በኢፌዴሪ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ የተመራ የፌዴራል አመራሮች ቡድን በጎፋ ዞን ፕሮጀክቶችንና የልማት ኢኒሼቲቮችን ምልከታ
የጎፋ ዞን መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
ቀን 2024-12-11
ቡድኑ በጎፋ ዞን ኡባ ደብረ ፀሐይ እና ዛላ ወረዳዎች ባሉ ቀበሌያት በግል ባለሀብቶችና በአርሶ አደር ማሳ እየለሙ ያሉ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል። በኢፌዴሪ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ በምልከታ ወቅት በግሉ ባለሀብት ከሚተገበሩ የልማት ሥራዎች የአካባቢው አርሶ አደሮች ተሞክሮን በመውሰድ በማሳቸው እንዲተገበሩ አሳስበዋል። ቡድኑ ባደረገው ምልከታ በተለይ በሙዝ ምርት በአንድ ዘለላ እስከ 75 ኪሎ ግራም የሚመዝን ምርት እንደሚገኝ ገለፃ ተደርጎላቸዋል። ቡድኑ በምልከታው በሌማት ትሩፋት ሥራዎች በበሬ ድለባ የተሰማሩ አርሶ አደሮችን ተሞክሮ ፣ የሙዝ እርሻ፣ የሰሊጥ፣ የዶሮ እርባታ ፣ የንብ እርባታ እንዲሁም የበጋ መስኖ ሥራዎችን ምልከታ በማድረግ ላይ ይገኛል። በሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ላይ የባለሙያዎች ብርቱ ድጋፋዊ ክትትል እንደሚያስፈልግና የገበያ ዕድሎችም መመቻቸት እንዳለባቸዉ ክብርት ሚኒስትሯ አሳስበዋል። በጉብኝቱ የኢፌዴሪ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ ፣ የጎፋ ዞን አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ፣ የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የእንስሳት ጤናና ግብአት አቅርቦት ዘርፍ ኃላፊ አዲሱ ኢዮብ (ዶ/ር)፣ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የኢ- ገቨርነንስ ኃላፊ አቶ መንግስቱ በየነን ጨምሮ የጎፋ ዞን አመራሮች ተገኝተዋል።
በኢፌዴሪ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ የተመራ የፌዴራል አመራሮች ቡድን ፕሮጀክቶችንና የልማት ኢኒሼቲቮችን ምልከታ ለማድረግ
የጎፋ ዞን መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
ቀን 2024-12-11
በኢፌዴሪ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ የተመራ የፌዴራል አመራሮች ቡድን ፕሮጀክቶችንና የልማት ኢኒሼቲቮችን ምልከታ ለማድረግ ጎፋ ዞን ሣዉላ ከተማ ገብቷል። ቡድኑ ጎፋ ዞን ሣዉላ ከተማ ሲደርስ የጎፋ ዞን ም/አስተዳዳሪ እና የከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ኤርሚያስ ወሰኔ፣ የጎፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ፌተና እና ሌሎች የዞኑ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል። ልዑካኑ በዞኑ በሚኖራቸው ቆይታ ፕሮጀክቶችንና የልማት ኢኒሼቲቮችን ምልከታ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ተባብረን ከሰራን ኢትዮጵያን የብልጽግና ተምሳሌት ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካና ለዓለም ምሳሌ እናደርጋለን- ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ
የጎፋ ዞን መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
ቀን 2024-12-10
'ዲሽታ ግና' "ለሰላም፣ ለአብሮነት እና ለልማት" በሚል መሪ ሀሳብ የ 2017 የኣሪ ብሄረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል በጂንካ ከተማ ሁለገብ ስታዲየም እየተከበረ ይገኛል። በበዓሉ የተገኙት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ የኣሪ ብሄረሰብ የዘመን መለወጫ "ዲሽታ ግና" ለዘመናት ሲከበር የቆየ የብሄረሰቡ በኩርና ታላቅ በዓል መሆኑን ተናግረዋል። በዓሉ የተጣላ፣ የተኮራረፈ በፍፁም ቅንነት ፍቅርና ዕርቅን አዉርዶ የሚሻገርበት፣ የተቸገሩ ወገኖችን በመጠየቅ የሚከበር ታላቅ በዓል ነዉ ብለዋል። ጂንካ ከተማ ደምቃ ለማየታችን ሚስጢሩ የከተማዋ ነዋሪዎች ትብብርና ቅንጅት ዉጤት መሆኑን ጠቅሰዉ ሌሎች ከተሞች በጂንካ ከተማ ከመጣው ለዉጥ ትምህርት መቅሰም እንደሚችሉ ጠቁመዋል። ክልሉ ከተመሰረተ 2ተኛ ዓመቱን ብይዝም በርካታ የስኬት ተግባራት እያከናወነ እንደሚገኝ ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቅሰዋል። ህዝቡን በማስተባበር የተጀመሩ የልማት ስራዎችን አጠናክሮ መቀጠልና ወቅታዊና ጊዜያዊ ፈተናዎችን እንደሚሻገሩ ያላቸዉን ፅኑ እምነት ገልፀዋል። ተባብረን ከሰራን ኢትዮጵያ የብልጽግና ተምሳሌት ብቻ ሳትሆን ለአፍሪካና ለዓለም ምሳሌ እናደርጋለን ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ድሽታ ግና ሰላም ልማትና ብልፅግና በመሆኑ ከበዓሉ በኋላ የተጀመረው ልማት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል። የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አታ በዓሉ ለሰላም ግንባታ፣ ለብልጽግና፣ ለፍቅር ጠቃሚ የሆኑ እሴቶች ያሉት በመሆኑ የአደባባይ አከባበሩ በሁሉም አከባቢዎች ተጠናክሮ እንዲቀጥል ይሰራል ብለዋል። ዲሽታ ግና እና ሌሎች የባህል እሴቶች ከአከባቢው አልፈዉ የዓለም ሀብት እንዲሆኑ የተጀመሩ የምርምርና የማስተዋወቅ ስራዎችን ይቀጥላሉ ብለዋል። ለ 9ኛ ጊዜ እየተከበረ በሚገኘው የዲሽታ ግና የዘመን መለወጫ ዋዜማ የፓናል ዉይይት የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ተወካይ ዶ/ር ተስፋነሽ ቶላረ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ባዉዲን ጨምሮ የምክር ቤት አባላት፣ የቢሮ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል።
ያግኙን
☏046-777-1536
ተዛማጅ ሊንኮች
Copyright © 2021-2025 Gofa Zone Adminstration.All Rights Reserved
Gofa,Ethiopia