼ እግር ኳስ ቡድን በወንዶችም በሴቶችም የዞኑ ምልክት Brand እንደመሆናቸው መጠን ከፍተኛ ውጤት እንዲያስመዘግቡ በጀት ከመመደብ እና ተጨማሪ ሀብት ከማሰባሰብ ባለፈ የልምምድ ወቅት እና ከመዳ ውጭ በሚደረጉ ጫወታ በአካል በመገኘት የማበረታታት ሥራ በመሥራት አንፃራዊ ውጤት ማምጣት ተችሏል፡፡ ለላው አቅመ ደካማ እና የጎዳና ተዳዳሪ ወገኖቻችንን ከሣውላ ከተማ አስተዳደር ጋር በመቀናጀት በጌና በዓል የምሳ ግዣ ማድረግ ተችሏል፡፡ የፕሮጀክት ሥራዎችን በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብና የጥራት ደረጃ ማጠናቀቅ የግድ ይላል፤ ከዚህ አንፃር በኦይዳ ወረዳ ጎይብ ቀበሌ የንፁህ ዉኃ መጠጥ ፕሮክት በ Hope International Ethiopia የገንዘብ ድዳፍና 10% የህብረተሰብ ተሳትፎ በ3 ወር ጊዜ ውስጥ አጠናቀን በማስመረቅ አገልግሎት እንድሰጥ ተደርጓል፡፡ በዞን የምስተዋለውን የቢሮ ጥበት ለመቅረፍ በዞኑ አስተዳደር ወጪ በ4 ሳይቶች እየተገነቡ የነበሩ G+0 ህንፃዎች አስፈላጊ የዲዛይን ለውጥ በማድረግ፣ ባለሙያ በመመደብ እና በአካል በየጊዜ ክትትል በማድረግ በአጭር ጊዜ ጊዜያዊ የዞኑ አስተደዳደር ጽ/ቤት፣ ሱካ፣ ሰዝጋ እና ቁፄ G+0 በማስመረቅ ወደ አገልግሎት እንዲገቡ ተደርጓል፡፡ ዞናችን እጅግ በጣም ከፍተኛ የተፈጥሮ ሀብት ክምችት እና አቅም(Potential) ያለው ዞን ነው፡፡ ዞናችን በ3ቱ የአየር ፀባይ ማለትም በደጋ፣ በወይና ደጋ እና በቆላ የሚከፈል በመሆኑ ለተለያዩ ምርቶች ምቹ ነው፤ ለአብነት ቡና፣ ሰሊጥ፣ ኮሮሪማ፣ ዝንጅብል፣ ለውዝ፣ ጤፍ፣ በቆሎ፣ ሙዝ፣ አሪቲ እና ወዘተ በስፋት ይመረታል፡፡ በተጨማሪ የቁም ከብት ስርጭት በክልሉ ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል፡፡ በቱሪዝም ዘፍር ሆቴል፣ ሪዞርት እና ሎጅበተጨማሪነት የታሸገ ውሃ የኢንቨስትመነት ዘርፍ በለሎችም ዘርፎች ተሰማርተው ራሳቸውንና ሀገራቸውን እንድጠቅሙ በዝህ አጋጣሚ ጥሪዬን ማስተላለፍ እወዳለሁ፡፡ የኮይሻ የኤለክትሪክ ሀይል ማመንጫ ፕሮጀክት እና የኮይሻ ገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ለዞናችን ህዝብ ትልቅ የመልማት እድል ይዞ የመጣ ነው፡፡ በተለይ ሣውላ ከተማ ለአካባቢው በአቀማማጥ ማዕከል ያደርጋታል፤ ሣውላ ለ5 መስመሮች መተላለፍ እና መዳረሻ ያደርጋታል፡፡ 1ኛ- ከሣዉላ- ቡልቂ- መሎ ላሃ- ኮይሻ- ጂማ- አዲስ አበባ፣ 2ኛ ሣዉላ- ሶዶ- አዲስ አበባ፣ 3ኛ ሣዉላ- ዛላ- ካምባ- ገረሴ- አርባ ምንጭ- አዲስ አበባ፣ 4ኛ ሣዉላ- ኦይዳ- ደማ- ደቡብ ኦሞ ጂንካ እና 5ኛ ሣዉላ- ዛላ- ቤቶ- ደቡብ ኦሞ ጂንካ፡፡ አብዛኛዎቹ የቱሪስት ምንቀሳቀሻ መስመሮች ናቸው፡፡ ይህን ትልቅ የመልማት እድል አስቀድሞ በመረዳት አስፈላጊና ተገቢ ርብርብ አንዲደረግ ህዝባችንን የማንቃት ሥራ የጀመርን ቢሆንም በስፋት ህዝቡን፣ የአከባቢውን ባለሃብት ብሎም ኢንቨስተሮችን በውል ማስረዳት ያስፈልጋል፡፡ ዞናችን የከፍተኛ ባለስልጣነት ትኩረት የሳበበትም ወቅትም ነበር ለአብነት ሁለት ዙር በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በክቡር አቶ ዕርስቱ ይረዳው የተመራ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ልዑክ በዞናችን ስር የተለያዩ የልማት ሥራዎቸን የጎበኘበትና ከህብረተሰቡ ተወካዮች ጋር ውይይት በማድረግ ለተለያዩ የህዝብ ጥያቀዎች ምላሽ የተሰጠበት ነበር ለአብነት (የዛላ ወረዳ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋም፣ በኡባ ደብሬ ፀሐይ ወረዳ የበቶ ከተማ መጀመርያ ደረጃ ሆስፒታል ያልተጠናቀቁ ሥራዎች እንዲቀጥሉ ማስቻል እና የመሳሰሉ ተግበራት) ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ክብርት ዶ/ር ሊያ ታደሰ የጤና ሚኒስቴርሚንስትር እና ክብርት ወ/ሮ አለምፀሐይ ጳውሎስ የጤና ሚኒስቴር ሚ/ዴኤታ የተመራ አጠቃላይ ማነጅመነት አባላት በዞናችን ስር በተለይ የሣውላ አጠቃላይ ሆስፒታል እና የቡልቂ ጤና ጣቢያ በመጎብኘት ለሚታዩ መሠረታዊ ጉድለቶች በገቡት ቃል መሠረት ከ12 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የህክምና መሳሪያዎች አበርክተዋል፤ ከሁሉም በላይ በደም እጦት ምክንያት ውድ ህይወታቸውን የሚያጡ እናቶች ቁጥር ከፍተኛ የነበሬ መሆኑ በመረዳት በዞኑ መዲና ሣውላ ከተማ የደም መሰብሰቢያ ማዕከል /Blood Collection Center/ የፈቀዱ ሲሆን በሂደት ደረጃውን ከፍ ለማድረግ የቦታ ርክክብም ተደርጓል፡፡ መንገድ የሁሉም ልማቶች መጀመሪያ እና የጀርባ አጥንት ነው፡፡ በዞናችን ስር ትላልቅ የመንግስት ፕሮጀክቶች መካከል አንዱና ዋነኛ በኢትዮጵያ ምንገዶች ባለስልጣን እየተገነባ ያለው የሶዶ-ዲንኬ-ሣውላ-ሼፍቴ ኮንክሪቲ አስፓልት መንገድ ነው፡፡ ለዘመናት ከህዝባችን የመልማት ጥያቄዎች መካከል ቁንጮዉን የምይዝ ከመሆኑም በላይ ይህ የመንገድ ጥያቄ በትክክልኛ ጊዜ ባለመፈቀዱ ምክንያት ህዝባችን ከብዙ የልማት እንቅስቃሴዎች ወደ ሗላ በመቅረት ዋጋ ከፍሏል፡፡ በመሆኑም ፕሮጀክቱ በተቀመጠለት የጊዜ እና የጥራት ገደብ እንድጠናቀቅ በየወሩ የፕሮጀክቱ አፈፃፀም በሪፖርት እና በመስክ ምልከታ በማድረግ ጥብቅ ክትትልና ድጋፍ ስደረግ ቆይቷል ውጤትም አምጥቷል፡፡ ለላው የዞኑ አስተዳደር ህንፃ ጨረታ በመጀርያ ዙር ህጋዊ አሸናፊ ባለመኖሩ ለሁለተኛ ዙር እንዲወጣ በማድረግ ህጋዊ አሸናፊ የመለየት ሥራ ተሰርቷል፤ ፕሮጀክቱ በጥሩ ሁኔታ የተጀመረ ሲሆን እስክጠናቀቅ ድረስ አስፈላጊ ድጋፍ ሁሉ አደርጋለሁ፡፡ ከአጎራባች መዋቅሮች ጋር የጋራ በሚያደርጉን አጀንዳዎች ዙሪያ በሠላምና ፀጥታ ሥራዎች አልፎ አልፎ በሚፈጠር የወሰን ግጭት፣ ጊዜውን ጠብቆ በሚፈጠር የቤት እንስሳት ዝርፍያና የሠዎች ግድያ ዙሪያ ከባስከቶ ልዩ ወረዳ፣ ከደቡብ ኦሞ ዞን እና ከቤንቺ ሼኮ ዞን ጋር በጋራ ስንሠራ ቆይተናል ተጨባጭ ለውጥ አስመዝግበናል፤ በህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ከጋሞ እና ከደቡብ ኦሞ ዞን ጋር በመናበብ ተስርቷል፡፡ በንፁ ውሃ መጠጥ፣ በትምህርት፣ በመንገድ፣ በጤና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ያለው ችግር ሰፊ ከመሆኑ እንፃር የቅድምያ ቅድምያ የሚሰጣቸውን በመለየት ደረጃ በደረጃ ለመቅረፍ ተሞክሯ ል፡፡ በወጣቶች የሥራ እድል ፈጠራ፣ የህግ የበላይነት እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን አቅም በፈቀደ መጠን ለመፍታት ከዞኑ እና አጠቃላይ መዋቅር አመራሮች ጋር ሰፊ ጥረት ተደርጎል፡፡ በመጨረሻም ከግለኝነት፣ ከአሻጥር፣ ከሠረኝነት፣ ከቡድንተኝነት፣ ከመጠላለፍ እና ከመጠፋፋት ፖለቲካ ወጥተን በህዝባችን ላይ አለቃ ሳይሆን የህዝቡ እውነተኛ አገልጋይ መሪ በመሆን በፍፁም መሠጠት፣ ቅንነት፣ ታማኝነት እና ንፅህና ማገልገል ይገባል፡፡ የብልፅግና ጉዟችን አንዱና ዋነኛው አደጋ ሌብነት እንደመሆኑ መጠን በተለይ በኦይዳ፣ ዛላ እና ሣውላ ከተማ አስተዳደር ለተነሱ የህግ የበላይነት፣ የህዝብ ሀብት አጠቃቀም የግልፀኝነትና ብክነት ችግር ጥቆማዎች መነሻ በማድረግ ባጠረ ጊዜ ህጋዊ የማጣራት ሥራ በመሥራት አብዛኛዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ ተወስዷል፡፡ ቀሪዎች ላይ ተገቢ እና ህጋዊ ማጣራት እየተደረገ ይገኛል፡፡ ህዝባችንን በተለያዩ አጀንዳዎች ዙሪያ በማስተባበር ከፍተኛ የህብረተሰብ ተሳትፎ ተግባራት አከናውነናል፡፡ የጎፋና ኦይዳ ህዝቦች በሀገር አንንድነት እና ሉአላዊነት የማይደራደሩ በተግባር እስከ ግንባር በመዝመት ከወንድም ኢትዮጵያን ጋር ወራርውንፋሽስት የጣልያን ጦር በአድዋ በማሸነፍ በመላው የጥቁር ህዝቦች ታሪክ ደማቅ ታሪክ ፅፈዋል፤ በተጨማሪ ወራርውን የሶማሊያ ጦር በካራማራ ድባቅ ስመታ የህዝባችን ተጋድሎና ጀግንነት ታላቅ ነበር፡፡ ለዚህ ታርካዊ ጀብድ በሀገራችን መዲና በአዲስ አበባ ‘’የጎፋ ሰፈር’’ ህያው ምስክር ነው፡፡ ይህ አርበኝነታቸው ለዘመናት ሳይበርድና ሳይቀዘቅዝ ስለመዝለቁ እንቁ ልጃችን ምክትልአስር አለቃ ገበያነሽ ደባልቄ የሠራችው ገድል ምስክር ነው፡፡ በአሁኑ ትውልድ በሰሜን ዕዝ የመከላለያ ሠራዊታችን ላይ በጁንታው የህወሃት ቡድን በተፈጠረ ክህደት እና በተካሄደ እጅግ አሰቃቂ ጭፍጨፋ ምክንያት እጅግ በጣም በአጭር ጊዜ ውስጥ ህዝባችንን ከጫፍ ጫፍ በማስተባበር የመጀመሪያው ዙር ድጋፍ እንደ አዲስ ዞን ሳይሆን በክልሉ ካሉ ነባር እና ከሁሉም ዞኖች ከፍተኛውን ድጋፍ በአይነትና በቁጥር 203 ሰንጋ፣ 16 ፍየል፣ 4 በግ በተጨማሪ 4 ሚሊዮን ብር ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የገንዘብድጋፍ የተሰበሰቤ ሲሆን በአጠቃላይ ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረግ ተችላል፡፡ለላው በመሎ ላሃ እና በቶ ከተማ አስተዳደር በከፍተኛ የህብረተሰብ ተሳትፎ የከተማ ውስጥ ለውስጥ የመብራት ዝርጋታ እና ለሎች የልማት ሥራዎች እንደ ምርጥ ተሞክሮ በመውሰድና እውቅና በመስጠት በአመራር ተልዕኮ ወደ ሁሉም የዞኑ ከተሞች ማስፋት ተችሏል፤ በተለይ በኦይዳ ወረዳ ሸፍቴ ከተማ፣ ዛላ ወረዳ በአጭር ጊዜ አመሪቂ ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል፡፡ በዞናችን ስር አዳዲስ 3 መዋቅሮች ምስረታ ማካሄድ ችለናል፤ በዚህም መሠረት የመሎ ጋዳ ወረዳ ከዞኑ መዋቅር መፈቀድ ጋር አብሮ የተፈቀደ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች ይፋዊ የምስረታ መርሃ-ግብር ሳይደረግ ቆይቷል፡፡ ይሁን እንጂ የካቲት 07/ 2013 ዓ/ም የዕለቱ ክብር እንግዳ የተከበሩ አቶ ተስፋዬ በልጂጌ የዴሞክረሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚንስትር፣ ለሎች ከፍተኛ የክልልና ዞን ከፍተኛ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት እጂግ ደማቅ በሆነ ስነ-ስርአት ተመስርቷል፡፡ ተጨማሪ በክልሉ መንግስት ውሳኔ መሠረት የመሎ ኮዛ ወረዳ መቀመጫ ላሃ ከተማ እና የዑባ ደብረፃይ ወረዳ መቀመጫ የበቶ ከተማ ወደ ከተማ አስተዳደርነት እንዲያድጉ ተደርጓል፡፡ ለአንደ አከባቢ ሁለንተናዊ እድገት የአካባቢ ልህቃን በወሳኝ ጉዳዮች ላይ አንድነት እና ወንድማማችነት ወሳኝ ጉዳዮች ናቸው፤ ከዚህ አንፃርዞናቸችን ጠንካራ፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ እና ተደማጭ ዞን ለማድረግ እንዲያስችለን የዞኑ የመጀመሪያ የዞኑ ምሁራን የአንድነት እና የመግባባት መድረክ በሀዋሣ ከተማ በተሳካ ሁኔታ አካህደናል፡፡ በሂደቱ አሸናፊም ሆነ ተሸነፊ የለም፤ አሸናፊ ሰፊው ህዝባችን ነው፡፡ በማህበራዊ ዘርፍ የጎፋ ባራንቼ እግር ኳስ ቡድን በወንዶችም በሴቶችም የዞኑ ምልክት Brand እንደመሆናቸው መጠን ከፍተኛ ውጤት እንዲያስመዘግቡ በጀት ከመመደብ እና ተጨማሪ ሀብት ከማሰባሰብ ባለፈ የልምምድ ወቅት እና ከመዳ ውጭ በሚደረጉ ጫወታ በአካል በመገኘት የማበረታታት ሥራ በመሥራት አንፃራዊ ውጤት ማምጣት ተችሏል፡፡ ለላው አቅመ ደካማ እና የጎዳና ተዳዳሪ ወገኖቻችንን ከሣውላ ከተማ አስተዳደር ጋር በመቀናጀት በጌና በዓል የምሳ ግዣ ማድረግ ተችሏል፡፡ የፕሮጀክት ሥራዎችን በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብና የጥራት ደረጃ ማጠናቀቅ የግድ ይላል፤ ከዚህ አንፃር በኦይዳ ወረዳ ጎይብ ቀበሌ የንፁህ ዉኃ መጠጥ ፕሮክት በHope International Ethiopia የገንዘብ ድዳፍና 10% የህብረተሰብ ተሳትፎ በ3 ወር ጊዜ ውስጥ አጠናቀን በማስመረቅ አገልግሎት እንድሰጥ ተደርጓል፡፡ በዞን የምስተዋለውን የቢሮ ጥበት ለመቅረፍ በዞኑ አስተዳደር ወጪ በ4 ሳይቶች እየተገነቡ የነበሩ G+0 ህንፃዎች አስፈላጊ የዲዛይን ለውጥ በማድረግ፣ ባለሙያ በመመደብ እና በአካል በየጊዜ ክትትል በማድረግ በአጭር ጊዜ ጊዜያዊ የዞኑ አስተደዳደር ጽ/ቤት፣ ሱካ፣ ሰዝጋ እና ቁፄ G+0 በማስመረቅ ወደ አገልግሎት እንዲገቡ ተደርጓል፡፡ ዞናችን እጅግ በጣም ከፍተኛ የተፈጥሮ ሀብት ክምችት እና አቅም(Potential) ያለው ዞን ነው፡፡ ዞናችን በ3ቱ የአየር ፀባይ ማለትም በደጋ፣ በወይና ደጋ እና በቆላ የሚከፈል በመሆኑ ለተለያዩ ምርቶች ምቹ ነው፤ ለአብነት ቡና፣ ሰሊጥ፣ ኮሮሪማ፣ ዝንጅብል፣ ለውዝ፣ ጤፍ፣ በቆሎ፣ ሙዝ፣ አሪቲ እና ወዘተ በስፋት ይመረታል፡፡ በተጨማሪ የቁም ከብት ስርጭት በክልሉ ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል፡፡ በቱሪዝም ዘፍር ሆቴል፣ ሪዞርት እና ሎጅበተጨማሪነት የታሸገ ውሃ የኢንቨስትመነት ዘርፍ በለሎችም ዘርፎች ተሰማርተው ራሳቸውንና ሀገራቸውን እንድጠቅሙ በዝህ አጋጣሚ ጥሪዬን ማስተላለፍ እወዳለሁ፡፡ የኮይሻ የኤለክትሪክ ሀይል ማመንጫ ፕሮጀክት እና የኮይሻ ገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ለዞናችን ህዝብ ትልቅ የመልማት እድል ይዞ የመጣ ነው፡፡ በተለይ ሣውላ ከተማ ለአካባቢው በአቀማማጥ ማዕከል ያደርጋታል፤ ሣውላ ለ5 መስመሮች መተላለፍ እና መዳረሻ ያደርጋታል፡፡ 1ኛ- ከሣዉላ- ቡልቂ- መሎ ላሃ- ኮይሻ- ጂማ- አዲስ አበባ፣ 2ኛ ሣዉላ- ሶዶ- አዲስ አበባ፣ 3ኛ ሣዉላ- ዛላ- ካምባ- ገረሴ- አርባ ምንጭ- አዲስ አበባ፣ 4ኛ ሣዉላ- ኦይዳ- ደማ- ደቡብ ኦሞ ጂንካ እና 5ኛ ሣዉላ- ዛላ- ቤቶ- ደቡብ ኦሞ ጂንካ፡፡ አብዛኛዎቹ የቱሪስት ምንቀሳቀሻ መስመሮች ናቸው፡፡ ይህን ትልቅ የመልማት እድል አስቀድሞ በመረዳት አስፈላጊና ተገቢ ርብርብ አንዲደረግ ህዝባችንን የማንቃት ሥራ የጀመርን ቢሆንም በስፋት ህዝቡን፣ የአከባቢውን ባለሃብት ብሎም ኢንቨስተሮችን በውል ማስረዳት ያስፈልጋል፡፡ ዞናችን የከፍተኛ ባለስልጣነት ትኩረት የሳበበትም ወቅትም ነበር ለአብነት ሁለት ዙር በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በክቡር አቶ ዕርስቱ ይረዳው የተመራ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ልዑክ በዞናችን ስር የተለያዩ የልማት ሥራዎቸን የጎበኘበትና ከህብረተሰቡ ተወካዮች ጋር ውይይት በማድረግ ለተለያዩ የህዝብ ጥያቀዎች ምላሽ የተሰጠበት ነበር ለአብነት (የዛላ ወረዳ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋም፣ በኡባ ደብሬ ፀሐይ ወረዳ የበቶ ከተማ መጀመርያ ደረጃ ሆስፒታል ያልተጠናቀቁ ሥራዎች እንዲቀጥሉ ማስቻል እና የመሳሰሉ ተግበራት) ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ክብርት ዶ/ር ሊያ ታደሰ የጤና ሚኒስቴርሚንስትር እና ክብርት ወ/ሮ አለምፀሐይ ጳውሎስ የጤና ሚኒስቴር ሚ/ዴኤታ የተመራ አጠቃላይ ማነጅመነት አባላት በዞናችን ስር በተለይ የሣውላ አጠቃላይ ሆስፒታል እና የቡልቂ ጤና ጣቢያ በመጎብኘት ለሚታዩ መሠረታዊ ጉድለቶች በገቡት ቃል መሠረት ከ12 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የህክምና መሳሪያዎች አበርክተዋል፤ ከሁሉም በላይ በደም እጦት ምክንያት ውድ ህይወታቸውን የሚያጡ እናቶች ቁጥር ከፍተኛ የነበሬ መሆኑ በመረዳት በዞኑ መዲና ሣውላ ከተማ የደም መሰብሰቢያ ማዕከል /Blood Collection Center/ የፈቀዱ ሲሆን በሂደት ደረጃውን ከፍ ለማድረግ የቦታ ርክክብም ተደርጓል፡፡ መንገድ የሁሉም ልማቶች መጀመሪያ እና የጀርባ አጥንት ነው፡፡ በዞናችን ስር ትላልቅ የመንግስት ፕሮጀክቶች መካከል አንዱና ዋነኛ በኢትዮጵያ ምንገዶች ባለስልጣን እየተገነባ ያለው የሶዶ-ዲንኬ-ሣውላ-ሼፍቴ ኮንክሪቲ አስፓልት መንገድ ነው፡፡ ለዘመናት ከህዝባችን የመልማት ጥያቄዎች መካከል ቁንጮዉን የምይዝ ከመሆኑም በላይ ይህ የመንገድ ጥያቄ በትክክልኛ ጊዜ ባለመፈቀዱ ምክንያት ህዝባችን ከብዙ የልማት እንቅስቃሴዎች ወደ ሗላ በመቅረት ዋጋ ከፍሏል፡፡ በመሆኑም ፕሮጀክቱ በተቀመጠለት የጊዜ እና የጥራት ገደብ እንድጠናቀቅ በየወሩ የፕሮጀክቱ አፈፃፀም በሪፖርት እና በመስክ ምልከታ በማድረግ ጥብቅ ክትትልና ድጋፍ ስደረግ ቆይቷል ውጤትም አምጥቷል፡፡ ለላው የዞኑ አስተዳደር ህንፃ ጨረታ በመጀርያ ዙር ህጋዊ አሸናፊ ባለመኖሩ ለሁለተኛ ዙር እንዲወጣ በማድረግ ህጋዊ አሸናፊ የመለየት ሥራ ተሰርቷል፤ ፕሮጀክቱ በጥሩ ሁኔታ የተጀመረ ሲሆን እስክጠናቀቅ ድረስ አስፈላጊ ድጋፍ ሁሉ አደርጋለሁ፡፡ ከአጎራባች መዋቅሮች ጋር የጋራ በሚያደርጉን አጀንዳዎች ዙሪያ በሠላምና ፀጥታ ሥራዎች አልፎ አልፎ በሚፈጠር የወሰን ግጭት፣ ጊዜውን ጠብቆ በሚፈጠር የቤት እንስሳት ዝርፍያና የሠዎች ግድያ ዙሪያ ከባስከቶ ልዩ ወረዳ፣ ከደቡብ ኦሞ ዞን እና ከቤንቺ ሼኮ ዞን ጋር በጋራ ስንሠራ ቆይተናል ተጨባጭ ለውጥ አስመዝግበናል፤ በህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ከጋሞ እና ከደቡብ ኦሞ ዞን ጋር በመናበብ ተስርቷል፡፡ በንፁ ውሃ መጠጥ፣ በትምህርት፣ በመንገድ፣ በጤና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ያለው ችግር ሰፊ ከመሆኑ እንፃር የቅድምያ ቅድምያ የሚሰጣቸውን በመለየት ደረጃ በደረጃ ለመቅረፍ ተሞክሯ ል፡፡ በወጣቶች የሥራ እድል ፈጠራ፣ የህግ የበላይነት እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን አቅም በፈቀደ መጠን ለመፍታት ከዞኑ እና አጠቃላይ መዋቅር አመራሮች ጋር ሰፊ ጥረት ተደርጎል፡፡ በመጨረሻም ከግለኝነት፣ ከአሻጥር፣ ከሠረኝነት፣ ከቡድንተኝነት፣ ከመጠላለፍ እና ከመጠፋፋት ፖለቲካ ወጥተን በህዝባችን ላይ አለቃ ሳይሆን የህዝቡ እውነተኛ አገልጋይ መሪ በመሆን በፍፁም መሠጠት፣ ቅንነት፣ ታማኝነት እና ንፅህና ማገልገል ይገባል፡፡



ዶ/ር ጌትነት በጋሻው


ከሁሉ አስቀድሜ በአስቸጋሪና ዉስብስብ ፈተና ውስጥ በጽናት በማለፍ በሀገራችን የተጀመረዉ የለውጥና ብልጽግና ጉዞ ለመላዉ ኢትዩጵያዊያን በተለይ ደግሞ ለዞናችን ህዝቦች ያመጣቸዉን እጅግ አጓጊ የለዉጥ ትሩፋቶችና የፈነጠቀዉን ተስፋ ይበልጥ ለማስቀጠል፣ ለውጡ በምንም አይነት መንገድ እንዳይቀለበስ የበኩላቸዉን ያልተቆጠበ ድጋፍ በማድረግ ላይ ያሉ የዞናችን ህዝቦች በድጋሚ በዞን ዋና አስታዳዳሪነት እንዳገለግል ከፍተኛ እምነት በመጣል መሪዉ ፓርቲና የተከበረዉ ምክር ቤት ለሰጠኝ ታሪካዊ እድልና ህዝባዊ አደራ የተሰማኝን ልባዊ ደስታ እገልጻለሁኝ፡፡ ከአጓጊና አስደናቂ የለውጥ ጅማሮና ትልቅ ተስፋ ጎን ለጎን ቀላል የማይባልና የሁላችንም ትብብር የሚፈልጉ ተግዳሮቶችና ሥጋቶችን እያስተናገደች ባለችዉ ሀገራችን በየትኛዉም ደረጃ ቢሆን መንግስትና ህዝብን ማገልገል ዕድልም ፈተናም መሆኑ እዉን ነዉ፡፡ የውጭና የውስጥ ፈተናዎች ሀገራዊ ህልውናችንን እየተፈታተኑና ስጋት ላይ እየጣሉ ባለበት ነባራዊ ሁኔታ ውስጥም ሆነን በህገመንግስቱ ድንጋጌ መሠረት ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ አካሂደን በህዝብ ዘንድ ቅቡልነት ያለው መንግስት እየተመሰረት ባለበት ሁኔታ ምንም አይነት ፈተናና ተግዳሮት ቢኖር ህዝብንና መንግስትን ማገልገል ታሪካዊ ዕድልም አደራም ነዉ፡፡ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በታሪካችን ካካሄድናቸው ምርጫዎች የፖለቲካ ምህዳሩ ለተፎካካሪ ፓርቲዎች ምቹና በነጻነት ሀሳባቸውን ያራመዱበት፣ በስልጣን ላይ ያለው ፓርቲና ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጠንካራ የሀሳብ ትግል ያደረጉበት፣በዚህም ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና በህዝብ ዘንድ ቅቡልነት ያለው ብሎም ኢትዮጵያ አሸናፊ ሆና የወጣችበት ሆኖ መጠናቀቁን ተከትሎ በክልልና በፌዴራል ደረጃ ቅቡልነት ያለው መንግስት የመመስረት ሂደት ስኬታማ በሆነ መልኩ ማስኬድ ተችሏል። አዲስ የተመሰረተዉ መንግስት የህዝቡን የሰላም፤ ልማትና መልካም አስተዳደር ፍላጎት ለማሟላት በሚያደርገዉ ጥረት ዉስጥ እንደ ጎፋ ዞን አስተዳደርም የተጀመረውን ሁሉ አቀፍ የልማትና መልካም አስተዳደር ሥራዎች ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገርና በምርጫ ወቅት ለህዝባችን ቃል የገባንባቸዉ ማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ፤ የሰላም፤ መልካም አስተዳደርና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ጥያቄዎች እዉን ለማድረግ መላዉ የዞናችንን ሕዝቦችና የልማት ኃይሎች በማሳታፍ፤ በማስተባበርና በማቀናጀት የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ርብርብ ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በአካራሪዉ ህወሃት መራሹ ቡድን የተቀሰቀሰዉ ጦርነት፤ የዜጎች ሞትና መፈናቀል፤ እንዲሁም ይህንን በመጠቀም በእጅ አዙር የራሳቸውን አጀንዳ ሊያስፈጽሙ የሚሹ የውጭ ሀይሎች በመቀናጀት የከፈቱብን የፕሮፖጋንዳና ኢፍትሃዊ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ፤ መላዉ አመራራችንና ህዝባችን እንደ ከዚህ ቀደሙ እጅ ለእጅ በመያያዝና በአንድነት በመቆም የተጋረጠብንን ሀገራዊ የህልውና አደጋ ሙሉ በሙሉ ልንቀለብስና የጀመርነውን የለውጥና የብልጽግና ርዕያችንን ከግብ ለማድረስ በጋራ ርብርብ ልናደርግ ይገባል!!! ብዝሓነታችንና እሴቶቻችን በታሪክ ሀዲድ ለረጅም ዘመናት እየተሳሰሩና በማይፈታ መልኩ ይበልጥ እየተጋመዱ የመጡ የኢትዮጵያዊነታችንና ሀገራዊ አንድነታችን መገለጫ፣ የትናንት ትሩፋትና የዛሬ ውበታችን መሆኑ እዉን ነዉ። ሆኖም ከለዉጡ በፊት በነበሩት የአገዛዝ ዓመታት ስለአንድነታችን ብሎም የጋራ ማንነታችንና እሴቶቻችን ከማሰብ ይልቅ ስለልዩነቶቻችን ይበልጥ እንድናብሰለስል በማድረግ እርስ በእርስ እንድንጠራጠር፣ በጠላትነት እንድንተያይ፣ እንዳንተማመን በማድረግ የራስን ድብቅ ፍላጎት ለማስፈጸም፤ ይህ ካልተሳካ በደንታ ቢስነት ሀገር ለማፍረስ ጭምር ወደ ኋላ እንደማይሉ ማየት ተችሏል። ስለሆነም በዞናች የሚገኙ የጎፋና የኦይዳ ብሔረሰቦች እንዲሁም መላዉ ህዝባችን ለዘመናት ተዋደዉና ተጋምደዉ በፍቅር፤ በአብሮነት፤ በመተሳሰብ የገነቡትን የስነልቦና አንድነት፤ ትስስር፤ የጋራ ማንነት አጠናክረን በማስቀጠል የህዝባችንን የልማትና መልካም አስተዳደር ፍላጎት በፍትሃዊነት ለማሟላት ልንተጋ ይገባል፡፡በየደረጃዉ ያሉ አመራሮቻንና የመንግስት ሰራተኞች፣ምሁራን፣ወጣቶች፣ ሴቶች፣በትምህርት ገበታ ላይ ያሉ ተማሪዎችና ታዳጊዎች ብሎም መላዉ ህብረተሰባችን ለጎጠኛና ከፋፋይ ኃይሎች ትርክት ሰለባ ሳይሆኑ፣ በሀገርና ህዝብ ጉዳይ ላይ እንደ ጥንት አባቶቻችን ያለ ልዩነት በጋራ በመቆም፣ አንድ ሆነን በጋራ ማንነት ተሳስረን በሁሉም መስክ ለብልጽግና ርብርብ በማድረግ የማይተካ ሚና መጫወት ይጠበቃል፡፡ ዞናችንን ብሎም ህዝባችንን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ እንድንችልና በቀጣይም የበለጸገች ሀገር፣ ክልል ብሎም ዞን ለመገንባት የጀመርነዉን የብልጽግና ጉዞ አጠናክረን ለማስቀጠል በየዓመቱ የኢኮኖሚ ዕድገትና የልማቱን ቀጣይነት ማረጋገጥ ወሳኝ በመሆኑ ባለፉት ዓመታት በማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ሌሎች ዘርፎች የታዩትን ችግሮች በማስተካከል በልማት በዴሞክራሲ ሥርዐት ግንባታና በመልካም አስተዳደር መስኮች ያገኘናቸዉን መልካም ተሞክሮዎች በማጠናከር በሁሉም ዘርፍ ሀገራዊ ለዉጡን የሚመጥኑ ተግባራትን ለመፈጸም የሚያስችል አቅም ገንብተን በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ ይጠበቅብናል፡፡ ዞናችን ያለዉ እምቅ የተፈጥሮና የምርት አቅም ከፍተኛ ቢሆንም፤ ምድሩ ለምለም፤ጋራ ሸንተረሩ የበርካታ ወንዞችና ምንጮች መፍለቂያ፤ ምቹ አየርና የተፈጥሮ ፀጋ የታደልን ቢሆንም በግብርናዉ መስክ በተለይ በሰብል፤ ጥራጥሬ፤ ቡናና ሻይና ቅመማ ቅመም፤ እንስሳት ሀብት ልማት ዘርፍ ምርትና ምርታማነት በማሳደግ የአርሶ አደራችንን ብሎም የመላዉ ህዝባችንን ተጠቃሚነት ከማረጋጋጥ አኳያ ከአመለካከት ጀምሮ ቴክኖሎጂ መጠቀምና ማስፋፋት እንዲሁም ቁርጠኛ አመራርና በቂ ሙያዊ ድጋፍም ከመስጠት አንጻር በሁሉም መዋቅሮቻችን ከፍተኛ ዉስንነት አለብን፡፡ በመሆኑም የእርሻ እና እንስሳት ሀብት ልማት ሥራ የህዝባችን የኢኮኖሚ መሠረት በመሆኑ በቀጣይ በልዩ ትኩረትና በከፍተኛ የህዝብ ተሳትፎና ንቅናቄ የሚመራ ይሆናል፡፡ በተፈጥሮ ሀብት ልማት ዘርፍ የተፋሰስ ልማት ሥራችን የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖዎችን ለመቋቋምና ምርትና ምርታማነተ ለማሳደግ ወሳኝ ተግባር በመሆኑ በልዩ ትኩረት ተጠናሮ የሚቀጥል ሲሆን አነስተኛ የመስኖ ሥራዎችን ለማከናወን የእጅ ጉድጓድ እንዲቆፈር ለማድረግ፣ ወንዞችና ጅሬቶችንና ጠልፎ ወደ ልማት ለማስገባት፣ ምንጭ የማጎልበት ሥራ ለመስራት፣ የውሃ ፓምፖችን ወደ ልማት ለማስገባት የተለያዩ ኩሬዎችና ገንዳዎችን በመጠቀምና ዘመናዊ የመስኖ አውታሮችን ወደ ልማት በማስገባት በርካታ ሄ/ር ማሳ በመስኖ እንዲለማ ይደረጋል፡፡ የአፈር ለምነትን ከማሻሻል አንጻር የተቀናጄ አፈር ለምነት ማሻሻያ ሥራዎች ይከናወናሉ፡፡ከእንስሳት ሀብት ልማት አኳያ የዝርያ ማሻሻል፤ መኖ ልማትና የእንስሳት ጤና ስራዎችን አጠናክረን እናከናዉናለን፡፡በዚህም በምግብ ራስን ከመቻል ጀምሮ በምርትና ምርታማነትና በሀገር አቀፍ ደረጃ ታዉቆ ባለሀብቶች በአካባቢዉ ሀብታቸዉን ኢንቨስት እንዲያደርጉ ለማስተዋወቅ፤ የዉጪ ምንዛሬ ማመንጨት የሚችሉ ምርቶች ለዓለም እንዲተዋወቁ፤ ለማድረግ በትኩረት ሊሰራ ይገባል፡፡ በዞናችን እየታዩ ያሉ በተፈጥሮ ሀብትና አከባቢ ጥበቃ ጉድለት እየተከሰቱ ያሉ ችግሮችን በአጭርና ረጅም ጊዜ ዕቅድ ለይቶ ለመፍታት ከፍተኛ ርብርብ የሚናደርግ ሲሆን አደጋ ስራ አመራር ፖሊሲ መሠረት የህብረተሰባችንን የአደጋ ተጋላጭነት ሁኔታ ደረጃ በደረጃ ለማስወገድ የህብረተሰቡን ተሳትፎ ማዕከል ያደረገ የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ምላሽ መረጃን ለመከታተል የተፈጥሮና ሰዉ ሰራሽ አደጋዎች መንስኤዎችን ለማቃለል በየደረጃዉ የሚገኙ መንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ የባለድርሻ አካላት ቅንጅትና የጋራ ኃላፊነት ይጠይቃል፡፡ በመሆኑም የቅድመ ማስጠንቀቂያ ምላሽ በዞኑ ሊከሰቱ የሚችሉትን የአደጋ ጠቋሚ አመላካቾችን በመጠቀም በተቻለ ፍጥነት ጥናቶችን በማካሄድ አደጋዎችን አስቀድሞ መከላከል፣ ከተከሰቱም ሊያስከተሉ የሚችሉትን ጉዳቶችን ለመቀነስ የሚያስችሉ አስቸኳይ እርምጃዎችን በመዉሰድ ወቅታዊ ምላሽ ተግባራትን ለማከናወን ከፍተኛ ጥረት ይደረጋል፡፡ የሁለተኛ ደረጃ መሬት መለካትና በካርታ የተደገፈ ሰርትፊኬት ለመስጠት፤ የተለኩ ማሳዎችን ወደብሔራዊ የገጠር መሬት መረጃ ማዕከል ለማስገባት፤ የህብረት ሥራ ሁለገብ ዩኒዬኖችን በማጠናከር ካፒታል ማሳደግ ማህበራትንና አባላትን ተጠቃሚ ለማድረግ፤ የህብረት ሥራ ማህበራ በምርት ዓይነት ግብይትና አቅርቦት ሚናቸዉን እንዲወጡ በትኩረት ይሰራል፡፡ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታን ለመተግበር የሚያስችል የአቅም መገንባት፤ የአካባቢ ጥበቃ ጉዳዩችን የተለያዩ ሚዲያዎችን በመጠቃም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ግንዛቤ ማሳደግ፤በትምህርት ቤቶች አሁን ያሉትን ነባር ክባበትን የማጠናከር ሥራ መሥራት፣ የመንግስትና የግል ባለሀብቶች ፕሮጀክቶች የአካባቢና ማህበራዊ ተፅዕኖ ግምገማ ፕሮጀክቶች የይሁንታ ፍቃድ እና የውሳኔ ሀሳብ እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ስራዎቻችንን፤ ፕላን ዝግጅትና ትግበራ፤ የመኖሪያ ቤት አቅርቦት፤ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት፤ መሬት አስተዳደር፤ ገቢ አቅም፤ ወዘተ ለማሻሻል በትኩረት ይሰራል፡፡እንዲሁም አዳዲስ ኢንቨስተሮችን ወደ አካባቢያችን በመሳብ ኢንቨስት እንድያደርጉ፤ ሥራ ፈላጊ ዜጎችን በጾታ፣ በዕድሜና በትምህርት ደረጃ የመለየት ስራ ለማከናወን፤ ለስራ ፈላጊ ዜጎችን በተለያዩ ስራ አማራጮች በቋሚና በጊዘያዊ ስራ ዕድል ለመፍጠር፤ ለአዳድስና ለነባር ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች በብቃት አሀዶች ያለባቸውን ክህሎት ለመሙላትና አቅም ለማሳደግ የተለያዩ አጫጭር ስልጠና በመስጠት፤ ነባር አንድ ማዕከላት አገልግሎት ጣቢያዎችን ድጋፍ በማድረግ በአሰራር፣ በሰው ሀይልና በማቴሪያል በማጠናከር ተጠቃሚዎች ጥራቱን የጠበቀ፣ የተሟላ እና የእድገት ደረጃን መሰረት ያደረገ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ፣ የሀገር ውስጥ የገበያ ዕድል በማመቻቸት ኢንተርፕራይዞች የገበያ ዕድል ተጠቃሚ እንድሆኑ ለማድረግ፤ አዳዲስ አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎችን በማቋቋም ነባር ኢንዱስትሪዎችን በማጠናከር ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር፤ ኢንዱስትሪዎች ከአነስተኛ ወደ መካከለኛ እንዲሸጋገሩ ለማድረግ በትኩረት ይሰራል፡፡ የንግድና ገበያልማት፤ የገቢ አሰባሰብና አስተዳደር፤ትራንስፖርትና መንገድ ልማት፤ የውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ስራዎቻችንን አሁን ካለበት ደረጃ ለማሻሻል፤ የፋይናንስና በጀት አስተዳደር ስራዎቻችንን ይበልጥ በማጠናከርና ተጠያቂነት በማስፈን ሙስናንና ብልሹ አሰራርን ያለምህረት ለማረም፤ በሁሉም መስክ ህጋዊነትን ለማስፈንና ህገወጥነትን ለመከላከል በትኩረት ይሰራል፤ ከፍተኛ ትግልም ይደረጋል፡፡ በማህበራዊ ዘርፍ የትምህርት፤ የጤና፤ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና፤ የሴቶችን ህጻናትና ወጣቶች መብትና ሁለንተናዊ ደህንነት፤ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ፤ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሀይል ልማት ስራዎች አያ የተቋማት አደረጃጀትን ለማሻሻል፤የሪፎርም አመራርና ትግበራ ሥርዓትን ማጠናከር፣በስታንዳርድ መሠረት አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትን አሠራር ማሳደግ፣የመልካም አስተዳደር ችግሮች አፈታትን ማሳደግ፣ በመንግስት ተቋማት ውስጥ የፀረ ኪራይ ሰብሳቢነት ትግል ለማጠናከር፤የሰው ሀብት አስተዳደርና የኢንስፐክሽን አገልግሎት አሰጣጥን ማሳደግ፣ የሥራ ምዘና ጥናትና ደረጃ አወሳሰን ሥርዓት ተግባራዊነትን ለማሳደግ ከፍተኛ ጥረት ይደረጋል፡፡ የዘርፉ ባለሙያዎች፤ መላዉ አመራራችንና ህዝባችን በየደረጃዉ በቅንጅት በመንቀሳቀስ የፍትህ መጓደልን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት፤ ሰላምና ፀጥታን ለማረጋገጥ፤ ወንጀልንና ህገወጥነትን ለመከላከል፤ እንዲሁም ለዜጎች ፍትሃዊና ፈጣን አገልግሎት በመስጠት የህዝብ እርካታን ለማረጋገጥ ይሰራል፡፡ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ባሉበት የአገራችንን ቀጣይነትና ህልዉና ለማረጋገጥ ህዝቡ የሰጠንን ዕድል በአግባቡ ተረድተን ኢትዮጵያዊነትን የማበልፀግና ሀገራችንን የማስቀጠል ጉዳይ ለጥያቄ የሚቀርብ ባለመሆኑ የብሔር ፅንፈኝነትና ሠፈርተኝነት በማስወገድ፤ አገራዊ አንድነት እና ህብረ ብሔራዊ ኢትዮጵያዊነት ሥነ-ልቦና እየጐለበተ እንዲሄድ ለማድረግ፤ በኢትዮጵያ አንድነት፣ ሉዓላዊነት፣ ነፃነትና አገራዊ ክብር ለማረጋገጥ፤ በጋራ ጉዳይ ላይ ከሁሉም ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችጋር ተቀራርበን በመስራት የጀመርነዉን የዲሞክራሲ ጉዞና አዲስ ምዕራፍ ወደ ስኬት ልናሸጋግር ይገባል፡፡ ከዚህ አኳያ የዞኑ አስተዳደርና በየደረጃዉ ያሉ መዋቅሮቻችንና አመራራችን በአገልጋይነት መንፈስ በመንቀሳቀስበዞናችን ፈጣን ልማት፤ የህዝብ ተጠቃሚነትና ዘላቅ እድገት ብሎም ብልጽግና ለማረጋገጥ በጋራ ርብርብ የሚደረግ ይሆናል፡፡ በመጨረሻም፤ የተከበራችሁ የዞናችን ህዝቦች መንግስት ለጣሉብኝ አደራና እምነት በድጋሚ ከልብ የመነጨ ምስጋና እያቀርብኩ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ለዞኑ አስተዳደርና በየደረጃዉ ላለዉ መዋቅርና አመራር የበኩሉን አዎንታዊ ድጋፍ፤ ሞራልና አለኝታ እንዲሰጥ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡ ፈጣሪ ኢትዮጵያና ህዝቦቿን ይባርክ!!! አመሰግናለሁ!!! ዶ/ር ጌትነት በጋሻዉ (የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ)



    facebook page

    telegram Chanal




jsCalendar


Copyright © 2021-2025 Gofa Zone Adminstration.All Rights Reserved
Gofa,Ethiopia